30 days ago
ሮቦት ውሻዎ ሊሰሚሩ ነው
#ethiopia | የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር ከስካይቦርን (Skyborne) ኩባንያ ጋር በ6.5 ሚሊዮን ዶላር የተፈራረመው ስምምነት፣ ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የታጠቁ የሮቦት ውሾችን ወደ ጦር ግንባር በይፋ ሊቀላቅል መሆኑ ተሰምቷል።
ኮዲያክ (CODiAQ) የተሰኘውና ዘመናዊ የጦር መሣሪያዎችን የታጠቀው ይህ ሮቦት፣ በተለይ ወታደሮች ከፍተኛ የሕይወት መስዋዕትነት ሊከፍሉባቸው በሚችሉ አስቸጋሪ የፊት መስመር ግዳጆች ላይ እንዲሰማራ ተደርጎ የተሰራ ነው።
ሮቦቱ ጠላትን ከመሰለል ባለፈ ህንፃዎችን ዘልቆ በመግባት ጥቃት የመፈጸም፣ ፈንጂዎችን የመለየትና በጠባብ ስርጦች ውስጥ የሚደረጉ ውጊያዎችን በብቃት የመወጣት አቅም እንዳለው ተገልጿል።
በአሁኑ ወቅት ጥብቅ የታክቲክ ግምገማ እየተደረገለት የሚገኘው ይህ ቴክኖሎጂ፣ ውጤታማነቱ ሲረጋገጥ በአሜሪካ ልዩ ኮማንዶ ኃይሎች ውስጥ በቋሚነት ግዳጅ ላይ የሚሰማራ ሲሆን፤ ይህም የወደፊቱ የጦርነት ስልት ከሰው ኃይል ይልቅ በቴክኖሎጂ ውጤቶች ላይ ጥገኛ እየሆነ መምጣቱን የሚያሳይ ትልቅ እርምጃ ሆኖ ተመዝግቧል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu
#technology #militaryrobot #ai #skyborne #codiaq #futurewarfare #innovation #defensenews

Comments