1 day ago
በየዓመቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ60 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ህይወታቸውን ያጣሉ
#ethiopia | በየዓመቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ60 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በተለያዩ ምክንያቶች ህይወታቸውን እንደሚያጡ መረጃዎች ጠቁመዋል።
የሞት ምጣኔ በሀገራት መካከል በከፍተኛ ሁኔታ የሚለያይ ሲሆን ዋና ዋና ምክንያቶቹ የዕድሜ ስብጥር የአረጋውያን ቁጥር መብዛት ደካማ የጤና ስርዓት ጦርነትና ግጭት ዋነኞቹ ናቸው።
ከሰሀራ በታች ባሉ ሀገራት እንደ ድህነት ያሉ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጽዕኖዎች ለሞት ምጣኔው ከፍተኛ መሆን እንደምክንያትነት ይጠቀሳሉ።
በተጨማሪም በሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ደግሞ በቂ የህክምና አቅርቦት አለመኖር ተላላፊ በሽታዎች እና የእናቶችና ህፃናት ሞት ምጣኔ ከፍተኛ መሆን ዋና ምክንያቶች ናቸው።
በጦርነት ውስጥ ባሉ ሀገራት የሰው ህይወት ማጣት እና የጤና ተቋማት መውደም የሞት ምጣኔውን ከፍተኛ አድርጎታል።
በምስራቅ አውሮፓ እንደ ቡልጋሪያ እና ላቲቪያ ያለው የሞት ምጣኔ በቁጥር ከፍ ብሎ የሚታየው አረጋውያን በመብዛታቸው ምክንያት ነው ተብሏል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #worldpopulation #deathrate #europe #africa

Comments