7 months ago
☀️ "ሲስተም ጠፍቷል" ቀረ!
በ23 የአዲስ አበባ ወረዳዎች የሶላር ኃይል ተተከለ
#ethiopia | የአዲስ አበባ ሲቪል ምዝገባና የነዋሪዎች አገልግሎት ኤጀንሲ፤ አገልግሎቱን ይበልጥ ቀልጣፋ ለማድረግ እና በኃይል መቆራረጥ ምክንያት የሚፈጠረውን እንግልት ለማስቀረት በ23 ወረዳዎች ያስገነባው የሶላር ኃይል ፕሮጀክት ዛሬ በይፋ ተመርቋል።
በኮርነር ስቶን ኢንቨስትመንት ግሩፕ (Corner Stone Investment Group) አማካኝነት የተከናወነው ይህ ፕሮጀክት፤ መብራት በሚጠፋበት ጊዜ ወሳኝ የሆኑ የምዝገባ እና የነዋሪዎች አገልግሎቶች እንዳይቋረጡ ያስችላል።
በምረቃው መርሐግብር ላይ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ፕሮጀክቱ የከተማዋን አገልግሎት አሰጣጥ በቴክኖሎጂ ለማዘመንና የመሠረተ ልማት ችግሮችን ለመቅረፍ ያለውን ፋይዳ ገልጸዋል። የኃይል አቅርቦቱ መሟላት የመንግሥት ሠራተኛው ያለምንም መስተጓጎል ለነዋሪዎች አገልግሎት እንዲሰጥ ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር ጠቁመዋል።
የአዲስ አበባ ሲቪል ምዝገባና የነዋሪዎች አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ ንጉሤ እንደገለጹት ፕሮጀክቱ በተለይም የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ በሚኖርበት ወቅት የምዝገባና የነዋሪዎች አገልግሎት እንዳይቋረጥ እንደሚያስችል ገልጸዋል።
በምረቃው መርሐግብር ላይ የተገኙት የቦሌ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ እሸቱ ለማ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ ፕሮጀክቱ በኃይል መቆራረጥ ምክንያት የሚፈጠረውን የአገልግሎት መስተጓጎል ለመቅረፍ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው የገለጹት ዋና ሥራ አስፈፃሚው አክለውም፣ የፀሐይ ኃይል ቴክኖሎጂው በኃይል መቆራረጥ ምክንያት የሚፈጠርን የአገልግሎት ክፍተት አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት እንደሚያስችል ገልጸዋል።
የፕሮጀክቱን አጠቃላይ አፈጻጸምና የቴክኒክ ዝግጅት በተመለከተ የኮርነር ስቶን ኢንቨስትመንት ግሩፕ መሥራች አንዱ የሆኑት አቶ ጃራ ባልቻ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን፣ ድርጅታቸው ጥራቱን የጠበቀ የሶላር ቴክኖሎጂን ለተቋማቱ በማቅረቡ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል በቀጣይ በሌሎችም ተቋማት መሠል ስራዎችን ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል። አያይዘውም ለተገልጋይ ህዝብ እፎይታን የሚሰጥ ፕሮጀክት ለአገርና ለሕዝብ ለማዳረስ ይዘን መጥተናል ብለዋል።
በዚሁ የሶላር ኃይል ፕሮጀክት የምረቃ መርሐግብር ላይ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከተማዋ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ፣ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ጀማሉ ጀምበሩ፣ የቦሌ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ እሸቱ ለማ (ዶ/ር)፣ የአዲስ አበባ ሲቪል ምዝገባና የነዋሪዎች አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ ንጉሤ እንዲሁም የኮርነር ስቶን ኢንቨስትመንት ግሩፕ መሥራች አንዱ የሆኑት አቶ ጃራ ባልቻ እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
#addisababa #civilregistration #solarpower #cornerstoneinvestment #servicedelivery #ethiopia

Comments