2 months ago
ማንችስተር ዩናይትድ ወደ አውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ለመመለስ የሚያስችለውን እጅግ ወሳኝ ውጤት አገኘ
#ethiopia | በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ34ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ማንችስተር ዩናይትድ በሜዳው ኦልድትራፎርድ ብሬንትፎርድን አስተናግዶ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
በጨዋታው ካሲሚሮ እና ቤንጃሚን ሼስኮ የዩናይትድን የማሸነፊያ ግቦች ሲያስቆጥሩ ለብሬንትፎርድ ብቸኛዋን ግብ ማቲያስ የንሰን አስቆጥሯል።
ምንም እንኳን ብሬንትፎርድ የኳስ ቁጥጥር የበላይነት ቢኖረውም የተገኙትን አጋጣሚዎች በአግባቡ የተጠቀመው ማንችስተር ዩናይትድ ነጥቡን ይዞ መውጣት ችሏል።
ይህ ውጤት ዩናይትድ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ በ61 ነጥብ ሦስተኛ ደረጃ ላይ እንዲቀመጥና ለቀጣዩ ዓመት የሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎ እጅግ እንዲቃረብ አድርጎታል።
በሌላ በኩል ሽንፈት የገጠመው ብሬንትፎርድ በ48 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ባለፉት ስድስት ጨዋታዎች ድል መራቆቱን ቀጥሏል።
በዚህ ጨዋታ ላይ ብሩኖ ፈርናንዴዝ ለቤንጃሚን ሼስኮ ግብ መሆን ምክንያት የሆነችውን ኳስ በማቀበል በውድድር ዓመቱ ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን የማመቻቸት ብዛቱን ወደ 19 አሳድጓል።
የ34ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በዚህ ውጤት የተጠናቀቁ ሲሆን የ35ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ከሚያዚያ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የሚቀጥል ይሆናል።
#manchesterunited #brentford #premierleague #football #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

7 months ago
♦️አርሰናል ቤሬንትፎርድን በማሸነፍ መሪነቱን አጠናክሯል
Arsenal 2 - 0 Brentford
#ethiopia | መድፈኞቹ የሊጉን መሪነት አስቀጥለዋል፤ዛሬ በተደረገው የሊጉ 14ኛ ሳምንት ጨዋታ ኤምሬትስ ላይ ቤሬንትፎርድን አስተናግደው 2ለ0 በማሸነፍ ከተከታያቸው ማን.ሲቲ ጋር ያላቸውን የነጥብ ልዩነት ወደ አምስት አስፍተዋል።
አርሰናል ቤሬንትፎርድን ሲያሸንፍ የማሸነፊያውን ጎሎች ስፔንያዊው ሞሪኖ በ11ኛ እንዲሁም ተቀይሮ የገባው ቡካዮ ሳካ በ90'+1' ሁለተኛውን ጎል አስቆጥረዋል።
አርሰናል 14 የሊጉን ጨዋታዎች አድርጎ 10ሩን አሸንፎ፣በሶስቱ አቻ ወጥቶ፣በአንድ ጨዋታ ተሸንፎ በ20 የግብ ከፍየ፣በ33 ነጥብ የሊጉ መሪ ሲሆን እኩል 14 ጨዋታ ያደረገው ማን.ሲቲ በበኩሉ ዘጠኝ ጨዋታ አሸንፎ በአራቱ ተሸንፎ በአንድ ጨዋታ አቻ ወጥቶ በ16 የጎል ክፍያ በ28 ነጥብ በሁለተኛ ደረጃ ይከተላል።
69ኛ ደቂቃ ላይ የሚገኘው ሊቨርፑል በሠንደርላንድ 1ለ0 በሜዳው እየተመራ ይገኛል።
በጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ(ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል)
#arsenal #arsenalfc #brentford #gunners #gunnersforever #premierleague

Comments