3 months ago
ደም በመለገስ የእናቶችን ሕይወት እንታደግ! — ከቡና ደጋፊዎችና ከኮሌጃችን የቀረበ ጥሪ
#ethiopia | ታላቅ የሰብዓዊነት መርሐ ግብር! ኮሌጃችን ከ"ኳስ ሜዳ እና አካባቢው የቡና ደጋፊዎች መረዳጃ ዕድር" ጋር በመተባበር ልዩ የደም ልገሣ መርሐ ግብር አዘጋጅቷል።
ይህ ልገሣ በተለይ በወሊድ ወቅት ደም ለሚያስፈልጋቸው እናቶቻችን ሕይወት መትረፍ ታስቦ የተዘጋጀ ነው። አንድ ጠብታ ደም የአንዲት እናትን ሕይወት፣ የአንድን ቤተሰብ ተስፋ ሊያድን ይችላል።
መቼና የት?
ነገ ሚያዚያ 18/2018 ዓ.ም (እሁድ)
ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ
በኮሌጁ ቅጥር ግቢ — ዋናው ሕንጻ መግቢያ
የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊነት በስታዲየም ጩኸት ብቻ አይገደብም፤ እንዲህ ባሉ ወሳኝ የሕይወት አድን ተግባራት ላይም ግንባር ቀደም መሆንን ይጠይቃል።
ነገ ጠዋት ሁላችንም በኮሌጃችን ቅጥር ግቢ በመገኘት ደም በመለገስ ለወገኖቻችን አለኝታነታችንን የምናሳይበት ዕለት ነው። እናቶችን ማዳን ትውልድን ማዳን ነው!
ደምዎን ይለግሱ፣ ሕይወት ይታደጉ!
#getu #blooddonation #ethiopiabunna #savemothers #communityservice #addisababa #humanitarian #lifesaving #ደምልገሣ #እናቶችንእናድን #ኢትዮጵያቡና #አዲስአበባ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

12 months ago
የጥበብ ሰው አርቲስት ደበበ እሸቱ የዓይን ብሌን ለደምና ሕብረህዋስ ባንክ አገልግሎት ተለግሷል
#ethiopia | የጥበብ ሰው ደበበ እሸቱ ባደረባቸው ህመም ምክንያት ከዚህ አለም ቢለዩም ቃልኪዳን በገቡት መሰረት በባለቤታቸው ወ/ሮ አልማዝ እና አጠቃላይ ቤተሰቦቻቸው መልካም ፍቃድ የዓይን ብሌናቸው ለኢትዮጵያ ደምና ሕረህዋስ ባንክ አገልግሎት ስለተለገሰ የዓይን ባንክ መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር አምሳለ ጌታቸው ባሉበት ተነስቷል።
የተነሳው የዓይን ብሌን አስፈላጊው ፍተሻ ተደርጎለት ለአገልግሎት ይውላል ያሉት የዓይን ባንክ መሪ ስራ አስፈፃሚዋ ዶ/ር አምሳለ ጌታቸው በህይወት እያሉ ቃል በመግባት ደጋፊዎቻቸውና ወዳጅ ቤተሰቦቻቸውም ቃል እንድገቡ በማስተማር መልካም ሥራ ሰርተው እንዳለፉ በመግለፅ እርሳቸው ቢያልፉም ብርሃናቸውንም ስማቸውንም ከመቃብር በላይ ህያው አድርገው አልፈዋል ብለዋል።
የህይወትና የብርሃን ስጦታ
ደም ይለግሱ ብሌንዎን ቃል ይግቡ #bloodforlife #blooddonation #blooddonationcampaign
የኢትዮጵያ ደምና ሕብረ-ህዋስ ባንክ አገልግሎት

Comments