1 month ago
ፕሬዝዳንቱ ካይሮ ደርሰዋል!
#ethiopia | የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ በዛሬው እለት ግብጽ ገብተዋል።
ፕሬዝዳንቱ ካይሮ የገቡት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ ነው ሲል አልጀዚራ ዘግቧል።
ፕሬዝዳንቱ ካይሮ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በግብጹ ፕሬዚዳንት አብደል ፈታህ አልሲሲ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
ጉብኝቱ የሁለቱን ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እና አጠቃላይ ስትራቴጂካዊ አጋርነት የበለጠ ለማጠናከር ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
ሁለቱ መሪዎች በዋና ዋና ዘርፎች በተለይም በኢንፍራስትራክቸር በታዳሽ ኃይል በቴክኖሎጂ እና በሱዌዝ ካናል የኢኮኖሚ ቀጠና ውስጥ ይወያያሉ ተብሏል።
እንዲሁም በቻይና የኢንቨስትመንት ማስፋፊያ ዙሪያ ውይይት እንደሚያደርጉና አዳዲስ የስምምነት ሰነዶችን እንደሚፈራረሙ ይጠበቃል።
ግብጽ በቻይና የመሰረተ ልማት እና የንግድ መስመር ዝርጋታ እቅድ ውስጥ በመካከለኛው ምስራቅና አፍሪካ ቁልፍ ስትራቴጂካዊ አጋር በመሆኗ አዳዲስ የጋራ ፕሮጀክቶችን መተግበር ላይ ይመክራሉም ተብሏል።
የፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ጉብኝት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ዘመናትን የተሻገረ ወዳጅነት የሚያጠናክርና የሁለቱን ህዝቦች የጋራ ጥቅም ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር ነው ሲሉ ባለሙያዎች ተናግረዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgn #china #egypt #alsisi #cooperation #diplomacy #economy #hornafrica #security #middleeast

7 months ago
የሆርሙዝ ወሽመጥ መዘዝ የግብፅን ጉሮሮ የሚዘጋ ነው
#ethiopia | የግብፁ ፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ አል-ሲሲ፣ በዓለም አቀፉ የንግድና የነዳጅ መስመር የሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ (Strait of Hormuz) ላይ ሊፈጠር የሚችል ማንኛውም መስተጓጎል በግብፅ ኢኮኖሚ ላይ “ከባድ አደጋ” እንደሚጋርጥ አስጠነቀቁ።
ፕሬዝዳንቱ ይህንን መልዕክት ያስተላለፉት፣ የ10ኛው ረመዳን የድል በዓልን ምክንያት በማድረግ የሀገሪቱ የጦር ኃይሎች ባዘጋጁት ዓመታዊ የኢፍጣር መርሃ ግብር ላይ ባደረጉት ንግግር ነው።
ቁልፍ ስጋቶችና የተነሱ ነጥቦች፦
* የነዳጅ ዋጋ ንረት፦ የሆርሙዝ ወሽመጥ ለዓለም አቀፍ የኃይል አቅርቦት ወሳኝ መተላለፊያ መሆኑን የገለጹት ፕሬዝዳንቱ፣ የመስመሩ መዘጋት የነዳጅ ዋጋን ሰማይ በማድረስ በዓለም አቀፍ ደረጃ የዋጋ ንረትን እንደሚቀሰቅስ ገልጸዋል።
* በስዊዝ ካናል ላይ የሚደርስ ኪሳራ፦ ለግብፅ የውጭ ምንዛሬ ዋነኛ የጀርባ አጥንት የሆነው የስዊዝ ካናል (Suez Canal)፣ ከንግድ ፍሰት መቆረጥ ጋር ተያይዞ ከፍተኛ የገቢ ቅናሽ ሊገጥመው እንደሚችል አል-ሲሲ አሳስበዋል።
* አጠቃላይ የኢኮኖሚ ጫና፦ የነዳጅ ዋጋ መጨመር በግብፅ የውስጥ ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ላይ ተጨማሪ ጫና በመፍጠር የዜጎችን የመግዛት አቅም ሊፈትን እንደሚችል ጠቁመዋል።
ፕሬዝዳንት አል-ሲሲ አክለውም፣ ግብፅ ከቀጠናዊና ከዓለም አቀፋዊ የደህንነት ስጋቶች ጋር ተያይዘው የሚመጡ ኢኮኖሚያዊ ትንኮሳዎችን በንቃት መከታተልና መመከት እንዳለባት ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
ይህ ማስጠንቀቂያ የመጣው በቀጠናው ያለው የጂኦ-ፖለቲካ ውጥረት በዓለም አቀፍ የንግድ እንቅስቃሴ ላይ ስጋት እየፈጠረ ባለበት ወቅት መሆኑ ጉዳዩን ይበልጥ አሳሳቢ ያደርገዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #egypt #suezcanal #straitofhormuz #alsisi #globaleconomy #energysecurity #ግብፅ #ኢኮኖሚ

Comments