19 days ago
ሀገርን ከዓለም የሚያገናኘውና የብልጽግናችን መሠረት የሆነው የኢትዮጵያ አቪዬሽን
*******************************
የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዘርፍ የአየር መንገድ አገልግሎት ብቻ አይደለም፤ ይልቁንም ሀገራችንን ከዓለም ጋራ የሚያስተስር፣ የኢኮኖሚዋን የደምስር የሚያንቀሳቅስና ለብልጽግናዋ ጉዞ መሠረት የሆነ የልማቷ የጀርባ አጥንት ነው።
ኢትዮጵያ ለጊዜው የባሕር በር የሌላት ሀገር ብትሆንም፣ የአቪዬሽን ዘርፏ በሰማይ ላይ የገነባው ጠንካራ የትራንስፖርትና የሎጅስቲክስ መረብ ሀገራችንን ከዓለም አቀፉ የንግድ መረብ ጋር አገናኝቷታል።
ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ከመሰብሰብ ጀምሮ ቡና፣ አበባና ፍራፍሬን ጨምሮ ትኩስ የግብርና ምርቶችን በጥራትና በፍጥነት ወደ አውሮፓ፣ እስያና አሜሪካ ገበያዎች እንዲደርሱ በማድረግ ረገድ የካርጎ አገልግሎቱ የማይተካ ሚና ይጫወታል።
በሌላ በኩል፣ ኢትዮጵያ የአፍሪካ መዲና እንደመሆኗ መጠን በዲፕሎማቲክና በኮንፈረንስ ቱሪዝም የምታደርገው እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ በአቪዬሽን ዘርፏ ጥንካሬ ላይ የተመሠረተ ነው።
ከአፍሪካና ከዓለም ዙሪያ የሚመጡ ዲፕሎማቶች፣ ነጋዴዎችና ቱሪስቶችን በቀጥታና በተቀናጀ መንገድ ወደ አዲስ አበባና ወደተለያዩ የሀገራችን መስህቦች በማጓጓዝ የሆቴልና መስተንግዶ አገልግሎት ዘርፍ ያነቃቃል።
በተጨማሪም እንደ ነገሌ ቦረና፣ ደብረ ማርቆስ እና ባሕር ዳር ያሉ የክልል ኤርፖርቶች መስፋፋት የክልል ከተሞችን የኢንቨስትመንትና የቱሪዝም ማዕከል እንዲሆኑ ያደረገ ሲሆን፣ ይህም በቀጥታና በተዘዋዋሪ ለብዙ ሺህ ዜጎች የሥራ ዕድል ፈጥሯል።
የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዘርፍ ከአህጉራዊ የበረራ ማዕከልነቱ ባሻገር፣ የቀጣናውን የባሕር በርና የትራንስፖርት አማራጮች ለማስፋት የምታደርገውን ጥረት የሚደግፍና የኢኮኖሚ ዕቅዷን የሚያሳልጥ የሎጅስቲክስ ቅንጅት እየፈጠረ ይገኛል።
ይህ ዘርፍ ከባህርና ከየብስ ትራንስፖርት ጋር ሲቀናጅ ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ያላትን የሎጅስቲክስ የመሪነት ሚና በከፍተኛ ሁኔታ ያጎለብተዋል።
የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ እና የአውሮፕላን ጥገና ማዕከልም ዘመናዊ ቴክኖሎጂና ብቁ የሰው ኃይል በማልማት ለሀገራችን የዕውቀት ሽግግር ትልቅ መሠረት ናቸው።
በዚህም የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዘርፍ ሀገራችንን ከዓለም ጋር የሚያገናኝ የንግድ ድልድይ እንዲሁም የውጭ ምንዛሬ ግኝትና የጠቅላላ ሀገራዊ ምርት ዕድገት ዋነኛ አንቀሳቃሽ በመሆኑ፣ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት ቢባል ማጋነን አይሆንም።
በሔዋን ጌታቸው
#ethiopia #ebc #ethiopianaviation #ethiopianairlines #aviationindustry #economicgrowth #ethiopianeconomy #cargoservices #airlogistics #tourismethiopia

Comments