13 days ago
በ660 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የሚገነባው የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ መስመር የማጓጓዣ ጊዜን በ80% ይቀንሳል።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ (EIH) እና የዳንጎቴ ግሩፕ በጋራ አክሲዮን (Joint Venture) የሚያለሙት የ660 ሚሊዮን ዶላር የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ መስመር በሁለት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ወደ ሥራ እንደሚገባ በትላንትናው ዕለት ይፋ ተደርጓል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ባስተላለፉት መልዕክት "ይህ ታሪካዊ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክት የሎጂስቲክስ ወጪዎችንና መዘገየቶችን የሚቀንስ፣ የኢነርጂ ደህንነትን የሚያጠናክር እንዲሁም የኢትዮጵያ-ጂቡቲ የንግድ ኮሪደርን ውጤታማነትና ጽናት የሚያሳድግ ነው" ሲሉ ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጅቡቲ በተካሄደው የመሰረት ድንጋይ ማኖሪያ ሥነ-ስርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ነዳጅ በጭነት መኪና ሲገባ አምስት ቀናት እንደሚወስድ አንስተው፣ አዲሱ የቧንቧ መስመር ይህንን ጉዞ ወደ አንድ ቀን ዝቅ እንደሚያደርገው አስረድተዋል።
ለመሆኑ ይህ ፕሮጀክት ምን ያካትታል ?
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ቃል አቀባይ ቢልሌኔ ሥዩምን ጠቅሶ ብሉምበርግ እንደዘገበው፤ በፕሮጀክቱ ፥
- የ120 ኪሎሜትር የቧንቧ መስመር ዝርጋታን፤
- በዳሜርጆግ 375,000 ኩቢክ ሜትር እንዲሁም በደወሌ 800,000 ኩቢክ ሜትር የመያዝ አቅም ያላቸው ሁለት የነዳጅ ማከማቻ ተርሚናሎችን ግንባታ ይካሄዳል።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ (EIH) ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ብሩክ ታዬ ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት፤ የቧንቧ መስመሩ በተቋሙ እና በናይጄሪያው ዳንጎቴ ግሩፕ በጋራ አልሚነት የሚገነባና እንደሚተዳደር አንስተዋል።
ከጂቡቲ ዳሜርጆግ ወደብ እስከ ኢትዮጵያ ደወሌ የሚዘረጋው ይህ የ120 ኪሎሜትር መስመር፤ በጭነት መኪኖች ይካሄድ በነበረው ረጅም የጉዞ ሂደት ላይ ይታይ የነበረውን ቅሸባ፣ ብክነት እና ህገ-ወጥ አሰራር በዘላቂነት እንደሚቀርፍም ገልጸዋል።
ዶክተር ብሩክ አክለውም፥ ኢትዮጵያ የራሷ ዴፖ ባልነበራት ጊዜ መርከቦች ቦታ ጠብቀው ለማራገፍ ከሁለት ቀን እስከ ሁለት ሳምንት ድረስ ይወስዱባት የነበረውን መዘግየትና አሁንም ድረስ የምትከፍለውን የዲሞሬጅ (የመጠበቂያ) ወጪ እንደሚያስቀር ነው የተናገሩት።
በደወሌ የሚገነባው ሁለተኛው ዴፖ ደግሞ ከአዋሽ በተጨማሪ ለወራት የሚበቃ ስትራቴጂካዊ የነዳጅ ክምችት ከመፍጠሩም ባሻገር፣ ከኢትዮ-ጂቡቲ የባቡር ሃዲድ ጋር በመገናኘቱ ነዳጅ በቧንቧ ከተቀበለ በኋላ በባቡርና በጭነት መኪኖች ወደ አገር ውስጥ ለማሰራጨት የሚያስችል ነው።
ፕሮጀክቱ በመጪዎቹ ሁለት አመታት እንደሚጠናቀቅም ነው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ (EIH) ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ብሩክ ታዬ የገለጹት።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለፕሮጀክቱ የፋይናንስ ድጋፍ ላደረጉት ለአፍሪካ ኤክስፖርት-ኢምፖርት ባንክ (Afreximbank) ፕሬዝዳንት ዶክተር ጆርጅ ኤሎምቢ ምስጋና አቅርበዋል።
@TikvahethMagazine

በታላቁ ፕሮጀክት ማብሰሪያ ላይ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ንግግር ዋና ዋና ነጥቦች
*************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ፣ በጅቡቲ፣ በዳንጎቴ ግሩፕ እና በአፍሪካ ኤክስፖርት-ኢምፖርት ባንክ (Afreximbank) ትብብር የሚከናወነውን ግዙፍ የነዳጅ ማጓጓዣ ፓይፕላይን እና የማከማቻ ፕሮጀክት አስመልክተው ያደረጉት ንግግር ዋና ዋና መልእክቶች፦
✅የፕሮጀክቱ ዋና ዓላማ፦ በጅቡቲ ዳመርጆግ እና በኢትዮጵያ ደወሌ መካከል የሚዘረጋ የ120 ኪሎ ሜትር የነዳጅ ማጓጓዣ ፓይፕላይን እና በሁለቱም በኩል በድምሩ ከ1 ሚሊዮን ኩቢክ ሜትር በላይ የመያዝ አቅም ያላቸው የነዳጅ ማከማቻዎች ግንባታ ነው።
✅በአሁኑ ወቅት ነዳጅ በቦቴ ተጭኖ አዲስ አበባ ለመድረስ የሚወስደውን የ5 ቀን ረጅም ጉዞ ወደ 1 ቀን ዝቅ በማድረግ የንግድ፣ የኢንዱስትሪ እና የቤተሰብ ወጪዎችን በከፍተኛ ደረጃ ይቀንሳል።
✅ በቀይ ባሕር አካባቢ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚከሰቱ አለመረጋጋቶች ወቅት የኢትዮጵያን የነዳጅ ክምችት አስተማማኝ በማድረግ ዘላቂ የኃይል አቅርቦትን ያረጋግጣል።
✅ፕሮጀክቱ ከወደብ፣ ከሀይዌይ፣ ከምድር ባቡር እና ከሞጆ ዘመናዊ የሎጂስቲክስ ማዕከል ጋር እንደ አንድ የተቀናጀ ሥርዓት በመሥራት ቀጣናዊ የንግድ ተወዳዳሪነትን ያሳድጋል።
✅ የአጋሮች የሥራ ክፍፍል፦
· ጅቡቲ፦ ስትራቴጂካዊ መገኛዋን፣ የወደብ አቅሟን እና የኃይል ሎጂስቲክስ ልምዷን፤
· ኢትዮጵያ (በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በኩል)፦ ሰፊ ገበያዋን እና የሀገራዊ ኢንቨስትመንት ማሰባሰብ አቅሟን፤
· ዳንጎቴ ግሩፕ፦ የካፒታል እና የኢንዱስትሪ ትግበራ አቅሙን፤
· አፍሪካ ኤክስፖርት-ኢምፖርት ባንክ (Afreximbank)፦ የፋይናንስ ድጋፉን ያቀርባሉ።
✅ ፕሮጀክቱ የአፍሪካ ባለሀብቶችና ተቋማት በራሳቸው አቅም የአህጉሪቱን ታላላቅ የመሠረተ-ልማት ችግሮች መፍታት እንደሚችሉ ማረጋገጫ ነው።
✅ ዋናው ግብ የታቀደውን ፕሮጀክት በፍጥነት ወደ ተግባር በመቀየር ሕዝቡ በተመጣጣኝ የነዳጅ ዋጋ፣ የተቀናጀ የንግድ እንቅስቃሴ እና የላቀ ኢኮኖሚያዊ ተፎካካሪነትን በተግባር እንዲያገኝ ማድረግ ነው።
#ethiopia #djibouti #dangotegroup #afreximbank #regionalintegration #infrastructure #pmabiyahmed

4 months ago
Ethio telecom & Afreximbank Join Forces to Accelerate Africa’s Digital Future!
Ethio telecom hosted a high-level strategic engagement with senior executives from the African Export-Import Bank (Afreximbank) at its headquarters. The meeting served a powerful dual purpose: formally welcoming Afreximbank’s newly appointed Regional Director and Head of Mission for East Africa, Mr. Humphrey Nwugo, and exploring strategic financing partnerships to fuel Ethiopia’s digital transformation.
During the engagement, Ethio telecom’s CEO presented the company’s remarkable transformation journey and key achievements realized over successive strategic periods. The presentation highlighted Ethio telecom’s strong operational and financial performance, continued market leadership, expanding digital ecosystem, and its pivotal role in advancing Ethiopia’s national digital transformation agenda and inclusive socio-economic development.
Discussions focused on pairing Afreximbank’s robust continental financing capabilities with Ethio telecom’s ambitious "Next Horizon: Digital and Beyond 2028" strategy. Ethio telecom showcased its successful evolution from a traditional telecom operator into a regional tech powerhouse, highlighting the massive growth of its digital ecosystem, including telebirr, Zemen Gebeya, TeleStream, advanced cloud services, and Z-nexus.
Impressed by Ethio telecom’s strong financial performance, leadership, and regional expansion goals, the Afreximbank delegation expressed strong interest in a long-term strategic financing partnership. Both institutions are committed to moving forward with tailored financing solutions that will drive digital infrastructure, support enterprise transformation, and foster sustainable economic development across the continent.
This milestone engagement marks an exciting step toward building a more connected, inclusive, and thriving African digital economy!
#ethiotelecom #afdb #afrexim #telebirr #digitalethiopia #digitalafrica #gsma #itu #worldbank #oecd #g6countries

Sponsored by
Surafel
Comments