1 month ago
አሁንም በጭቃና በፍርስራሽ ስር የቀረ ተስፋ አለ!
#ethiopia | በኔፓል በደረሰ የጎርፍ አደጋ የሟቾች ቁጥር ከ600 በላይ ደረሰ።
*በሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ አሁንም ደብዛቸው ጠፍቷል
ባለፈው እሁድ በኔፓል በደረሰው የድንገተኛ ጎርፍ አደጋ በርካታ ቤተሰቦችን ወደ ታላቅ ሃዘንና እንባ ከቶታል።
የሀገሪቱ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ባለስልጣን ይፋ ባደረገው ልብ ሰባሪ መረጃ እስካሁን ከ600 በላይ ዜጎች ህይወት ማለፉ ተረጋግጧል።
ከዚህ በተጨማሪም ቢያንስ 2,426 ሰዎች ደብዛቸው ጠፍቶ እየተፈለጉ ሲሆን የቀሪዎቹ ህይወት ምን ላይ እንዳለ ለማወቅ ቤተሰቦቻቸው በታላቅ ጭንቀትና ህመም ውስጥ ሆነው በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ ብለዋለ።
የነፍስ አድን ቡድኖችና የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በጭቃና በጎርፍ በተሸፈኑ ስፍራዎች ውስጥ ተአምር በመጠባበቅ አሁንም ፍለጋቸውን ቀጥለዋል።
ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ ሰዎች በየመንገዱና በየፍርስራሹ ስር በመቅረታቸው የሟቾች ቁጥር አሁንም ሊጨምር እንደሚችል ባለስልጣናቱ ገልፀዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #nepal #flood #accident #earthquake #slide #unitednation #death

2 months ago
"እሳት በእኔ ላይ ምንም አይነት የበላይነት የለውም!"
#ethiopia | በ6 ዓመቱ የሰውነቱ 73 በመቶ ክፍል በእሳት የተቃጠለው ህጻን ከዓመታት በኋላ የእሳት አጥፊ ባለሙያ ሆኗል።
ከዓመታት በፊት በደረሰበት አስከፊ የእሳት አደጋ ሙሉ አካሉ በእሳት ተቃጥሎ ህይወቱ ሊያልፍ ምንም አልቀራም ነበር።
የ6 ዓመቱ ህጻን ተሪ ማካርቲ በደረሰበት ከባድ የመቃጠል አደጋ ከ73 በመቶ በላይ ሰውነቱ ቆስሎ ለአንድ ሙሉ ዓመት በሆስፒታል አልጋ ላይ ተኝቶ አሳልፏል።
በህጻንነቱ የደረሰበት ያ አሰቃቂ አደጋ በአካሉ ላይ ዘላቂ ጠባሳዎችን ቢያስቀምጥም ተሪ ግን ህይወቱን በፍርሃት ውስጥ ሆኖ ለመምራት አልፈቀደም።
ለአካለ መጠን ሲደርስ ተሪ ህይወቱን ሙሉ በሙሉ የለወጠውንና የስነ ልቦና ፍርሃት ፈጥሮበት የነበረው "እሳት" ፊት ለፊት ለመጋፈጥ ወሰነ።
በጽኑ ውድድርና ስልጠና አልፎ በዋሽንግተን የስልጠና ማዕከል የበጎ ፈቃደኛ እሳት አጥፊ በመሆን ብቃቱን አስመስክሯል።
በስልጠና ወቅት ለመጀመሪያ ጊዜ እሳት ፊት ለፊት ሲቆም ፍርሃት ቢያናውጠውም "እሳት በእኔ ላይ ምንም አይነት የበላይነት የለውም" በማለት ፍርሃቱን ድል አድርጓል።
በአሁኑ ወቅት የራሱን ተሞክሮ በመጠቀም በእሳት አደጋ የተጎዱ ህጻናትን ለማገዝና የልጅነት ጊዜያቸውን በጥሩ ሁኔታ እንዲያሳልፉ በበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ ተሰማርቶ ይገኛል።
በህይወታችን የሚያጋጥሙን ከባድ ፈተናዎችና ፍርሃቶች ለታላቅ አላማችን መነሻ ሊሆኑ ይችላሉ ሲል ተሪ ተናግሯል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesge #fire #accident #emergency #hospital

6 ልጆቿን ለማዳን እሳቱ ውስጥ ስድስት ጊዜ የተመላለሰችው ጀግና እናት!
#ethiopia | በስዊድን ኤድስቢን ከተማ የምትኖረው ኤማ ስኮልስ የተባለች እናት በመኖሪያ ቤቷ ላይ በተነሳው አሰቃቂ የእሳት አደጋ 6 ልጆቿን ሙሉ በሙሉ በህይወት ለማዳን ያደረገችው ተጋድሎ የመላው አለምን ቀልብ ስቧል።
ማለዳ ላይ በቤታቸው የሳሎን ክፍል ውስጥ ድንገተኛ አደጋ ተከሰተ።
እሳቱ በፍጥነት በመስፋፋቱ ሁለቱ ታናናሽ ወንድ ልጆቿ የማምለጫ መንገዳቸው ተዘግቶ በእሳት ነበልባል ተከበቡ።
ኤማ ለአፍታ እንኳ ሳታመነታ ልጆቿን ከነበልባሉ እሳት ታደገቻቸው።
ታላላቆቹ አራት ልጆቿ አሁንም ከላይኛው ፎቅ በቃጠሎው ተከበው እንደነበር የተረዳችው ኤማ ደረጃው በእሳት እየነደደ ወደ ላይ በመውጣት ሁሉንም ወደ በረንዳ አውጥታ ከስጋት ነፃ አደረገቻቸው።
ሆኖም ትንሿ ሴት ልጅዋ አሁንም ቤት ውስጥ እንደቀረች ስታውቅ ለሶስተኛ ጊዜ ወደ ተቃጠለው ቤት ገብታ ልጇን በህይወት ማውጣት ችላለች።
በዚህ አሰቃቂ አደጋ ምክንያት ከ6ቱ ልጆቿ መካከል አንዳቸውም ጉዳት አላስተናገዱም።
ሆኖም ኤማ 93 በመቶ የሚሆነው የሰውነቷ ክፍል በእሳት በመቃጠሉ ለሳምንታት በፅኑ ህክምና ህይወቷን ስትታገል ቆይታለች።
ከቃጠሎው በኋላ ስሜቷን ሳታውቅ ቆይታ ስትነቃ የመጀመሪያ ጥያቄዋ ስለራሷ አካል ሳይሆን "ልጆቼ በህይወት አሉ?" የሚል ነበር።
በአሁኑ ወቅት ከከባድ ቃጠሎው ያገገመችው ኤማ በአካሏ ላይ የቀሩት ጠባሳዎች የህመም ሳይሆን የፅናት እና የጥልቅ እናትነት ፍቅር መገለጫዎች በመሆናቸው በኩራት እንደምትቀበላቸው ትናገራለች።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #sweden #emma #mother #accident #fire #emergency

"ያደረግከው ነገር እጅግ አስደናቂ ነው
አሜሪካ ልክ እንዳንተ የጀግኖች ሀገር
ናት"
#ethiopia | ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የ10 ዓመቱን ህፃን ከከባድ የውሃ ማዕበል ያዳነውን ታዳጊ በነጩ ቤተመንግስት ተቀብለው አድናቆታቸውን ገለፁለት።
የራሱን ህይወት ለአደጋ አጋልጦ የ10 ዓመት ህፃን ልጅ ከሞት ያዳነው ታዳጊ በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከፍተኛ አድናቆትና የጀግንነት እውቅና ተሰጠው።
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከታዳጊው ጋር በተገናኙበት ወቅት "ያደረግከው ነገር እጅግ አስደናቂ ነው ሁሉም ሰው አይቶሃል" ሲሉ አድናቆቻቸውን ገልጸውለታል።
ህፃኑን የታደገበት መንገድ እውነተኛ የሰብአዊነት እና የደፋርነት ማሳያ በማለት ገልጸዋል።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለታዳጊው ባስተላለፉት መልእክት "አሜሪካ ልክ እንዳንተ የጀግኖች ሀገር ናት አንተ ለሀገርህ ትልቅ ምሳሌ ሆነሀል" በማለት የአሜሪካውያንን የቆራጥነትና እርስ በእርስ የመረዳዳት እሴት ያንፀባረቀ ተግባር መሆኑን አጉልተዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #america #president #donaldtrump #accident #rescueteam #recognition

Comments