2 months ago
"ተስፋን እንጂ ፍርሃትን አንቀበልም!"
- 15ኛው ዓለም አቀፍ የፓርኪንሰን ቀን በአዲስ አበባ ተከበረ
#ethiopia | የፓርኪንሰን ፔሸንት ሳፖርት ኦርጋናዜሽን ኢትዮጵያ (PPSO-E) 15ኛውን ዓለም አቀፍ የፓርኪንሰን ቀንን ዛሬ መጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ጎልፍ ክለብ በልዩ ሁኔታ አክብሯል።
የፓርኪንሰን ታማሚዎች፣ አስተማሚዎች፣ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የጤና ባለሙያዎችና የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች በተገኙበት በደመቀ ሁኔታ ተከብሯል።
በጤና ሚኒስቴር የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ሕይወት ሰለሞንን ጨምሮ የተለያዩ ኤክስፐርቶች በህመሙ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ንግግር አድርገዋል።
"ተስፋን እንጂ ፍርሃትን አንቀበልም!" በሚል መሪ ቃል የፓናል ውይይቶች፣ ዶክመንተሪ ፊልሞችና አስተማሪ ፕሮግራሞች ቀርበዋል።
የፓርኪንሰን ሕመምተኞች በህብረተሰቡ ዘንድ ተገቢውን ግንዛቤና ድጋፍ እንዲያገኙ፣ እንዲሁም በቀጣይ በዘርፉ በስፋት መሥራት እንደሚገባ ተጠቁሟል።
#getu #parkinsonethiopia #ppso #worldparkinsonsday #healthawareness #hopeoverfear #addisababa #ethiopiahealth #የፓርኪንሰንቀን #ጤና #ግንዛቤ #ተስፋ #አዲስአበባ #ጌጡተመስገን #getutemesgen