6 months ago
"ተስፋን እንጂ ፍርሃትን አንቀበልም!"
- 15ኛው ዓለም አቀፍ የፓርኪንሰን ቀን በአዲስ አበባ ተከበረ
#ethiopia | የፓርኪንሰን ፔሸንት ሳፖርት ኦርጋናዜሽን ኢትዮጵያ (PPSO-E) 15ኛውን ዓለም አቀፍ የፓርኪንሰን ቀንን ዛሬ መጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ጎልፍ ክለብ በልዩ ሁኔታ አክብሯል።
የፓርኪንሰን ታማሚዎች፣ አስተማሚዎች፣ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የጤና ባለሙያዎችና የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች በተገኙበት በደመቀ ሁኔታ ተከብሯል።
በጤና ሚኒስቴር የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ሕይወት ሰለሞንን ጨምሮ የተለያዩ ኤክስፐርቶች በህመሙ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ንግግር አድርገዋል።
"ተስፋን እንጂ ፍርሃትን አንቀበልም!" በሚል መሪ ቃል የፓናል ውይይቶች፣ ዶክመንተሪ ፊልሞችና አስተማሪ ፕሮግራሞች ቀርበዋል።
የፓርኪንሰን ሕመምተኞች በህብረተሰቡ ዘንድ ተገቢውን ግንዛቤና ድጋፍ እንዲያገኙ፣ እንዲሁም በቀጣይ በዘርፉ በስፋት መሥራት እንደሚገባ ተጠቁሟል።
#getu #parkinsonethiopia #ppso #worldparkinsonsday #healthawareness #hopeoverfear #addisababa #ethiopiahealth #የፓርኪንሰንቀን #ጤና #ግንዛቤ #ተስፋ #አዲስአበባ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

"ተስፋን እንጂ ፍርሃትን አንቀበልም!" 15ኛው ዓለም አቀፍ የፓርኪንሰን ቀን በአዲስ አበባ በደመቀ ሁኔታ ተከበረ
#fastmereja I በአዲስ አበባ ጎልፍ ክለብ ዛሬ በተካሄደው ደማቅ ሥነ-ሥርዓት፣ የፓርኪንሰን ታማሚዎችና ደጋፊዎቻቸው ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አሰምተዋል።
በፓርኪንሰን ፔሸንት ሳፖርት ኦርጋናዜሽን ኢትዮጵያ (PPSO-E) አዘጋጅነት ዛሬ መጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የተከበረው ይህ ዕለት፣ በኢትዮጵያ ለ15ኛ ጊዜ የተከበረ ዓለም አቀፍ የፓርኪንሰን ቀን ነው።
"ተስፋን እንጂ ፍርሃትን አንቀበልም!" በሚል መሪ ቃል በተከናወነው በዚህ መርሃ ግብር ላይ የጤና ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የዘርፉ የሕክምና ባለሙያዎች፣ ታማሚዎች፣ አስተማሚዎችና የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ተገኝተዋል።
በዕለቱ የጤና ሚኒስቴር የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ሕይወት ሰለሞን ባስተላለፉት መልዕክት፣ የፓርኪንሰን ሕመም በኅብረተሰቡ ዘንድ ያለውን ግንዛቤ ለማሳደግና ተገቢውን ሕክምና ተደራሽ ለማድረግ ሚኒስቴሩ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሠራ ገልጸዋል። እንደ ባለሙያዎቹ ገለጻ፣ ሕመሙ የነርቭ ሥርዓትን የሚጎዳና የእንቅስቃሴ መዛባትን የሚያስከትል ቢሆንም፣ ቀድሞ በሚደረግ ምርመራና ተገቢው ክትትል የታማሚዎችን የኑሮ ጥራት ማሻሻል ይቻላል።
መርሃ ግብሩ በፓናል ውይይቶች፣ የግንዛቤ ማስጨበጫ ዶክመንተሪ ፊልሞችና በተለያዩ አነቃቂ ንግግሮች የታጀበ ሲሆን፣ በተለይም ታማሚዎች የሚያጋጥሟቸውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫናዎች ለመቀነስ የተቀናጀ ጥረት እንደሚያስፈልግ ተመላክቷል።
የፓርኪንሰን ፔሸንት ሳፖርት ኦርጋናዜሽን ኢትዮጵያ በበኩሉ፣ ማህበሩ ላለፉት ዓመታት ለታማሚዎች ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱንና በቀጣይም የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።
መጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ.ም.
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

Comments