19 days ago
አዲስ አስመጪዎችና ላኪዎች የብሔራዊ ባንክ የሂሳብ ቁጥርን በአንድ መስኮት አገልግሎት እንዲያገኙ ፍቃድ ተሰጠ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዲስ አስመጪዎችና ላኪዎች የብሔራዊ ባንክ የሂሳብ ቁጥርን በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአንድ መስኮት አገልግሎት በኩል እንዲያገኙ ፍቃድ ሰጥቷል፡፡
ባንኩ ከኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ጋር በመተባበር አዲስ ፍቃድ ላወጡ አስመጪዎችና ላኪዎች የብሔራዊ ባንክ የሂሳብ ቁጥር አሰጣጥን የሚያቀል አዲስ የዲጂታል አገልግሎት አስተዋውቋል፡፡
አገልግሎቱ የባንኩ የሂሳብ ቁጥሮች በጉምሩክ ኮሚሽን አንድ መስኮት አገልግሎት በኩል ያለምንም ውጣ ውረድ እንዲሰጥ በማስቻል አስተዳደራዊ ሂደቶችን የሚቀንስና ፈጣን የንግድ አሰራርን የሚደግፍ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
አዲሱ አገልግሎት የሚመለከተው ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሂሳብ ቁጥር ለሚያወጡና አዲስ ፍቃድ ላገኙ አስመጪዎችና ላኪዎች ብቻ መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡
ቀደም ሲል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሂሳብ ቁጥር ያላቸው የንግድ ተቋማት ለሁሉም የገቢና የወጪንግድ ግብይቶቻቸው ይጠቀሙበት በነበረው ነባር ቁጥር መጠቀም እንደሚችሉ ባንኩ ገልጿል፡፡
ይህ አሰራር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከገቢና ወጪ ንግድ ጋር የተያያዙ አገልግሎቶችን ለማዘመን፣ የንግድ አሰራርን ምቹ ለማድረግ እንዲሁም የዲጂታል የሕዝብ አገልግሎት አሰጣጥን ለማጠናከር እያከናወነ ያለው ጥረት አካል መሆኑንም አመልክቷል፡፡
Seledadotio

2 months ago
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ወደ ቻይና ለሚላኩ ምርቶች የወጪ ንግድ ፈቃድ የመስጠት መብት ለሁሉም የሀገሪቱ የንግድ ባንኮች መፍቀዱን አስታወቀ
#ethiopia | ቀደም ሲል ወደ ቻይና ለሚላኩ ምርቶች የወጪ ንግድ ፈቃድ (Export Permit) የመስጠት ስልጣን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE) ላይ ብቻ ተወስኖ የነበረው አሰራር ሙሉ በሙሉ ተሰርዟል።
ማዕከላዊ ባንኩ ይህንን እርምጃ የወሰደው በወጪ ንግድ ላይ ያሉ ቢሮክራሲዎችን ለማቃለል፣ የዘርፉን ተወዳዳሪነት ለመጨመር እና ለላኪዎች ምቹና ፈጣን የባንክ አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ ነው።
ሁሉም ፈቃድ ያላቸው የንግድ ባንኮች ከዛሬ ጀምሮ ከተለመዱት የወጪ ንግድና የውጭ ምንዛሬ መመሪያዎች ጋር በተጣጣመ መልኩ አገልግሎቱን ለደንበኞቻቸው መስጠት እንዲጀምሩ በጥብቅ ታዟል።
ይህ አዲስ መመሪያ ላኪዎች የመረጡት ባንክ ዘንድ ሄደው ጉዳያቸውን እንዲያስፈጽሙ በር የሚከፍት በመሆኑ፣ የሀገሪቱን የንግድ እንቅስቃሴ በእጅጉ ያነቃቃል ተብሎ ይጠበቃል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#የኢትዮጵያብሔራዊባንክ #የወጪንግድ #ቻይና #ኢትዮጵያ #ባንክ #ቢዝነስ #ethiopianeconomy #nbe

Comments