3 months ago
ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ኢትዮ-ኢስታንቡል ሆስፒታልን ጎበኙ
የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ክቡር ታዬ አጽቀሥላሴ በኢትዮ-ኢስታንቡል ሆስፒታል ተገኝተው በኢትዮጵያዊያንና በውጭ ሀገር ስፔሻሊስቶች እየተከናወነ በሚገኘው የልብ ህሙማን ህፃናት የነፃ ቀዶ ጥገና አገልግሎት ተጠቃሚ የሆኑ ህፃናትን ጎብኝተዋል።
ፕሬዝዳንቱ በጉብኝታቸው ወቅት ሆስፒታሉ እያከናወነ ያለውን ዘመናዊ የሕክምና አገልግሎትና የበጎ አድራጎት ሥራ አድንቀው በኢትዮጵያ የሕክምና ዘርፉ ወደ አዲስ ምዕራፍ መሸጋገሩን ጠቁመዋል።
ለሕክምናው ቡድን አገልግሎት "Heart to Heart Children’s Aid" የተሰኘው ፋውንዴሽን ካሰባሰበው የእርዳታ ገንዘብ እና Ethio-Istanbul General Hospital ባደረገው ሙሉ የሆስፒታል አገልግሎትና የባለሙያዎች አቅርቦት በሚያደርጉት ድጋፍ ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ ሲሆን፣ በፕሮፌሰር ሳሻ የሚመራው የጣሊያኑ የ"ፔድሬ ፓዮ" የሕክምና ቡድንም በሥፍራው ተገኝቶ ከኢትዮ ኢስታንቡል ሆስፒታል ባለሙያዎች ጋር በመዋሀድ እየሰጠ ባለው አገልግሎት በ12 ቀናት ውስጥ ብቻ በአዲስ አበባ 58 በጅግጅጋ 16 በድምሩ የ74 ሕፃናት የልብ ቀዶ ጥገና በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።
የሆስፒታሉ መስራችና ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ብርሃን ተድላ እንደገለጹት፣ ኢትዮ-ኢስታንቡል ሆስፒታል አሁን የተሰሩትን 74 ህፃናት ሳይጨምር ባለፉት ሁለት ዓመታት ለ114 ሕፃናት በብር 120,000,000.00 (አንድ መቶ ሃያ ሚሊዮን ብር) በሚገመት ወጪ ነፃ ሕክምና ሰጥቷል።
ሆስፒታሉ ከተመሰረተ ሦስት ዓመት ቢሆነውም፣ ከ86 በላይ የሰብስፔሻሊስት ዶክተሮችን በመያዝ ውስብስብ የልብ፣ የካንሰር፣ የደም ስር የጭንቅላት የህብለሰረስና የአጥንት ቀዶ ጥገና ህክምናና በሌሎችም አገልግሎቶች ላይ ሰፊ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል።
አቶ ብርሃን አክለውም፣ ሆስፒታሉን ለማቋቋም ያነሳሳቸው በራሳቸው ላይ የደረሰ የሕክምና እንግልትና ዜጎች ለሕክምና ወደ ውጭ ሀገር ሄደው የሚደርስባቸውን የገንዘብ ወጪና የሞራል ጉዳት ለማስቀረት ካላቸው ራዕይ መሆኑን በመግለፅ አገልግሎቱን ከዚህ በተሻለ በስፋት ለመስጠት እንዲያስችላቸው ላቀረቡት የቦታ ጥያቄ መንግስት ትኩረት እንዲሰጥላቸው አሳስበዋል።
ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በንግግራቸው፣ "ያስተማረንን ሕዝብ ማስታወስ ትልቅ በረከት ነው" በማለት በውጭ ሀገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ወደ ሀገራቸው ተመልሰው እንዲያገለግሉ ጥሪ አቅርበዋል።
እንዲህ ያሉ ለትርፍ ብቻ ታስበው ሳይሆን ለመልካም አገልግሎት የተቋቋሙ የላቁ የሕክምና ተቋማት መኖራቸው ዜጎች ወደ ውጭ በመሄድ ከሚያወጡት ከፍተኛ ወጪና ከሚደርስባቸው እንግልት እንደሚታደጋቸውም ገልጸዋል።
በተያያዘም ክቡር ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀስላሴ ለሕክምና ቡድኑ ባስተላለፉት የምስጋና መልእክት፣ በሕፃናቱና በቤተሰቦቻቸው ላይ የታየውን ደስታ "የተስፋ ብርሃን" በማለት ገልጸውታል። በተለይም የሕክምና ቡድኑ ወደ ጅግጅጋ በመጓዝ አገልግሎት መስጠቱ የሁለቱን ሀገራት (ኢትዮጵያና ጣሊያን) ግንኙነት ይበልጥ እንደሚያጠናክር ጠቁመዋል።
በዕለቱ ምስክርነታቸውን የሰጡ ወላጆች፣ የሕክምናውን ወጪ በመሸፈን ልጆቻቸው ማሳከም ባለመቻላቸው ለዓመታት ሲሰቃዩ መቆየታቸውን ገልፀው አሁን ባገኙት ነፃ የልብ ቀዶ ጥገና ልጆቻቸው ዳግም ሕይወት ማግኘታቸውን በደስታና በምርቃት ገልጸዋል።
ይህ የህፃናት ነፃ የልብ ሕክምና አገልግሎት በቀጣይነት ወደ ኦሮሚያ፣ አማራ፥ ትግራይ፣ ሲዳማ፣ ደቡብና ሌሎችም ክልሎች በመጓዝ ቀሪዎቹን ሕፃናት ለማከም ዕቅድ መያዙን አቶ ብርሃን ተድላ ገልፀው ለዚህ ዘመቻ መሳካት ከፍተኛ አስተዋፅኦና ትብብር ላደረጉት ለጤና ሚኒስቴር፣ ለጉምሩክ ኮሚሽን፣ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ለስካይላይት ሆቴል፣ ለኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣንና ለሌሎችም በዘመቻው ለተሳተፉ የህክምና ተቋማት እንዲሁም የገንዘብ ድጋፍ ላደረጉ በጎ አድራጊዎችና ለፋውንዴሽኑ የቦርድ አባላት ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል። #ኢትዮኢስታንቡልሆስፒታል #የልብሕክምና #በጎአድራጎት #ጤና #ታዬአጽቀሥላሴ #ኢትዮጵያ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

5 months ago
❤️ አዶናይ ለታላቅ ሰብዓዊ ተግባር ወደ አሜሪካ ተጓዘ
#ethiopia | የኸርት ቱ ኸርት ቺልድረንስ ኤይድ ፋውንዴሽን (Heart to Heart Children's Aid) የበጎ ፈቃድ አምባሳደር ወጣት አዶናይ ብርሃነ፣ የልብ ሕሙማን ሕፃናትን ሕይወት ለመታደግ የሚያስችል ገቢ ለማሰባሰብ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ አቅንቷል።
የፋውንዴሽኑ መሥራችና የኢትዮ ኢስታንቡል ሆስፒታል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ብርሃን ተድላ እንደገለጹት፣ መርሃ-ግብሩ በሚከተለው መልኩ ይከናወናል፦
* የጅማሮ ቻሌንጅ፦
ነገ ቅዳሜ ማርች 14 (መጋቢት 5/2018 ዓ.ም) ከቀኑ 2:00 PM ጀምሮ የገቢ ማሰባሰቢያ ቻሌንጅ በይፋ ይጀምራል።
* የማጠቃለያ ፕሮግራም፦
ማርች 21 (መጋቢት 12/2018 ዓ.ም) በዋሽንግተን ዲሲ ማርዮት ሆቴል በሚከናወን ታላቅ ዝግጅት ይጠናቀቃል።
ጥሪ፦
በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ሕፃናቱ የሕክምና ዕድል እንዲያገኙ የበኩላቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።
የኢትዮ ኢስታንቡል ሆስፒታል አስተዋጽኦ
ሆስፒታሉ እስካሁን ባለው ቆይታው የሚከተሉትን ተግባራት አከናውኗል፦
* ለ113 ሕፃናት ነፃ የልብ ቀዶ ጥገና አድርጓል።
* ለዚህም ከ120 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ አድርጓል።
* ይህ ሥራ በአንድ ተቋም ብቻ የማይገፋ በመሆኑ፣ በፋውንዴሽኑ በኩል የወገን ድጋፍ ማሰባሰብ አስፈላጊ ሆኗል።
በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ ከ25 ሺህ በላይ የልብ ሕሙማን ሕፃናት የሕክምና ዕድል ለማግኘት በተስፋ በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ። የወጣት አዶናይ ጉዞና የፋውንዴሽኑ ጥረት የእነዚህን ሕፃናት ተስፋ ለማለምለም ያለመ ነው።
የሕፃናትን ልብ በጋራ እንታደግ!
#hearttoheart #የልብሕሙማን #አዶናይብርሃነ #ኢትዮኢስታንቡል #ሰብዓዊነት #ኢትዮጵያ #humanitarian #heartsurgery #ethiopia #getu #temesgen #getutemesgen #ጌጡ #ተመስገን #ጌጡተመስገን

Comments