19 hours ago
🔥 " በዛፍ ስር ተጠልለን ነው ያለነው፤ የዕለት ጉርስ እንኳ የለንም " - ተጎጂ አርሶ አደሮች
በደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ፣ " ምስትንክር " በምትባል ጎጥ መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ/ም ረፋድ 3:30 አካባቢ በደረሰ የእሳት አደጋ የ30 አባውራዎች 56 ቤቶች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል።
52 የሳር እና 4 የቆርቆሮ ቤቶች፣ 348 ኩንታል እህል፣ አልባሳት፣ የቤት እቃዎች፣ 8 የንብ ቀፎዎች እና ዶሮዎች ሙሉ በሙሉ ተቃጥለዋል።
ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ አርሶ አደሮች " የአደጋው መነሻ ምን እንደሆነ አናውቅም ፤ ከኩሽና ነው የተነሳው የሚል ወሬ ነው የሰማነው " ብለዋል።
" ወቅቱ የሰብል መሰብሰቢያ ስለሆነ ሁሉም ወደ ስራ ቦታ በሄደበት ወቅት ነው ቃጠሎው የተከሰተው " ሲሉ አስረድተዋል።
እሳቱ ከባድ እንደነበርና ያዩ ሰዎች ለመቆጣጠር ቢሞክሩን እንዳልቻሉ፤ የ30 አባወራዎች አንድም ንብረት ሳይተርፍ ለዕለት ጉርስ የሚሆን ነገር ሳይቀር መውደሙን ገልጸዋል።
171 የህብረተሰብ ክፍሎች ለችግር የተጋለጡ ሲሆን፣ አብዛኞቹ በእድሜ የገፉ ሽማግሌዎችና ህፃናት ናቸው።
የወረዳው አስተዳደር የመጠለያ ሸራ ያቀረበ ቢሆንም እስካሁን ምንም አይነት የምግብ ድጋፍ አልተደረገላቸውም።
አርሶ አደሮቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደተናገሩት፣ ንብረታቸው በሙሉ በመውደሙ በዛፍ ስር ተጠልለው የሚገኙ ሲሆን፣ አጣዳፊና አስቸኳይ የሰብአዊ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ጥቅምት 2 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia

1 day ago
“በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የተባባሰው ውጥረት ከፍተኛ ስጋት አሳድሮብኛል”-ኖርዌይ
የኖርዌይ መንግሥት በሰሜናዊ ኢትዮጵያ እየተባባሰ በመጣው ውጥረትና በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል እየጨመረ በመጣው ውጥረት ከፍተኛ ስጋት እንዳደረበት አስታወቀ። የኖርዌይ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፣ የኤርትራ ወታደሮች ድንበር አቋርጠው ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን የሚጠቁሙ ሪፖርቶች እጅግ አሳሳቢ መሆናቸውን ገልጿል።
ሚኒስቴሩ በተጨማሪም ሁሉም ወገኖች መረጋጋትን እንዲጠብቁና ግጭቱን ሊያባብሱ ከሚችሉ ድርጊቶች እንዲቆጠቡ ጥሪ አቅርቧል። በግጭትና በተደጋጋሚ የሰብአዊ ቀውሶች ለዓመታት ሲጎዳ የቆየው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ተጨማሪ ግጭት ቢከሰት የሰብአዊ ሁኔታውን የበለጠ እንደሚያባብስ አስጠንቅቋል።
ኖርዌይ የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋትን ለማምጣት አሁንም አስፈላጊ መሠረት እንደሆነ አስታውቃለች። ያልተፈቱ ጉዳዮች በውይይትና በድርድር መፍታት እንዳለባቸውም በመግለጽ፣ የሚመለከታቸው አካላት ለቀጣይ ድርድር ስምምነቱን እንደ መነሻ እንዲጠቀሙበት ጠይቃለች።
በተጨማሪም የዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ሕጎች እንዲከበሩ፣ ሲቪሎች ከግጭት እንዲጠበቁና የሰብአዊ እርዳታ ያለ ገደብ ለተረጂዎች እንዲደርስ ጥሪ አቅርባለች። የአገራት ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት መከበር እንዳለበት በማሳሰብ፣ የቀጠናውና ሌሎች የውጭ አካላት ተጽዕኖአቸውን ውጥረትን ለማርገብና ሰላማዊ የፖለቲካ መፍትሔ ለማምጣት እንዲጠቀሙበት አሳስባለች።
Seledadotio

2 days ago
የራያ ህልውና አደጋና የአብን አስቸኳይ የትኩረት ጥሪ
አብን በራያ ሕዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለውን መዋቅራዊ ጭቆና፣ የማንነት ክህደት እና የተደራጀ ማፈናቀል አስመልክቶ ዛሬ ጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም. መግለጫ አውጥቷል።
ንቅናቄው በራያ ሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለው መሠረታዊ የህልውና ስጋትና የጸጥታ መደፍረስ ወደ አደገኛ ምዕራፍ እየተሸጋገረ መሆኑን ገልጿል።
በመግለጫው እንደተመለከተው፣ የፌዴራል የጸጥታ ኃይሎች ከአካባቢው መውጣትን ተከትሎ ሕወሓት ሰፊ በቀል መፈጸሙ እና ከመቶ ሺህ በላይ ነዋሪዎች መፈናቀላቸው ይታወሳል።
የሰላም ስምምነቱ ከተፈረመ በኋላም እንኳ በአካባቢው ዳግም በተቀሰቀሰው ግጭት የንጹሐን ሕይወት ማለፉ እና ከፍተኛ የንብረት ውድመት መድረሱ ተገልጿል።
አብን በመግለጫው እንደገለፀው ራሱን "የትግራይ ሰላም ሠራዊት (TPF)" ብሎ የሚጠራው የታጠቀ ቡድን ወደ ቀያቸው በመመለስ ላይ በነበሩ ተፈናቃዮችና እነሱን ለመቀበል በተሰባሰቡ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ካህናት እና ወጣቶች ላይ ተኩስ በመክፈት ጉዳት አድርሷል ሲል ወንላል
ቡድኑ በራያ ሰላም አስከባሪ ኃይል ላይ ድንገተኛ ተኩስ የከፈተ ሲሆን፤ መስከረም 23 ቀን 2019 ዓ.ም. ሕፃናትና እናቶች የተሳፈሩባቸውን ከ20 በላይ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች በማገት ለከባድ መሣሪያ ጥቃት ሰለባ አድርጓል።
አካባቢውን በኃይል በመቆጣጠር ትምህርት ቤቶች በአማርኛ ቋንቋ እንዳያስተምሩ ማገዱን እና ሕዝቡን የማስፈራራት ስራ እየሰራ መሆኑ ተመላክቷል።
አብን የራያ ሕዝብ ጥያቄዎች ዘላቂ ምላሽ እስኪያገኙ ድረስ አካባቢውን ከየትኛውም የታጠቀ ኃይል ነፃ በማድረግ፣ ሕዝቡ የራሱን ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲያቋቁም፤ "የትግራይ ሰላም ሠራዊት" የሚባለው ቡድን ያለ ቅድመ ሁኔታ ከአካባቢው እንዲወጣና ተፈናቃዮች ያለምንም ስጋት ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ አሳስቧል።
የአማራ ክልል መንግሥት ክልሉ በሕዝቡ ላይ እየተፈጸመ ያለውን መዋቅራዊ በደል በዝምታ መመልከቱን አቁሞ ለሕዝቡ ሰብአዊ ደኅንነትና መብት የማያወላውል አቋም እንዲይዝ ጥሪ ቀርቧል።
አብን የራያ ሕዝብ የሕዝቡ አንድነቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል፣ ከፋፋይ ሴራዎች ራሱን እንዲጠብቅ እና ማህበረሰባዊ አደረጃጀቶቹን አጠናክሮ ከፌዴራል ጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት አካባቢውን እንዲጠብቅ ጠይቋል።
ድርጅቱ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) እና የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር (OHCHR) በአካባቢው የተፈጸሙትን ጥቃቶች እና ተፈናቃዮች እንዳይመለሱ የተደረገበትን ክልከላ በአካል በመገኘት ገለልተኛ ምርመራ እንዲያካሂዱ ጥሪ ቀርቧል።

ትግራይ በኮማንድ ፖስት ልትመራ ነው‼
ከ6 ወር በኋላም ምርጫ ይካሄዳል ተባለ‼
የሕወሓት መሪዎች ከክልሉ ከተሞች ለቅቀው መውጣታቸውን ተከትሎ ትግራይ በፌደራል መንግሥቱ ኮማንድ ፖስት ሥር እንደምትመራና ከስድስት ወራት በኋላ ምርጫ እንደሚካሄድ አቶ ጌታቸው ረዳ ገለፁ።
አቶ ጌታቸው ለቲቢኤስ እንደገለጹት፦
የኮማንድ ፖስቱ ዋና ዓላማ የሕግ የበላይነትን ማረጋገጥ፣ ደኅንነትን ማስከበርና ክልሉን መልሶ ማደራጀት ነው።
የክልሉን ፀጥታ የመከላከያ ሠራዊትና የትግራይ ሰላም ኃይሎች በጋራ የሚያስከብሩ ሲሆን፣ ሰብአዊ እርዳታም ይቀርባል።
ከምዕራብ ትግራይ የተፈናቀሉ ነዋሪዎች ወደ ቀያቸው እንደሚመለሱና ከ6 ወራት በኋላ በሚካሄደው ምርጫ የተመረጠ አስተዳደር ሥልጣን እንደሚረከብ ተናግረዋል።

#tigray
" ህወሓት ተመልሶ አይመጣም። .... የህወሓት አመራሮች ከኤርትራ ድንበር በስተደቡብ በኩል መረብ ወንዝ ዙሪያ ነው የሚገኙት " - አቶ ጌታቸው ረዳ
👉 " ወታደራዊ መልሶ ማጥቃት ለማድረግ ዝግጁ ነን ፤ የትኛውም ኃይል ከትግራይ አይወጣም " - ህወሓት
ለ6 ወራት ያህል ትግራይ በፌዴራል ኮማንድ ፖስት ስር እንደምትቆይና ከዚያ በኋላ ክልላዊ ምርጫ እንደሚካሄድ የቀድሞ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንትና የአሁኑ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ አቶ ጌታቸው ረዳ ገለፁ።
አቶ ጌታቸው ከቲቢኤስ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደተናገሩት፣ የኮማንድ ፖስቱ ዋነኛ ተግባር ክልሉን ለአስተዳደር ስራ ምቹ ማድረግ፣ ጸጥታን ማስከበር እንዲሁም መልሶ ማቋቋምና ማገገምን ማመቻቸት ነው።
እንደ አቶ ጌታቸው ማብራሪያ፣ የፌዴራል ኃይል እና አጋሮቹ እያንዳንዱን ከተማ ሲቆጣጠሩ ሰብአዊ እርዳታ የሚቀርብ ሲሆን፣ የጸጥታ ጥበቃው በኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት (ENDF) እና በትግራይ ሰላም ኃይል ይከናወናል።
በተጨማሪም ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እንደሚመለሱ አሳውቀዋል።
የፖለቲካ ፓርቲዎች ከ6 ወር በኋላ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ስር ለሚካሄደው ምርጫ ዝግጅት እንዲጀምሩ ጥሪ አቅርበዋል።
በወንጀል ድርጊት የተሳተፉት ካልሆኑ በስተቀር የህወሓት አባላት በትግራይ መልሶ ማቋቋም ስራ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ ገልጸዋል።
ከቀናት በፊት ከኤርትራ ድንበር 35 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው ዓዲግራት በኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊትና በትግራይ ሰላም ኃይል ቁጥጥር ስር ውላለች።
አቶ ጌታቸው ረዳ ጦርነቱ ማብቃቱንና ህወሓት ተመልሶ የሚመጣበት እድል እንደሌለ ገልጸው፣ ዓድዋና አክሱም በቀጣይ ቀናት (ዛሬ ወይም ነገ) በቁጥጥር ስር እንደሚገቡ / እንደሚያዙ አመልክተዋል።
የህወሓት አመራሮች ከኤርትራ ድንበር በስተደቡብ በኩል መረብ ወንዝ ዙሪያ እንደሚገኙም ተናግረዋል።
በሌላ በኩል፣ የህወሓት አመራር የሆኑት አማኑኤል አሰፋ እና የድርጅቱ ኮሙኒኬሽን በሶሻል ሚዲያ ባወጡት መግለጫ " ወታደራዊ መልሶ ማጥቃት ለማድረግ ዝግጁ ነን ፤ የትኛውም ኃይል ከትግራይ አይወጣም " ሲሉ አስታውቀዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia #mekelle📍 ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ ለሁለት ሳምንት ያህል ተቋርጦ ዛሬ መልሶ በጀመረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመጀመሪያው በረራ፦ - አቶ ጌታቸው ረዳ - አብርሃም በላይ (ዶ/ር) - አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን - የትግራይ የሰላም ኃይል አዛዥ ጀነራል ወዲ አንጥሩ - የትግራይ ሰላም ኃይል አመራር ሜጀር ጃነራል ዘውዱ ኪሮስ - ኮሎኔል ወዲ አባተ ... እንደነበሩበት ተነግሯል። የቀድሞው የትግራይ…

3 days ago
ከንግግር ባለፈ በተጨባጭ ፕሮጀክቶች የሚረጋገጥ የብልጽግና ጉዞ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ ታሪካዊ የእድገት ምዕራፍ ላይ ትገኛለች። የኢትዮጵያ የመነሳት ዘመን በቃል ደረጃ የሚገለጽ የፖለቲካ መፈክር ሳይሆን በመሬት ላይ በሚታዩ ዘላቂና ግዙፍ ፕሮጀክቶች የሚረጋገጥ ሀገራዊ እውነታ ሆኗል።
ሀገሪቱ ለዘመናት የገባችበትን የጥሬ ዕቃ ኤክስፖርት ጥገኝነት በመስበር አዲስ የኢንዱስትሪና የኢኮኖሚ መዋቅር የመገንባት ስትራቴጂ በስፋት እየተተገበረ ይገኛል። በዛሬው ዕለት የተመረቀው ብሔራዊ የውድ ማዕድናት ማጣሪያ ፋብሪካም የዚህ ታላቅ አገራዊ ርዕይ አካል ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በምረቃው ወቅት እንደገለጹት÷ በማዳበሪያ ፋብሪካ የጀመርነውን ሥራ በወርቅ ማጣሪያ ደግመነዋል፤ በሌሎችም ዘርፎች እንዲህ ዓይነት ሥራዎችን በመስራት ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት 5 እና 10 ዓመታት ጥሬ ልኮ የበሰለ መቀበልን ታቆማለ ብለዋል።
ይህ ስኬት ሀገራችን ተፈጥሮአዊ ሀብቶቿን እሴት ጨምራ ለዓለም ገበያ ለማቅረብ ያላትን ቁርጠኝነት ያሳያል።
ይህ እሴት የመጨመር ጉዞ በወርቅና በማዳበሪያ ዘርፍ ብቻ የሚገደብ ሳይሆን በሌሎች ቁልፍ የኢኮኖሚ መስኮችም ሊደገምና ሊሰፋ የሚገባው መዋቅራዊ ሽግግር ነው።
በግብርናው ዘርፍ ሀገሪቱ የምታመርታቸውን እንደ ቡና፣ ሰሊጥና የቅባት እህሎች ያሉ ጥሬ ምርቶች በሀገር ውስጥ የማቀናበር ሥራ አጠናክሮ መሥራት አስፈላጊ ነው።
በተመሳሳይ በጨርቃጨርቅና አልባሳት ዘርፍ የተፈጥሮ ጥጥን በጥሬው ከመላክ ይልቅ በሀገር ውስጥ ፋብሪካዎች ፈትሎና አልብሶ ለውጭ ገበያ ማቅረብ ይገባል።
ኢትዮጵያ ያቀደችውን የብልጽግና ጉዞ እውን ለማድረግ የተጀመሩት ሀገራዊ ፕሮጀክቶች አዎንታዊ ውጤት እያመጡ ይገኛሉ።
ጥሬ ዕቃዎችን ብቻ ከመላክ ተላቃ እሴት የተጨመረባቸውን ምርቶች ወደ ዓለም ገበያ የማቅረብ ሂደቱ ተጠናክሮ ሲቀጥል ደግሞ ኢትዮጵያ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪነቷን በማረጋገጥ የጀመረችውን የብልጽግና ግብ በጽኑ መሠረት ላይ እንድታቆም ያስችላልታል።
በዮናስ ጌትነት

በአፋር ክልል በአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ምክንያት ድጋፍ ለሚፈልጉ ወገኖች የሰብአዊ ድጋፍ እየተጓጓዘ መሆኑ ተገፁጿል።
መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) በአፋር ክልል በአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ምክንያት ድጋፍ ለሚፈልጉ ወገኖች የሰብአዊ ድጋፍ ተደራሽ እያደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።
ከአዳማ የእህል ማከማቻ ማእከላዊ መጋዘን የተጫነ አስቸኳይ ሰብአዊ ድጋፍ ወደ አፋር ክልል በመጓጓዝ ላይ መሆኑንም ነው የተገለፀው።
ለተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ክልሎች በራሳቸው አቅም ምላሽ ለመስጠት እየተረባረቡ መሆኑን ያነሳው ኮሚሽኑ የቅድሚያ ቅድሚያ በሚሰጣቸው አካባቢዎች ተጨማሪ የሰብአዊ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል ሲል ነው ያስታወቀው።
በዚሁ መሠረትም በአፋር ክልል የቅድሚያ ቅድሚያ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች የሰብአዊ ድጋፍ በማድረስ ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።
የአፋር ክልል በራሱ አቅም የሚያደርገው ድጋፍ እና ክትትል እንደተጠበቀ ሆኖ ኮሚሽኑም የቅርብ ድጋፍና ክትትል እያደረገ መሆኑንና ከአዳማ የመጠባበቂያ መጋዘን ሰብአዊ ድጋፍ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ወደ አፋር ክልል መንቀሳቀሳቸውን ጠቁሟል።
#አሐዱ_ሬዲዮ_94
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ሀገር አቀፍ የህግ ተርጓሚዎች ጉባኤ በባሕር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው
*****************
የፌዴራል እና የክልል ፍርድ ቤቶች ለፍትህ ሥርዓቱ መጠናከር በጋራ እንዲሠሩ የሚያስችል ሀገር አቀፍ የህግ ተርጓሚዎች ጉባኤ በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አዘጋጅነት በባሕር ዳር ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንትና የህግ ተርጓሚዎች ጉባኤ ሰብሳቢ አቶ ቴዎድሮስ ምህረት በመድረኩ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ጉባኤው ፍርድ ቤቶች በአደረጃጀታቸውና በሥልጣን ወሰናቸው ያደረጓቸውን እንቅስቃሴዎች በመፈተሽ ከስኬቶችና ከክፍተቶች ተሞክሮ ለመጋራት እንደሚያስችል አስታውቀዋል።
ተገልጋዮችን እርካታ የሚያረጋግጥ ተቀራራቢ የህግ አተረጓጎም እና አተገባበር እንዲኖር ትልቅ ፋይዳ እንዳለውም ገልጸዋል።
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ አለምአንተ አግደው በበኩላቸው፣ የፌዴራልና የክልል ፍርድ ቤቶች በህግ ትርጓሜ ላይ በመቀናጀት የሚሠሩት አሠራር ድምበር የለሽ የሆነውን የፍትህ አገልግሎት ለማሳለጥ የሚያግዝ መሆኑን ጠቁመዋል።
የዳኝነት አገልግሎት ዘርፍ የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ፣ ሰብአዊ መብቶችንና ነፃነቶችን ለማስከበር እንዲሁም ለንግድና ኢንቨስትመንት መሳለጥ የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።
ይህን ተልዕኮ ለማሳካት በአማራ ክልል ፍርድ ቤቶች የተጀመሩ የለውጥ ሥራዎች ተጨባጭ ውጤት እያስገኙ መሆናቸውን ገልጸው፣ ጉባኤው ለለውጥ ሥራው የላቀ ስኬት አስተዋጽኦ እንዳለው እምነታቸውን ገልጸዋል።
በጉባኤው ላይ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንትን ጨምሮ የሁሉም ክልሎች ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች እና የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶች ፕሬዚዳንቶች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።
በራሔል ፍሬው
#ethiopia #ebc #justice #የመደመርመንግሥት #courtoffice

Sponsored by
Surafel
3 days ago
የእስራኤል ኃይሎች በየቀኑ ፍልስጤማውያንን መግደላቸውንና መጉዳታቸውን ቀጥለዋል ሲሉ ከ100 በላይ የመብት ቡድኖች አስታወቁ
በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት ከተደረገ ከአንድ ዓመት በኋላ፣ ከ100 በላይ የሰብአዊ፣ የሰብአዊ መብቶች እና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እንደገለጹት፣ ይህ ስምምነት በወረቀት ላይ ብቻ የሚገኝ ነው ብለዋል።
የተኩስ አቁም ስምምነቱ በስም ብቻ ነው ያለው፣ የእስራኤል ኃይሎች በየቀኑ ፍልስጤማውያንን መግደላቸውንና መጉዳታቸውን ቀጥለዋል፣ እንዲሁም በእርዳታ፣ በመሳሪያዎችና በግንባታ ቁሳቁሶች ላይ የተጣሉ ገደቦች ቤተሰቦች እንዳያገግሙ ይከለክላሉ”ሲሉ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በጋራ ባወጡት መግለጫ ተናግረዋል።
አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ የኖርዌይ የስደተኞች ምክር ቤት፣ የሕፃናት አድን ድርጅት፣ ኦክስፋም፣ ግሪንፒስ እና ሌሎች በርካታ ዓለም አቀፍ ቡድኖች ትራምፕ በጋዛ የሰላም ቦርድ ማዕቀፍ ውስጥ ግጭቶችን ለማስቆም ስምምነት ላይ ከደረሱ በኋላ 1,400 ፍልስጤማውያን ተገድለዋል። ከነ፣ኒህ ውስጥ ቢያንስ 327 ሕፃናት ናቸው።
በኤፍራታ ሚሊዮን
#ዳጉ_ጆርናል

4 days ago
ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ካቋረጡ ከጥቂት ቀናት በኋላ፣ አንዱ አንዱን "የጥቃት ጦርነት" ጀምሮብኛል ሲሉ መወነጃጀል ጀመሩ።
-የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ፤ በመቀሌ ከተማ የሚገኙ ነዋሪዎች፣ ሰላምና ስርዓትን ወደነበረበት ለመመለስ እንዲተባበሩ ለነዋሪዎች በድምፅ ማጉያ ጥሪ ማቅረባቸዉ ተሰማ። በሌላ በኩል የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ትግራይ ክልል ፤ መቀሌ ከተማ የሚያደርገዉን በረራ ጥቅምት 1 እንደሚጀምር ተመልክቷል።
-አምነስቲ ኢንተርናሽናልና ሂውማን ራይትስ ዎችን ጨምሮ በርካታ አህጉራዊ እና ዓለማቀፍ የመብት ተሟጋች ድርጅቶች፣ በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት እየተባባሰ የመጣውን የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ለመፍታት እና ተጨማሪ ጭካኔ የተሞላባቸው ወንጀሎችን ለመከላከል አስቸኳይ ልዩ ስብሰባ እንዲጠራ ለተመድ የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤትን ጠየቁ።
-የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ ፤ኢህአፓ፤ በኢትዮጵያ በተለያዩ እስር ቤቶች የታሰሩ እና «መንግስት ያቀረበውን የይቅርታ ሰነድ አንፈርምም» ብለው የቀሩ እስረኛ፣ ጋዜጠኞች፣ የፖለቲካ ሰዎች እና የማህበረሰብ አንቂዎች ላይ «ከፍተኛ ግፍ፣ ጫና እና እንግልት» እየደረሰ ነዉ ሲል አሳሰበ።
-ደቡብ አፍሪቃዊትዋ ዳና ናቫኔተም በአጭሩ ስማቸዉ "ናቪ" ፒላይ የዘንድሮዉን የጎርጎሮሳዉያን 2026 የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸነፉ።
Via:- ዶቼቬሌ
@Yenetube Fikerassefa

ፖል ቴርጋት (Paul Tergat)፡
የኬንያው የረጅም ርቀት ሩጫ ኮከብ፣ የዓለም ሻምፒዮንና
* የሃይሌ ገብረሥላሴ ታላቅ ተቀናቃኝ ለግራንድ አፍሪካን ረን እና ለአፍሪካ ኢምፖክት አዋርድ 2026 ዝግጅት ዋሽንግተን ዲሲ ደርሷል።
#ethiopia | ፖል ቴርጋት (Paul Tergat) በዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ታሪክ ውስጥ ስሙ በታላቅ አክብሮት ከሚጠቀሱ የረጅም ርቀት ሯጮች አንዱ ነው።
አምስት ተከታታይ የዓለም ክሮስ ካንትሪ ሻምፒዮና የግል የወርቅ ሜዳሊያዎችን በማሸነፍ፣ በኦሊምፒክ ሁለት የብር ሜዳሊያዎችን በማግኘትና የማራቶን የዓለም ክብረወሰንን በመስበር በስፖርቱ ውስጥ የማይረሳ ታሪክ ጽፏል።
ከኢትዮጵያዊው ታላቅ አትሌት ሃይሌ ገብረሥላሴ ጋር የነበረው ከፍተኛ ፉክክር የዓለም አትሌቲክስን በታላላቅ የስፖርት ትዝታዎች ካደመቁ ውድድሮች መካከል ይጠቀሳል።
በተለይም በ1996ቱ የአትላንታና በ2000ው የሲድኒ ኦሊምፒክ የ10,000 ሜትር ፍጻሜዎች ሁለቱን ታላላቅ አትሌቶች በታሪክ ውስጥ የማይረሱ ተቀናቃኞች አድርገዋቸዋል።
የሕይወት ታሪኩና የሩጫ ጅማሬ
ፖል ቴርጋት ሰኔ 17 ቀን 1969 በኬንያ ካባርኔት ተወለደ። በልጅነቱ የስፖርት ፍላጎት የነበረው ሲሆን፣ ወደ ሩጫ በመግባት በቀስታ ወደ ዓለም አቀፍ ደረጃ ደረሰ። እ.ኤ.አ. በ1992 የኬንያ ብሔራዊ ክሮስ ካንትሪ ሻምፒዮናን በማሸነፍ የታላቅ የስፖርት ሕይወቱን መሠረት ጣለ።
የቴርጋት የሩጫ ችሎታ በተለይ በክሮስ ካንትሪ፣ በ5,000 ሜትር፣ በ10,000 ሜትር፣ በግማሽ ማራቶንና በማራቶን ውድድሮች ታይቷል። ይህም ከትራክ ሩጫ እስከ መንገድ ሩጫ ድረስ በተለያዩ ርቀቶች ራሱን ማረጋገጥ እንደቻለ ያሳያል።
አምስት ተከታታይ የዓለም ክሮስ ካንትሪ ሻምፒዮና ድሎች
የፖል ቴርጋት በጣም አስደናቂ ስኬቶች አንዱ ከ1995 እስከ 1999 ድረስ በየዓመቱ በዓለም ክሮስ ካንትሪ ሻምፒዮና የወንዶች ከፍተኛ የግል ውድድር የወርቅ ሜዳሊያ ማሸነፉ ነው።
ይህንን ድል ለአምስት ዓመታት በተከታታይ ማስመዝገቡ በክሮስ ካንትሪ ታሪክ ውስጥ ከሚታወሱ ታላላቅ ስኬቶች አንዱ አድርጎታል።
1995 — ዱራም፣ እንግሊዝ
1996 — ስቴለንቦሽ፣ ደቡብ አፍሪካ
1997 — ቱሪን፣ ጣሊያን
1998 — ማራካሽ፣ ሞሮኮ
1999 — ቤልፋስት፣ ሰሜን አየርላንድ
ከዚህም በተጨማሪ በእነዚህ ውድድሮች የኬንያ ቡድን የበላይነትን ለማጠናከር ትልቅ ሚና ተጫውቷል።
በተለይ የ1999ኙ የቤልፋስት ድል አምስተኛው ተከታታይ የግል ሻምፒዮና ስለነበር በስፖርት ሕይወቱ ልዩ ቦታ ይይዛል።
. ከሃይሌ ገብረሥላሴ ጋር የነበረው ታሪካዊ ፉክክር
የፖል ቴርጋትን የስፖርት ታሪክ ስናነሳ የሃይሌ ገብረሥላሴን ስም አለማንሳት አይቻልም። ሁለቱ አትሌቶች በዓለም አትሌቲክስ ውስጥ የረጅም ርቀት ሩጫን ደረጃ ያሳደጉ ተቀናቃኞች ነበሩ።
የ1996ቱ የአትላንታ ኦሊምፒክ
በአትላንታ ኦሊምፒክ የ10,000 ሜትር ፍጻሜ ሃይሌ ገብረሥላሴ የወርቅ ሜዳሊያ ሲያሸንፍ፣ ፖል ቴርጋት የብር ሜዳሊያ አገኘ። ይህ ውጤት በሁለቱ መካከል የነበረውን የውድድር ፉክክር ይበልጥ አጉልቶ አሳየ።
የ2000ው የሲድኒ ኦሊምፒክ
በሲድኒ ኦሊምፒክ የ10,000 ሜትር ፍጻሜ ሁለቱ አትሌቶች እጅግ በተቀራረበ ውድድር ተፋለሙ። ሃይሌ የወርቅ ሜዳሊያውን ሲያስጠብቅ፣ ቴርጋት በ0.9 ሰከንድ ያህል ልዩነት በሁለተኛ ደረጃ በመጨረስ የብር ሜዳሊያውን አገኘ።
ይህ ውድድር ከውጤቱ ባሻገር የሁለቱን አትሌቶች የፍጥነት፣ የጽናትና የውድድር ስልት በግልጽ ያሳየ ነበር። ሃይሌና ቴርጋት በስፖርት ሜዳ ተቀናቃኞች ቢሆኑም፣ የነበራቸው ፉክክር ለዓለም አትሌቲክስ ትልቅ እሴት አበርክቷል።
. በግማሽ ማራቶን የተመዘገቡ ታላላቅ ድሎች
ቴርጋት በትራክና በክሮስ ካንትሪ ብቻ ሳይወሰን በመንገድ ሩጫም የላቀ ብቃት አሳይቷል። በግማሽ ማራቶን ውድድር ሁለት ተከታታይ የዓለም ሻምፒዮና ድሎችን አስመዝግቧል።
1999፡ በፓሌርሞ፣ ጣሊያን የዓለም ግማሽ ማራቶን ሻምፒዮናን አሸነፈ።
2000፡ በቬራክሩዝ፣ ሜክሲኮ የሻምፒዮና ድሉን ደገመ።
እንዲሁም እ.ኤ.አ. በ2000 በሊዝበን የግማሽ ማራቶን ሩጫን በ59 ደቂቃ ከ6 ሰከንድ በማጠናቀቅ የዓለም ክብረወሰን አስመዘገበ።
እነዚህ ስኬቶች ቴርጋት በተለያዩ የሩጫ ርቀቶች ላይ ያለውን ብቃት ከማሳየታቸውም በላይ ወደ ማራቶን ውድድር ለመሸጋገር ጠንካራ መሠረት ፈጥረውለታል።
. የበርሊን ማራቶን 2003፡ የዓለም ክብረወሰን
የፖል ቴርጋት የስፖርት ሕይወት ከፍተኛ ምዕራፍ ከሆኑ ውድድሮች መካከል በ2003 የበርሊን ማራቶን ይጠቀሳል።
እ.ኤ.አ. መስከረም 28 ቀን 2003 በጀርመን ዋና ከተማ በተካሄደው ውድድር ማራቶኑን 2 ሰዓት 4 ደቂቃ ከ55 ሰከንድ በሆነ ጊዜ በማጠናቀቅ የወንዶች ማራቶን የዓለም ክብረወሰንን ሰበረ። ይህም ከ2 ሰዓትና 5 ደቂቃ በታች የተመዘገበ ታሪካዊ ውጤት ነበር።
ይህ ውጤት ቴርጋትን በዓለም ማራቶን ታሪክ ውስጥ ከታላላቅ ሯጮች መካከል አስመዘገበው። ክብረወሰኑ ለአራት ዓመታት ያህል ቆይቶ በ2007 በኬንያዊው አትሌት ሳሙኤል ዋንጂሩ ሳይሆን በኬንያዊው አትሌት ሃይሌ ገብረሥላሴ በበርሊን በ2:04:26 ተሻሽሏል።
ከዚያ በኋላም ቴርጋት በ2005 የኒውዮርክ ማራቶንን በማሸነፍ በመንገድ ሩጫ ያለውን ብቃት አረጋግጧል።
6. የአትሌቲክስ ስኬቶቹ በአጭሩ
5
ተከታታይ የዓለም ክሮስ ካንትሪ የወርቅ ሜዳሊያዎች
1995–1999
2
የኦሊምፒክ የብር ሜዳሊያዎች
1996 እና 2000
2
የዓለም ግማሽ ማራቶን ሻምፒዮና ድሎች
1999 እና 2000
2:04:55
የማራቶን የግል ምርጥ ውጤት
በርሊን፣ 2003
ከሩጫ ሜዳ ባሻገር፡ ማኅበራዊ አስተዋጽኦ
ፖል ቴርጋት ስፖርትን በማሸነፍና በሜዳሊያ ብቻ የሚለካ እንዳልሆነ በሕይወቱ በኋላ ባከናወናቸው ሥራዎችም አሳይቷል።
በ2004 የተባበሩት መንግሥታት የዓለም የምግብ ፕሮግራም (WFP) የበጎ ፈቃድ አምባሳደር ሆኖ ማገልገል ጀመረ።
በ2005 ደግሞ የፖል ቴርጋት ፋውንዴሽንን መሠረተ፤ የድርጅቱ ዓላማ በስፖርትና በትምህርት አማካይነት የተጎዱና ዕድል ያነሳቸውን ሕፃናትና ወጣቶች ሕይወት ማሻሻል ነው።
በተጨማሪም በኦሎምፒክ ስደተኞች ፋውንዴሽን ቦርድ ውስጥ ከ2021 ጀምሮ አገልግሏል። ይህ ከአትሌቲክስ ውድድር በኋላም ስፖርትን ለማኅበራዊ ለውጥና ለወጣቶች ዕድል መፍጠሪያ ለመጠቀም ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል።
የፖል ቴርጋት ውርስ ምንድን ነው?
የፖል ቴርጋት የስፖርት ሕይወት በሦስት ዋና ዋና ጉዳዮች ሊጠቃለል ይችላል።
ጽናት፡ በክሮስ ካንትሪ፣ በትራክና በመንገድ ሩጫ ለብዙ ዓመታት ከፍተኛ ደረጃውን ጠብቋል።
ተቀናቃኝነትና የስፖርት ታሪክ፡ ከሃይሌ ገብረሥላሴ ጋር ያደረገው ፉክክር ለዓለም አትሌቲክስ ታላላቅ የውድድር ትዝታዎችን ፈጥሯል።
ማኅበራዊ ኃላፊነት፡ በፋውንዴሽኑና በሰብአዊ እርዳታ ሥራዎች ለወጣቶችና ለማኅበረሰቡ የሚጠቅም አስተዋጽኦ ለማድረግ ቀጥሏል።
መደምደሚያ
ፖል ቴርጋት ከኬንያ የተነሳ ብቻ ሳይሆን በዓለም አትሌቲክስ ታሪክ ውስጥ የራሱን ልዩ ስፍራ ያረጋገጠ ታላቅ ሯጭ ነው። አምስት ተከታታይ የዓለም ክሮስ ካንትሪ ሻምፒዮና ድሎች፣ ሁለት የኦሊምፒክ የብር ሜዳሊያዎችና በ2003 የተመዘገበው የማራቶን የዓለም ክብረወሰን የስፖርት ታሪኩን የሚያስታውሱ ዋና ዋና ስኬቶች ናቸው።
ከሁሉም በላይ ግን የቴርጋት ታሪክ የሚያስተምረን ስኬት በድል ብቻ እንደማይገለጽ ነው። ጽናት፣ ተግሣጽ፣ የረጅም ጊዜ ዝግጅትና ከውድድር ሜዳ ባሻገር ለሰዎች የሚደረግ አስተዋጽኦ አንድን ሻምፒዮን በታሪክ ውስጥ የሚያኖሩ እሴቶች ናቸው።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#paultergat #hailegebrselassie #athletics #marathon #kenya #ethiopia #worldathletics #getutemesgen #ጌጡተመስገን

የዘንድሮው ሰላም ኖቤል ሽልማት ለደቡብ አፍሪቃዊቷ ዳና ናቫኔተም ተሰጠ
ደቡብ አፍሪቃዊቷ ዳና ናቫኔተም በአጭሩ ስማቸዉ "ናቪ" ፒላይ የዘንድሮዉን የጎርጎሮሳዉያኑን የ 2026 የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ የሆኑት ፤ለሰላም እና ለዓለም አቀፍ ህግ መከበር ላደረጉት ጥረት መሆኑን የኖቬል ሽልማት ኮሚቴዉ ዛሬ ኖርዌ መዲና ኦስሎ ላይ ይፋ አድርጓል።
እንደ ኖቤል ኮሚቴው ገለጻ፣ በዚህ ዓመት ለሰላም ሽልማቱ በአጠቃላይ 287 እጩዎች ቀርበዉ ነበር። ከእጩዎቹ መካከል፤ በተለይ የዩክሬን የሰብአዊ እና የህፃናት መብት ተሟጋች ማይኮላ ኩሌባ፣ የህፃናት እርዳታ ድርጅት "ሴቭ ዘ ችልድረን" እና መንግስታዊ ያልሆነው የጋዜጠኞች ጥበቃ ኮሚቴ ፤ ያሸንፉሉ ተብለዉ ከተጠበቁት መካከል ነበሩ።
ሽልማቱ በዓለም ዙሪያ የጦር መሳሪያ ለማስፈታት እና ለሰላም በሚደረግ ጥረት ላይ ለሚተጉ ሰዎች እና ቡድኖች የሚበረከት ነዉ።
የኖርዌ የሰላም ሽልማት ከጎርጎረሳዉያኑ 1901 እስከ 2025 ባለው ጊዜ ለ143 ተሸላሚዎች በድምሩ 106 ጊዜ በዘርፉ ሽልማት ተሰጥቷል።
በጎርጎሪያኑ 2019 ዓ.ም የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ.ር አብይ አህመድ የሰላም ኖቤል ሽልማት አሸናፊ መሆናቸው ይታወሳል።
DW Amharic

5 days ago
አንድን ሹፌር በሰደፍ ሲመታ እና ሲደበድብ የሚታየው የፖሊስ አባል በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።
ሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በርካቶችን ያስቆጣ አንድ ቪድዮ እየተዘዋወረ ይገኛል።
ይህ ቪድዮ ሁለት የጭነት መኪናዎች በቆሙበት ለዜጎች የሕግ ከለላና ሰላም መስጠት የነበረበት አንድ የፖሊስ አባል አንድ ግለሰብ ላይ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት እና ድብደባ ሲፈጽም የሚያሳይ ነው።
በርካታ ሰዎች የተፈጸመውን ድርጊት " ከህግ የወጣ እና ኢሰብዓዊ ፤ በየቦታው በሹፌሮች ላይ የሚፈጸመውን በደል ጭምር በገሃድ የሚያሳይ " ሲሉ ኮንነውታል።
" አልተቀረጸ እንጂ ሹፌሮች በየቦታው ይህን መሰል ተግባር ነው የሚገጽማቸው " ሲሉም ገልጸዋል።
ድርጊቱ መቼ እና የት ተፈጸመ ?
ብዙሃንን ያስቆጣው ድርጊት የተፈጸመው በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በጋሞ ዞን፣ ቦረዳ ወረዳ " ጠንጠሌ " ተብሎ በሚጠራ አከባቢ ነው።
ቲክቫህ ኢትዮጵያም ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ በጋሞ ዞን የቦረዳ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ም/ኢንስፔክተር አብረሃም አየለን አነጋግሯቸዋል።
አዛዡ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ድርጊቱ የተፈፀመው መስከረም 23 ቀን 2019 ዓ/ም ከሰዓት በኋላ ነው።
" በወረዳው ጠንጠሌ አከባቢ ' ዮ ሆልዲንግ ' ከተሰኘ የድንጋይ ከሰል አቅራቢ ድርጅት ሳይት ከሰል ጭነው በመውጣት ላይ የነበሩ የዳንጎቴ የጭነት መኪና አሽከርካሪዎች በአከባቢው ከነበሩ የፖሊስ አባላት ጋር ያለመግባባት ተፈጥሮ ነበር " ብለዋል።
" የፖሊስ አባሉ ፍጹም ተገቢ ባልሆነ መንገድ አሽከርካሪውን ሲመታው የሚያሳይ ምስል በዚያው ቅፅበት በማህበራዊ ሚዲያ ተሰራጭቶ መረጃው በስልክ ነው የደረሰኝ " ሲሉ ገልጸዋል።
" መረጃው እንደደረሰን በዕለቱ ድርጊቱ በተፈፀመ 30 ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ ነው አባሉን በቁጥጥር ስር ያዋልነው " ያሉት አዛዡ " በአሁኑ ወቅት ምርመራ ተጀምሯል የፍርድ ቤት የጊዜ ቀጠሮ እየተጠበቀ ነው " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
" ድርጊቱ በየትኛውም አይነት መመዘኛ ትክክል አይደለም " ያሉ ሲሆን " የተፈጸመው ድርጊት ግለሰቡን እንጂ የወረዳውን ፣ የዞኑንና የክልሉን ፖሊስ የማይወክል ሆኖ ሳለ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የሚሳራጩት አንዳንድ ማብራሪያና ፍረጃዎች ተገቢነት የላቸውም " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ከዳንጎቴ ተቋም በኩል መረጃ ለማግኘት ሙከራ አድርጎ አልተሳካም።
አንድ በተቋሙ ለዞኑ የተፃፈ ደብዳቤን ግን ተመልክቷል።
" ይህ የአሁኑን ጨምሮ በሌሎችም ጊዜያት የተለያዩ ክፍያዎችን እየከፈሉ ቢሆንም የድርጅቱን አሽከርካሪዎች እና መኪኖች ላይ ያለአግባብ የማንገላታት ሁኔታዎች አሉ " ይላል።
ድርጅቱ " ለልማት ማህበር፣ ለፋይናንስ ቢሮ፣ ለከተማ ልማት እንዲሁም ያለደረሰኝ 'የተራ እና ሽራ አሰራ' በሚል በድምሩ እስከ 27,100 ብር ህጋዊና ህገ-ወጥ ክፍያዎችን እየከፈለ " መሆኑን ጠቁሟል።
በተጨማሪም "ፓርኪንግ" በሚል ያልቆሙበትን ክፍያ ለመጠየቅ ሲባል ወጣቶች በመደራጀት ሾፌሮቹን ከ3 እስከ 4 ቀናት በማስቆም ከፍተኛ እንግልት እንደሚያደርሱባቸው ገልጿል።
" በመንገድ ላይ የተመደቡ ፖሊሶች ያለአግባብ ከሾፌሮች ከ200 እስከ 500 ብር ይጠይቃሉ " የሚለው የድርጅቱ ደብዳቤ " ክፍያውን ያልፈጸሙ አሽከርካሪዎችን በማንገላታትና በመደብደብ ጉዳት መድረሱን " አመልክቷል።
አንድ አሽከርካሪ በደረሰበት ከፍተኛ ድብደባ ምክንያት ደብዳቤ እንደተፃፈለትም ጠቅሷል።
እነዚህ አሰራሮች በአስቸኳይ እንዲቆሙ፣ የህግ የበላይነት እንዲከበር፣ አሽከርካሪዎች ያለስጋት ስራቸውን እንዲያከናውኑ እና ስልጣናቸውን ያለአግባብ በመጠቀም ህገ-ወጥ ድርጊት የፈጸሙ አካላት በህግ እንዲጠየቁ ጠይቋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ/ም

ወንድሜ ሞተብኝ
የእናቴ ልጅ ገና በወጣትነቱ ሞተብኝ
ወንድሜ ብርሃንዬ ምንም ሳይሆን ማታ ላይ ፀሎት ወደሚያደርግበት ክፍል ለፀሎት ገብቶ በዛው ሞተብን 🥹💔
በልጅነቱ ከተወለደ ጀምሮ ለደብረሊባኖስ ገዳም ተሰቶ በዛው ተምሮ ተምሮ በዛው አድጎ በዛው ሞተብኝ
ያለፉት 9 ቀኖች ለቤተሰባችን በጣም ከባድ ሀዘን ነበር .. እንደአይን ብሌናችን የምንሳሳለት ወንድማችን , ለሰው እንኳን ወንድማችን ነው ብለን ለማውራት የምንፈራለት የምንሳሳለት ወንድማችን አጣነው....
የደብረሊባኖስ ገዳም እና የእኛ ቤተሰብ ታሪክ የሚጀምረው እንደዚህ ነው ... አያቴ እናቴን በወለደች በ 20 ቀኗ ባለቤቷ ድንገት ሲሞትባት እናቴ ሶስት ወር ሲሆናት ለአያቷ ሰታት እሷ በ 17 አመቷ ወደ ደብረሊባኖስ ገዳም ሂዳ ምንና መንኩሳ ከ 60 አመት በላይ በቆብ ( በምንኩስና) ገዳሙን በፈታይነት እንዲሁም ሌሎች በገዳሙ ሴቶች ሊሰሩት የሚችሉትን እየሰራች እና ገዳሙን እያገለገለች ኑራ ነበር ... አባቴ ደሞ በደርግ ጊዜ በስራ ምክንያት የተለዩ ክፍለሀገራት ይሄድ ነበር እናቴንም ልጆቹንም ይዞ ነው ስሄድ እና እየሰራ ሲኖር የነበረው የኔ ታላላቆች የተለያየ ቦታ ነው የተወለዱት ይህ ወንድሜ በሰሜን ሸዋ ፍቼ ነው የተወለደው ከዛ በኃላ አባቴ ከልጆቹ አንድ ሰው ቤቤተክርስትያን እንዲያድግ ምኞቱ ስለነበረ ሁላችን ወደ ደብረሊባኖስ ገዳም አያቴ ጋር እየሄድን እና እየተቀመጥን ፊደል ቆጥረናል እኔም በዜማ መምህር በነበሩት በየንታ መርአዊ ወንበር ስር ተቀምጬ እስከ መዝሙረ ዳዊት ድረስ በግዕዝ ተምሬጨርሼ ነው ከዛ ወደዘመናዊ ትምህርት የገባሁት ...ወንድሜ ብርሃኑ ግን ከ አራት አመቱ ጀምሮ በገዳም ሊማር እንድሄደ በዛው እየቀጠለ እየቀጠለ እድሜውን ሙሉ ተምሯል , ከዚህ በታች ያለውን ስርአተ ፍትሀቱ ላይ አባቶች ካነበቡለት ከመሰከሩለት ከህይወት ታሪኩ ላይ ነው የወሰድኩትኝ ...
እድሜያቸው ለትምህርት በደረሰ ጊዜ ወደዚህ ታላቁ ደብረ ሊባኖስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አንድነት ገዳም መጥተው በመጀመሪያ ደረጃ የንባብ ትምህርታቸውን
ከመምህር አባ ኢያሱ አሰፋ ጉባኤ ቤት በመግባት በልዩ ኹኔታ መዝሙረ ዳዊቱን በቃል ጭምር አጠናቀው ተምረዋል፡፡
በመቀጠልም በዚሁ ገዳም ውስጥ ስመጥርና አንጋፋ ከኾኑት ከአለቃ መርዓዊ ሣህለ ሚካኤል ጉባኤ ቤት በመግባት ከውዳሴ ማርያም ዜማ ጀምረው ጾመ ድጓ እና ድጓ አጠናቀው
በሚገባ ተምረዋል፡፡ ከዚህም በኋላ ከታላቁ ሊቅ የተክሌ አቋቋም መምህር ከኾኑት ከየኔታ በትረ ማርያም ገ/መድኅን የተክሌ አቋቋምን በመምህርነት ደረጃ በሚገባ አጠናቀው ተምረዋል፤ የቅኔ ሰዋስው ትምህርትንም ከመምህራን ቀጽለዋል፡፡
ክቡር አጋፋሪ ብርሃኑ እነዚህን ሁሉ ትምህርቶች ተምረው ለዚህ ሁሉ ሊቅነት ምሁርነትና ተጠያቂነት ያበቃቸው የእናታቸው የወይዘሮ ፍሬሕይወት ታፈሰ በጎ ምኞት ቅን አመለካከትና
የከፈሉት ታላቅ የእናት መሥዋዕትነት የአያታቸው የእማሆይ ብዙነሽ ታሃለው ጥብቅ ክትትል፣ ጥረትና ጸሎት ሲኾን ክቡር አጋፋሪ ብርሃኑ የዜማ ትምህርታቸውን ተምረው ገብተው
በልጅነት ጎናቸው አርፋለሁ ሲሉ አያታቸው እማሆይ ብዙነሽ የመጣኸው ለትምህርት እንጅ ለመኝታ መች መጣህ? እያሉ ከገድል ቤቱ በንባብ ከቅኔ ማሕሌቱ አገልግሎት እንዳይለዩ
አድርገው ተከታትለው ስላስተማሯቸው ነው፡፡
በዚህ መልኩ በመንፈሳዊ አገልግሎት በክርስትና ሕይወት አምረውና አሸብርቀው ከአደጉ በኋላ በተለያዩ የሥራ ቦታዎች ላይ ተመድበው አገልግለዋል፡፡
ከሁለት ሺሕ እስከ ሁለት ሺሕ ዐሥር ዓመተ ምሕረት በቅኔ ማሕሌቱ በኩል በአጋፋሪነት ማዕርግ ተመድበው የቦታውን ይትበሃል ከታላላቆች የቦታው ሊቃውንት ከአለቃ መርዓዊ
ሣህለ ሚካኤል እና ከየኔታ በትረ ማርያም ገ/መድኅን በማጥናት ብሎም በእጃቸው ጭምር በመጻፍ ለቦታው የይትበሃሉ ተጠያቂ የሥርዐተ ማሕሌቱ መሪ በመኾን
ሥርዐቱን በመጠበቅና በማስጠበቅ ከሊቃውንቱ ጋር በመከባበርና በመፈቃቀር ረጅሙን ዓመት በሚገባ
· አገልግለዋል፡፡
ክቡር አጋፋሪ ብርሃኑ ከዐሥር ዓመት የአጋፋሪነት ማዕርግ አገልግሎት በኋላ በሌሎች ልዩ ልዩ ሥራዎች ላይ እያገለገሉ በቅኔ ማሕሌቱ በኩልም የማሕሌቱ ኮከብ የሊቃውንቱ ጌጥ
የዝማሜው ውበት ነበሩ ከዚህ የተነሳ ሊቃውንቱም አጋፋሪ ይዝመመው አጋፋሪ ይወርበው፣አጋፋሪ ያንብበው ይሏቸዋል፣ እርሳቸውም ቢቃኙ፤ቢዘሙ፤ቢወርቡ ቢያነብቡ የማይሰለቹ
አንደበተ ርቱዕ አንደበተ ቀልጣፋ ድንቅ፣ ታላቅ፣ ሊቅና ምሁር ነበሩ፡፡
ከሁሉ የበለጠ ጸጋና ስጦታም አላቸው ለተራበ የሚያበሉ ለተጠማ የሚያጠጡ ለታረዘ የሚያለብሱ ካዘነው ጋር አዝነው የሚያረጋጉ ከተደሰተውም ጋር የሚደሰቱ ርኅሩኅ ታማኝ ሰው ወዳጅ ወንድም ነበሩ፡፡ " ....
ወንድሜ ገና ልጅ ነው እድሜው ከ 39 ወደአርባ እየሄደ ነበር ከደብረ ሊባኖስ ገዳም ወቶ እዚህ አዲስ አበባ የተለያዩ አድባራት እንዲሁ በአሜሪካ ያሉ አድባራት ላይ እንዲያገለግል የተለያዩ እድሎች መተውለት ቢጠየቅም በተደጋጋሚ አልፈልግም ገዳሙን ትቼ አልወጣም በማለት ኑሯል እኛ ፕሮግራም እንኳን ኑሮን አዲስ አበባ ከመጣ አንድ ቀን ብቻ አድሮ ነው የሚሄደው ከገዳሙ መለየት በፍፁም አይፈልግም ነበር .. ወንድሜ በድንግልና የኖረ መናኝ ነበር በሚቀጥሉት አመታቶች ላይ መንኩሶ ዻዻስ የሚሆን እና እረጅም አመት ኑሮ እኛን እህት እና ወንድሞቹን ሁሉ ቀብራችንን አሳምሮ ከዛ በኃላ ይሞታል ብዬ የማስበው ወንድሜ ሰስቼው ለሰው የማላወራው ወንድሜ አንደተለመደው የቀን ውሎውን በሰላም ውሎ ሁሌ ከመተኛቱ በፊት እንደሚያደርገው ሊፀልይ ወደ ፀሎት ክፍሉ እንደገባ ሞተብኝ 💔 ሳላስታምመው ምንህን ነው ወንድሜ ሳልለው በቃ እንዲሁ ቀረብኝ 🥹💔
በጣም እረጅሙ ቆንጆው ባለግርማ ሞገሱ የእግዚአብሔር አገልጋይ የእግዚአብሔር ባሪያ .. ያ እኔ እንዲሆንልኝ እንዲሳካልኝ የሚፀልይልኝ ወንድሜን ጨክኜ ቀብርኩት

6 days ago
ጃፓን ለየመን እና ለጅቡቲ የ10 ሚሊዮን ዶላር የድንገተኛ ጊዜ እርዳታ ለመስጠት ወሰነች
የጦርነቱ ተፅዕኖ ወደ ጎረቤት ሀገራት መዛመቱን እና በየመን እየከፋ የመጣውን የሰብአዊ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት ጃፓን ለየመን እና ለጅቡቲ የ10 ሚሊዮን ዶላር የድንገተኛ ጊዜ እርዳታ እንደምትሰጥ አስታውቃለች።
የጃፓን መንግስት እርዳታውን ማክሰኞ ዕለት ማጽደቁን የሀገሪቱ ኤምባሲ ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ገልጿል።እርዳታው የባብ አል-መንደብ ወሽመጥ ዙሪያን ጨምሮ በመካከለኛው ምስራቅ ሰላምና መረጋጋትን ለመደገፍ አልሞ የተዘጋጀ መሆኑም ተነግሯል።
የጃፓን መንግስት ይህ የባህር ወሽመጥ በኢነርጂ ደህንነት ረገድ ለጃፓንም ሆነ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ “እጅግ ከፍተኛ አስፈላጊነት” ያለው መሆኑን ገልጿል።
በዚህም መሰረት የመን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዓለም የምግብ ፕሮግራም ፣ በዓለም አቀፉ የሬድ ክሮስ ኮሚቴ እና በዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት በኩል 8 ሚሊዮን ዶላር የምታገኝ ሲሆን፣ ጅቡቲ ደግሞ በተመድ የስደተኞች ኤጀንሲ በኩል 2 ሚሊዮን ዶላር ይደርሳታል ተብሏል ።
በሚኪያስ ጸሐዬ

በፌስቡክ አስተያየት ምክንያት በሳውዲ አረቢያ የሞት ፍርድ የተፈረደበት የፍልሰተኛ ሰራተኛ ጉዳይ
በሳውዲ አረቢያ የሚሰራ የ24 አመት የሲሪላንካ ዜጋ የሆነው አኖጃን ሲቫራሳ፣ በፌስቡክ በጻፈው አስተያየት የእስልምና ሃይማኖትን እና ነቢዩ ሙሐመድን ሰድቧል በሚል የሞት ፍርድ ተፈረደበት።
ድርጊቱ የተከሰተው በሲሪላንካ በነበረ የሃይማኖት ክርክር ወቅት ሲሆን፣ አኖጃን በኋላ ላይ ጽሁፉን አጥፍቶ ይቅርታ ቢጠይቅም፣ መልእክቱ ተቀርጾ ለአሰሪው እና ለሳውዲ ባለስልጣናት በመላኩ በቁጥጥር ስር ውሏል።
መጀመሪያ ላይ የአምስት አመት እስራት እና የገንዘብ መቀጮ ተበይኖበት የነበረ ቢሆንም፣ አቃቤ ህግ ጉዳዩ በሸሪአ ህግ እንዲታይ ባቀረበው ይግባኝ ፍርዱ ወደ ሞት ተቀይሯል።
ይህ ውሳኔ በሲሪላንካ ከፍተኛ ቁጣን ያስነሳ ሲሆን፣ የእስልምና፣ የቡድሂስት እና የሂንዱ ሃይማኖት መሪዎች እና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ድርጊቱን ኮንነዋል።
የሲሪላንካ መንግስት ለዜጋው ምህረት ለማስገኘት ዲፕሎማሲያዊ ጥረት እያደረገ ይገኛል።
በአሁኑ ወቅት የቤተሰብ ግንኙነቱ ሙሉ በሙሉ የተቋረጠ ሲሆን፣ የሳውዲ ባለስልጣናት ፍርዱ የሚፈጸምበትን ጊዜ አላወቁም።

ዜጎች በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ጉዳት እንዳይደርስባቸው የአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ
መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) በካቶሊክ ሪሊፍ ሰርቪስ መሪነት በሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ የሰብአዊ ድጋፍ ላይ የተሰማሩ ድርጅቶች ጥምረት እ.ኤ.አ ከ2022 አንስቶ የሰላም እጦትና የተፈጥሮ አደጋ በነበረባቸው አካባቢዎች ሲተገበር የቆየው የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ ማብቃቱን አስታወቀ።
ጥምረቱ ከ40 ዓመታት በላይ በኢትዮጵያ የሰብአዊ ድጋፍ ስራዎች ላይ ተሰማርቶ የቆየ ሲሆን ባለፉት አራት አመታት ሲተገብር የቆየው “ጂኦፕ 2” የተሰኘው ፕሮጀክት ተጠናቆ አዲስ ፕሮጀክት ይፋ አድርጓል።
በካቶሊክ ሪሊፍ ሰርቪስ የኢትዮጵያ ተወካይ አቶ ዘመዴ ዘውዴ ለአሐዱ ሬዲዮ እንደተናገሩት በተጠናቀቀው ፕሮጀክት የተወሰዱ ትምህርቶች በቀጣይ ለሚተገበረው ፕሮጀክት ግብዓት ይሆናል።
ካለፈው አንድ አመት ወዲህ የውጭ ድጋፎች መቀነስ እንዲሁም የሀብትና የተረጂዎች ቁጥር አለመመጣጠን ትልቅ ፈተና እንደነበር ገልፀው ሆኖም ግን ሁሉንም የእርዳታና መልሶ ማቋቋም ስራዎች ሰርተናል ብለዋል።
በቀጣይ ተፈናቃዮችን እና በገጠር የሚገኙ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች በልዩ ሁኔታ የመደገፍ ስራ እንደሚሰራ ገልጸዋል።
በአየር ሁኔታ ለውጥ ምክንያት የሰብል ምርት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ እና ጉዳት በሚያጋጥምበት ወቅት ዜጎችን ለማገዝ ዝግጁ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
በቀጣይ የሚሰሩ የእርዳታ ስራዎች ከመንግስት አካላት ጋር በመተባበር ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው አካላት ብቻ ለማድረስ እየተሰራ መሆኑን አክለው ገልጸዋል።
በመሰረት ሙሉ
#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3

ጥራትን ማዕከል ያደረገው የመደመር መንግሥት
አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የሀገርን ብሩህ መጻኢ ዕድል በጽኑ መሠረት ላይ ገንብቶ ዘላቂ ብልጽግናን ማረጋገጥ የሚቻለው ሕዝብን ማዕከል ያደረገ ልማት ሲረጋገጥ ነው።
የመደመር መንግሥትም በተለያዩ ዘርፎች ሕዝብን ማዕከል ያደረጉ ሁለንተናዊ መዋቅራዊ ሽግግሮችን ሲያከናውን ቆይቷል።
ይህ መዋቅራዊ ሽግግር በተለይም በትምህርት፣ በጤና እና በማህበራዊ ዘርፎች ላይ ያጠነጠነ፤ ዜጋን የልማቱ ዋና ተጠቃሚና ባለቤት ያደረገ የፖሊሲ እና የተግባር ርምጃን የወሰደ አካሄድ ነው።
ለአብነትም የትምህርት ሀገርን ተረካቢ ትውልድ የሚቀረጽበት ዋና ማዕከል እንደመሆኑ መጠን፣ በመደመር መንግሥት ትልቅ የመዋቅር ለውጥ ከተደረገባቸው ዘርፎች አንዱ ነው።
ቀደም ሲል የነበረውን የትምህርት ቤቶችን ቁጥር የማብዛት ብቻ ትኩረት ወደ ትምህርት ጥራት፣ የምዘና ሥርዓት ጥብቅነት ብሎም የትምህርት ፍኖተ- ካርታን እስከ ማሻሻል የተጓዘ ስር ነቀል አቋምን ተከትሏል።
የሀገር አቀፍ እንዲሁም ክልላዊ ፈተናዎች ከስርቆትና ማጭበርበር እንዲጸዱ መደረጉ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ቁልፍ ርምጃ ሆኗል።
የቅድመ-መደበኛ፤ ሀገር በቀል እውቀቶች፤ የዜግነትና ግብረ-ገብ ትምህርት መስፋፋት እንዲሁም የዲጂታል እና የቴክኖሎጂ ስልጠናዎች ትግበራ ትውልዱን ለዘመኑ ዝግጁ የሚያደርጉ ውሳኔዎች ናቸው።
የተማሪዎች ምገባ መርሐ-ግብር ተማሪዎች በትምህርታቸው ላይ ብቻ እንዲያተኩሩና የማቋረጥ ምጣኔም እንዲቀንስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል።
እነዚህ ታሪካዊ ርምጃዎች ትምህርትን በቁጥር ብቻ ሳይሆን በጥራትና በትውልድ ግንባታ ሚዛን ለመለካት የተደረጉ ታላቅ ውሳኔዎች ናቸው።
ጤናማ ዜጋ ለሀገር እድገትና ምርታማነት መሠረት እንደመሆኑ መጠን፤ በተመሳሳይ በጤናው ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራት መሠረታዊ የጤና አገልግሎትን ሽፋንን ከማስፋት ባለፈ ጥራቱን ለማሳደግ ያለመ መዋቅራዊ ለውጥ ተካሂዶበታል።
የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ተዳራሽነትን በማስፋት የዜጎችን የሕክምና ወጪ ጫና መቀነስ ከመቻሉም ባሻገር የላቀ የሕክምና ማዕከላት ግንባታ፣ የሆስፒታሎች ደረጃ ማሻሻያ እና የእናቶችና ሕፃናት ጤና ጥበቃን የማጠንከር ሥራዎች በስፋት ተከናውነዋል።
የመድኃኒት አቅርቦት ሥርዓትን ማዘመን እና በቴክኖሎጂ የተደገፈ የሕክምና መረጃ አያያዝን በመዘርጋት፤ ዜጎች ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት በቅርበት እንዲያገኙ ተችሏል።
የኢኮኖሚ እድገት ትርጉም የሚኖረው በኢኮኖሚያዊ አቅም ውስንነት ተጋላጭ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ሲደግፍ ነው።
በዜጋ ተኮር ማህበራዊ ዘርፉ የተከናወኑ ሥራዎች ክብርና ሰብአዊነትን ማዕከል ያደረጉ ናቸው።
የከተሞች የሴፍቲኔት ፕሮግራሞች፣የሴቶች፤ የአረጋውያንና የአካል ጉዳተኞችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ የሚያረጋግጡ አሰራሮችን ዘርግተዋል።
በበጎ ፈቃድ አገልግሎት የመኖሪያ ቤቶች እድሳት፣ የምገባ ማዕከላት መመስረትና የዜጎችን ኑሮ የማሻሻል ዘመቻዎች ማህበራዊ ፍትሕንና አንድነትን በማጠናከር ረገድ ጉልህ ስኬትን አስመዝግበዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 7ኛ የስራ ዘመን 1ኛ ዓመት የጋራ መደበኛ ስብሰባ መክፈቻ ላይ እዳሉት÷ "ጥራትን መሰረት ያደረገ ሁለንተናዊ መዋቅራዊ ሽግግር እንዲኖር ይደረጋል፤ ትምህርት፣ ጤና እና ማህበራዊ ጥበቃን ከስፋት ወደ ጥራት በማሸጋገር ዜጋን ማዕከሉ ያደረገ ልማት ይፋጠናል፡፡"
ይህ የሚያሳየው፤ የመደመር መንግሥት የተከተለው ብሎም በቀጣይ የሚከተለው የልማት አቅጣጫ፤ ቁጥርና ስፋትን መሠረት ያደረገውን የተለምዶ አካሄድ ወደ ጥራት፣ ውጤታማነት እና የዜጎችን ሕይወት ማሻሻልን የትኩረት ማዕከሉ ወደ አደረገው እይታ ያሻገረ ነው።
ትምህርትን፣ ጤናን እና አጠቃላይ ማህበራዊ ዘርፉን በጥራት ማደራጀትና ማጠናከር ሰብዓዊ ልማትን ተጨባጭ ከማድረጉም በላይ የሀገር የመበልጸግ ርዕይን እውን ለማድረግ መዋቅራዊ መሠረት ጥሏል።
#የመደመር_መንግሥት
በመልካም ፈቃዱ

7 days ago
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት በሱዳን ሰላማዊ ሰዎች ላይ እየተፈፀሙ ያሉ ጥቃቶችን አወገዘ
ምክር ቤቱ በሱዳን ሰላማዊ ሰዎች ላይ እየተፈጸሙ ያሉ የድሮን እና ሌሎች ጥቃቶችን በማውገዝ በሀገሪቱ ላለው ቀውስ “ምንም ዓይነት ወታደራዊ መፍትሄ እንደሌለ” አስጠንቅቋል።
መግለጫው የወጣው የዓለም የምግብ ፕሮግራም በሰሜን ኮርዶፋን የምግብ አቅርቦት ጭኖ በነበረ የጭነት መኪና ላይ በተፈጸመ የአየር ጥቃት የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን ባስታወቀበት ወቅት ነው።
በጄኔቫ በተካሄደው ስብሰባ 47 አባላት ያሉት ምክር ቤቱ ለሱዳን ያዋቀረውን ገለልተኛ ዓለም አቀፍ የእውነታ አጣሪ ተልዕኮ የስራ ጊዜ ለማራዘም የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ በ28 የድጋፍ እና በ10 የተቃውሞ ድምጽ አጽድቋል።
ሱዳን ምክር ቤቱ ያቀረበችውን ቅሬታ ከግምት ውስጥ ማስገባት አለመቻሉን በመግለጽ አባል ሀገራቱ ይህን እርምጃ ውድቅ እንዲያደርጉት አሳስባለች።እ.ኤ.አ በሚያዝያ 2023 በሱዳን ጦር እና በከፊል-ወታደራዊው የፈጥኖ ደራሽ ኃይል መካከል የተጀመረው ጦርነት የአስር ሺዎችን ህይወት የቀጠፈ ሲሆን ከ13 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ደግሞ አፈናቅሏል።
የተመድ መረጃዎች እንደሚያሳዩት በዚህ ዓመት የመጀመሪያዎቹ አምስት ወራት ውስጥ ብቻ በድሮን ጥቃቶች ከ1,100 በላይ ሰዎች ተገድለዋል።

የእንግሊዝ ኤንባሲ የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ውጥረቱ አሳሳቢ ነው አለ
#fastmereja I የብሪታንያ (የዩናይትድ ኪንግደም) ኤንባሲ በአዲስ አበባ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን አስታወቀ። ኤንባሲው በሰጠው መግለጫ፣ ሁሉም ኢትዮጵያውያን አካታች እና ሰላማዊ የወደፊት ዕጣ ፈንታ እንዲኖራቸው የአፍሪካ ህብረት በሚመራው የሽምግልና ጥረት ለሚደረገው ሁሉ ድጋፍ ለማድረግ ዩናይትድ ኪንግደም ዝግጁ መሆኗን አረጋግጧል።
በመግለጫው የሰላማዊ ሰዎችን ደህንነት ማስጠበቅ ያለውን ትልቅ ፋይዳ እንደገና አፅንኦት ሰጥቶ የገለጸው ኤንባሲው፤ በተጎዱ አካባቢዎች መሰረታዊ አገልግሎቶች እንዲመለሱ እና ህይወት አድን ዕርዳታ ለተቸገሩት እንዲደርስ ጥሪ አቅርቧል። በተጨማሪም ሁሉም አካላት ደህንነቱ የተጠበቀና ያልተገደበ የሰብአዊ ድርጅቶች እንቅስቃሴ እንዲፈቅዱ እንዲሁም የሰብአዊ እርዳታ ሰራተኞችን እንዲያከብሩና እንዲጠብቁ አሳስቧል።
በሌላ በኩል፣ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ባለፉት ጊዜያት እየተባባሰ በመጣው ውጥረት የተሰማውን ጥልቅ ስጋት የገለጸው የብሪታንያ ኤንባሲ፤ በክፍለ አህጉሩ የሚገኙ ሀገራት ሁሉ የጎረቤቶቻቸውን ብሔራዊ ሉዓላዊነትና ግዛት አንድነት እንዲያከብሩ ጥሪ አቅርቧል።
ኤንባሲው አያይዞም ግጭቶችን ለማቀዝቀዝ፣ በንግግር ለመፍታት እንዲሁም ልዩነቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ሁሉም ተሳታፊ አካላት አስፈላጊውን ጥረት እንዲያደርጉ አበክሮ አሳስቧል።

በትግራይ ክልል በሚገኝ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) መጋዝን ላይ ከትላንት በስቲያ እሁድ ዘረፋ መፈጸሙን የድርጅቱ ዋና ጸሀፊ ምክትል ቃል አቃባይ ገለጹ።
በክልሉ ያሉ መንግስታዊ ያልሆኑ የዓለም አቀፍ እና ሀገር በቀል ድርጅቶች መጋዘኖች እና መገልገያዎች በተመሳሳይ መልኩ መዘረፋቸውንም ቃል አቃባዩ ተናግረዋል።
የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ምክትል ቃል አቃባይ ፋራህን ሃቅ ይህንን የተናገሩት፤ ትላንት ሰኞ መስከረም 25፤ 2019 ምሽት በሰጡት ዕለታዊ ጋዜጣዊ መግለጫ ነው።
የእሁዱ ዘረፋ በትግራይ ክልል የትኛው አካባቢ እንደተፈጸመ እና በጋዜጣዊ መግለጫቸው ያልጠቀሱት ምክትል ቃል አቃባይ ፋራህን፤ ሆኖም በክስተቱ የሰብአዊ አቅርቦቶች መጥፋታቸውን አስረድተዋል።
በዘረፋው ከተሰረቁት ውስጥ ምግብ፣ ምርጥ ዘር፣ የአፈር ማዳበሪያዎች እና የውሃ ፖምፖች እንደሚገኙበት የተመድ ዋና ጸሀፊ ምክትል ቃል አቃባይ ገልጸዋል።
የሰብአዊ እርዳታ ሰራተኞች፣ ተቋማት እና ንብረቶች “በፍጹም የጥቃት ኢላማ ሊሆኑ አይገባም” ያሉት ፋራሃን፤ በሁሉም ጊዜያት “ጥበቃ ሊደረግላቸው እንደሚገባ” ጨምረው አሳስበዋል።
Via Ethiopia Insider
@YeneTube FikerAssefa

8 days ago
የልዕልት ሊሲ (ልሳን ተፈሪ ፍቅረ ሥላሴ) ግለ-ታሪክ
ልዕልት ሊሲ—በይፋዊ መጠሪያዋ ልዕልት ልሳን ተፈሪ ፍቅረ ሥላሴ (Princess Lissan "Lissie" Selassie)—የኢትዮጵያን የብዙ ክፍለ ዘመናት ንጉሣዊ ታሪክ፣ የትውልድ መስመር እና ባህላዊ ቅርስ አጣጥማ የያዘች የዘመናችን ወጣት ንጉሣዊ ተወላጅ ናት።
በካሊፎርኒያ አሜሪካ አድጋ በባዮሎጂ ሳይንስ ዘርፍ የመጀመሪያ ዲግሪዋን ያጠናቀቀችው ልዕልት ሊሲ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ኢትዮጵያን ባስተዋወቀችባቸው መድረኮች፣ በሳይንሳዊ ዕውቀቷ እና በማህበረሰብ በጎ አድራጎት እንቅስቃሴዎቿ የምትታወቅ ወጣት አርአያ ናት።
ታሪካዊ የትውልድ ሐረግ እና የአራት ሥርወ-መንግሥታት ትስስር
የልዕልት ሊሲ የደም መስመር የኢትዮጵያን ህብረ-ብሔራዊ ታሪክ እና ብዝሃነት የሚያንፀባርቅ ሲሆን፣ ከአራት ታላላቅ የኢትዮጵያ ንጉሣውያን እና መሪዎች ሥርወ-መንግሥታት የተገኘ ልዩ የትውልድ ሐረግ አላት፦
👉የሸዋ ሰለሞናዊ ሥርወ-መንግሥት፦ የቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ፣ የአልጋ ወራሽ አምኃ ሥላሴ (አስፋው ወሰን) እና የቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ የበኩር የልጅ ልጅ የነበሩት የልዕልት እጅጋየሁ አስፋው ወሰን የዘር ሃገረግ ትስስር ናት።
👉የወለጋ - ኦሮሞ ሥርወ-መንግሥት፦ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ደጃዝማች ገብረእግዚአብሔር ተብለው ከተጠመቁት ከወለጋው ንጉሥ ኩምሳ ሞረዳ እና በኦሮሞ ማህበረሰብ ውስጥ የመሪነት ውርስ ከነበራቸው ከአያቷ ከንጉሥ ፍቅሬ ሥላሴ የሚመዘዝ የትውልድ መስመር አላት።
👉የትግራይ ሥርወ-መንግሥት፦ የትግራዩ ንጉሥ እና የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት አፄ ዮሐንስ 4 ኛ እንዲሁም የልጅ ልጃቸው የልዕልት ወለተ እስራኤል ስዩም የትውልድ ዘር ናት።
👉የወሎ ሥርወ-መንግሥት፦ የወሎው ንጉሥ ሚካኤል አሊ (መሐመድ አሊ) እና የልጅ ልጃቸው የቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ ባለቤት የእቴጌ መነን አስፋው የዘር ሃረግ ናት።
የቤተሰብ ሕይወትና አስተዳደግ
ልዕልት ሊሲ የታዋቂው አርቲስት ልዑል ይስሐቅ ፍቅረ ሥላሴ እና የቴክኖሎጂ ባለሙያ እንዲሁም የሰብአዊ መብት ተሟጋች ልዕልት አስኳል ተፈሪ ልጅ ስትሆን፣ የልዕልት እጅጋየሁ ፍቅረ ሥላሴ ታናሽ እህት ናት።
በሰሜን ካሊፎርኒያ አሜሪካ ያደገች ቢሆንም፣ ከኢትዮጵያ ባህል፣ እምነት እና ማህበረሰብ ጋር ባላት ጠንካራ ቁርኝት ትታወቃለች። እናቷ ገና በለጋ ዕድሜዋ ያስተማረቻትን አማርኛ ቋንቋ አቀላጥፋ ማንበብ፣ መጻፍ እና መናገር የምትችል ሲሆን፣ የኢትዮጵያን ባህላዊ እሴቶችና ታሪክ ጠብቆ በማስቀጠል ረገድ ከፍተኛ ፍላጎት አላት።
ትምህርት እና ሙያዊ ፍላጎት
ልዕልት ሊሲ በትምህርቷ የላቀ ስኬት ያስመዘገበች ሲሆን
👉ከካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ (University of California, Santa Cruz) በሶስት ዓመታት ብቻ በትምህርቷ በመግፋት በሞለኪውላር፣ ሴል እና ልማት ባዮሎጂ (Molecular, Cell, and Developmental Biology) የሳይንስ የመጀመሪያ ዲግሪዋን (B.S.) አግኝታለች።
👉በአሁኑ ወቅት ትኩረቷን በቤተ-ሙከራ ምርምር (Lab Research) እና በድህረ-ምረቃ (Master's programs) ትምህርቷ ላይ ያደረገች ሲሆን፣ ወደፊት በኢትዮጵያ የጤናው ዘርፍ አስተዋጽኦ የሚያበረክት ክሊኒክ የማቋቋም ትልቅ አልም አላት።
ዓለም አቀፍ ዝና እና የበጎ አድራጎት ሥራዎች
Le Bal des Débutantes (2023)፦ እ.ኤ.አ. በ2023 በፓሪሱ ሻንግሪ-ላ ሆቴል በተካሄደውና ከዓለም ዙሪያ የተተውጣጡ የንጉሣውያን እና የታዋቂ ቢሊየነሮች ቤተሰብ ወጣቶችን በሚያስተናግደው Le Bal des Débutantes ዝግጅት ላይ የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊት ተካፋይ ሆና በመመረጥ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ደረጃ በክብር ወክላለች።በዝግጅቱም የላንቪን (Lanvin) ዲዛይን ቀሚስ እና የቪ-ሙሴ (V MUSE) ጌጣጌጦችን በመልበስ የፋሽንና የዜና መጽሔቶች ትኩረት ሆናለች።
የበጎ አድራጎት እንቅስቃሴ፦ በራሷ ተነሳሽነት በሸዋ ሮቢት እና በደብረ ብርሃን የሚገኙ ወጣት ልጃገረዶችን ትምህርት ለማገዝ እና ራሳቸውን የመቻል አቅም ለማጎልበት የተለያዩ የበጎ አድራጎት ሥራዎችን ታከናውናለች።
እ.ኤ.አበታህሳስ 2022/2023 ወደ ኢትዮጵያ በመጓዝ የማህበረሰብ ጉብኝትና ድጋፍ አድርጋለች።

ህሩይ የፋሽንና የውበት ማሰልጠኛ ት/ቤት 140 ተማሪዎችን አስመረቀ
#ethiopia | በእንጅባራ ከተማ የሚገኘው ህሩይ የፋሽንና የውበት ማሰልጠኛ ት/ቤት በ5ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን 140 ተማሪዎች በድምቀት አስመርቋል።
በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ም/መምሪያ ኃላፊ ስንታየሁ መንግስቱ፣ ተቋሙ በከተማዋ የሚገኙ ወጣቶች በጋርመንት ቴክኖሎጂ ዘርፍ የሥራ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ መሆኑን ገልጸዋል።
የፋሽንና የጋርመንት ዘርፍ በቀጣይነት አዳዲስ እሳቤዎችንና የላቀ ክህሎትን የሚጠይቅ በመሆኑ፣ ተመራቂዎቹ በሰለጠኑበት ሙያ ብቻ ሳይወሰኑ በቀጣይም እውቀታቸውንና ክህሎታቸውን ማሳደግ እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።
ዘርፉ የፈጠራ ክህሎትን የሚጠይቅ መሆኑን ያነሱት ኃላፊው፣ ወጣቶች በጋርመንት ቴክኖሎጂ በስፋት በመሰማራት የሥራ ዕድል ፈጥረው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጠይቀዋል። በተጨማሪም ሥራቸውን የማኅበረሰቡን ወግና ባህል በጠበቀ መልኩ እንዲያከናውኑ ለተመራቂዎቹ የሥራ መመሪያ ሰጥተዋል።
የህሩይ የፋሽንና የውበት ማሰልጠኛ ት/ቤት መስራችና ሥራ አስኪያጅ ወጣት ህሩይ አምደወርቅ በበኩሉ፣ ት/ቤቱ በፋሽንና በውበት ዘርፍ ለወጣቶች የሥራ ዕድል በመፍጠር የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ያለ ተቋም መሆኑን ተናግሯል።
በተለይም እየተነቃቃ የመጣውን የባህል አልባሳት በማዘመንና ከዘመኑ ፋሽን ጋር በማጣጣም ወጣቶችን የሙያ ባለቤት ማድረግ የት/ቤቱ ዋና ዓላማ መሆኑን ገልጿል።
ህሩይ የፋሽንና የውበት ማሰልጠኛ ት/ቤት በ5ኛ ዙር የገበያውን ፍላጎት ያሟላሉ ብሎ ያመናቸውን 140 ተማሪዎች አሰልጥኖ ማስመረቁንም ገልጿል።
ወጣት ህሩይ እንደገለጸው፣ የፋሽንና የጋርመንት ዘርፍ በአነስተኛ ወጪ የሥራ ዕድል ለመፍጠር ሰፊ አቅም ያለው ዘርፍ ነው። ይህም ሀገሪቱ የያዘችውን የዕድገት ጎዳና ለማፋጠን ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ጠቁሟል።
ዘርፉ አሁንም በሀገር ውስጥ በሙሉ አቅሙ ያልተለማ መሆኑን የገለጸው ወጣት ህሩይ፣ ከውጭ የሚገቡ አልባሳትን በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት እየተደረገ ላለው ጥረት ተቋሙ የበኩሉን ድርሻ ለመወጣት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን አመላክቷል።
በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ የ5ኛ ዙር ሰልጣኝ ተመራቂዎች በሰሯቸው የሙያ ሥራዎች ተወዳድረው ለውጤታማ ተማሪዎች ሜዳሊያዎችና ሽልማቶች ተበርክተዋል።
ከተመራቂዎቹ መካከል 13 ዓመቷ ታዳጊ ፀደኒያ ታደለ ከመደበኛ ትምህርቷ ጎን ለጎን የሙያ ባለቤት ለመሆን በማሰብ ስልጠናውን በስኬት አጠናቃ ተመርቃለች።
ታዳጊዋ በምረቃው ዕለት በራሷ የሰራችውን የሙያ ሥራ ይዛ በውድድሩ ተሳትፋ አንደኛ ደረጃን በማስመዝገብ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆናለች።
ይህም የወጣቶችና የታዳጊዎች የሙያ ትምህርት ከመደበኛ ትምህርት ጋር ተጣምሮ ለቀጣይ ሕይወታቸው ጠቃሚ ክህሎት እንዲያገኙ የሚያስችል መሆኑን ያሳያል።

9 days ago
“እኛ ህንዶች የሰውን ህይወት የምንቀማ ሳንሆን ህይወት የምናድን ህዝቦች ነን” — ናሬንድራ ሞዲ
#ethiopia | የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ “እኛ ህንዶች የሰውን ህይወት የምንቀማ ሳንሆን ህይወት የምናድን ህዝቦች ነን” ሲሉ ተናገሩ።
ይህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ህንድ በአለም አቀፍ መድረክ የምታንጸባርቀውን ሰላማዊ እና ህይወትን የማዳን መርህ የሚያጎላ ነው።
ህንድ ለታዳጊ እና ለበለጸጉ ሀገራት ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸውን አስፈላጊ መድኃኒቶች እና ክትባቶችን በማቅረብ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ህይወት በማዳን ላይ ትገኛለች ብለዋል።
በተለያዩ ሀገራት የተፈጥሮ አደጋዎች፣ ግጭቶች ወይም ወረርሽኞች በሚከሰቱበት ወቅት ህንድ ቀድማ በመድረስ ፈጣን የሰብአዊ እና የህክምና እርዳታ በማቅረብ ትታወቃለች ነው ያሉት።
የህንድ ታሪክ እና ባህል በግጭት እና በጦርነት ሳይሆን በሰላም በወንድማማችነት እሴቶች ላይ የተገነባ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አጽንኦት ሰጥተውበታል።
በአጠቃላይ ሞዲ በንግግራቸው ህንድ ከአለም ሀገራት ጋር ያላትን ግንኙነት በኃይል እና በግጭት ሳይሆን በህይወት አድኚነት፣ በህክምና ድጋፍ እና በወንድማማችነት መንፈስ ላይ ተመስርታ እንደምትቀጥል ገልጸዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #pmmodi #narendramodi #india #indiaforeignpolicy #globalsouth #humanitarianaid

የፖሊስ አባሏ መፀዳጃ ጉድጓድ የተጣለች አራስ ሕፃንን ጡት በማጥባት ከመሞት ታደገቻት።
👉ጉድጓድ ውስጥ ጥላ የተሰወረችውን እናት ለመያዝ ፖሊስ ክትትል እያደረገ ነው።
በደቡብ ምስራቅ ኦሮሚያ ዞን በነንሠቦ ወረዳ 12 ሜትር ጥልቀት ባለው የመፀዳጃ ቤት ጉድጓድ ውስጥ የተጣለችን አራስ ሕፃን የፖሊስ አባሏ በሕብረተሰቡ ትብብር ከጉድጓድ አውጥታ የራሷን ጡት በማጥባት ሕይወቷን መታደጓን የወረዳው ፖሊስ አስታወቀ።
የነንሠቦ ጨቢ ከተማ የፀጥታ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ማሙሽ ከድር እንዳስታወቁት፤ የነንሲቡ ወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት የሴቶችና ሕፃናት ክፍል ኃላፊ የሆነችው ዋና ሳጅን አስቴር ደበሌ ይህንን የሰብአዊነት ተግባር ፈፅማ ሕፃኗን ከሞት ታድጋታለች።
መስከረም 21 ቀን 2109 ዓ.ም ከነንሠቦ ጨቢ አካባቢ ነዋሪዎች ለፖሊስ ባደረሱት ጥቆማ መሠረት፣ ዋና ሳጅን አስቴር ደበሌ 21 ኪሎ ሜትር ያህል መንገድ በመጓዝ መፀዳጃ ጉድጓድ ውስጥ ተጥላ ስታለቅስ የነበረችውን ሕፃን በፍጥነት በሕዝብ ትብብር ማስወጣት ችላለች።
የፖሊስ አባሏ ከመፀዳጃ ጉድጓድ የወጣችውን ሕፃን ሳትጠየፍ ካጠበችው በኋላ የራሷን ጡት በማጥባት በሕይወትና በሞት መካከል የነበረችውን የሳምንታት ዕድሜ አራስ ልጅ ታደጋለች።
አቶ ማሙሽ ከድር አክለው እንደገለጹት፣ የዋና ሳጅን አስቴር ደበሌ ተግባር ለብዙዎች ታላቅ አርአያና የእውነተኛ ሰብአዊነት ማሳያ መሆኑን የገለፁ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ከመፀዳጃ ጉድጓድ የወጣችው ሕፃን በነንሠቦ ጨቢ ጤና ጣቢያ የሕፃናት ማቆያ አስፈላጊው ክትትል ተደርጎላት በሙሉ ጤንነት ላይ ትገኛለች።
የሳምንታት እድሜ ያላትን ልጅ መፀዳጃ ጉድጓድ ውስጥ ጥላ የተሰወረችውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር ለማዋል በፖሊስ በኩል ክትትል እየተደረገበት ይገኛል።
ትግስት ላቀው

(ዘ-ሐበሻ ዜና) በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል ከቅርብ ቀናት ወዲህ እያደገ የመጣው የጦርነት ነጋሪት እና የድንበር ላይ ውጥረት አሜሪካን ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ጥሏታል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው ይፋዊ መግለጫ፣ የአፍሪካ ቀንድ ሌላ ጦርነት እና የሰብዓዊ ቀውስ መሸከም እንደማይችል በማስገንዘብ ሁለቱ ሀገራት ከከፋ ግጭት ራሳቸውን እንዲቆጥቡ እና ወደ 2018ቱ የሰላም ስምምነት ማዕቀፍ እንዲመለሱ ጥሪ አቅርቧል።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ቶማስ (ቶሚ) ፒጎት ባወጡት የፕሬስ መግለጫ፣ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል እያደገ የመጣው ድንበር ተሻጋሪ ውጥረት አጠቃላይ ቀጠናውን ሊያዳርስ እና ሊያተራምስ የሚችል አቅም እንዳለው አስጠንቅቀዋል። ቃል አቀባዩ በመግለጫቸው የአፍሪካ ቀንድ ተጨማሪ ወታደራዊ ግጭት እና የሰብአዊ ቀውስን የመቋቋም አቅም እንደሌለው አፅንኦት ሰጥተዋል። አክለውም ይህ አዲስ ሊፈጠር የሚችል ግጭት፣ አሜሪካ ከሁለቱም ሀገራት ጋር በጋራ ጥቅሞች ዙሪያ እያደረገች ያለውን ትብብር አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑን አሳስበዋል።
የአሜሪካ መንግስት ሁለቱም ሀገራት የጎረቤቶቻቸውን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት እንዲያከብሩ፣ እንዲሁም ከፍተኛ የሆነ የራስን የመግዛት እርምጃ እንዲወስዱ አጥብቆ ጠይቋል። ከዚህ በተጨማሪም አዲስ አበባ እና አስመራ በ2018ቱ የሰላም ማዕቀፍ በተስማሙት መሰረት ወደ ንግግር እና ትብብር እንዲመለሱ ጥሪ ቀርቧል። አሜሪካ በውይይት የሚገኝ ሰላም ለዘላቂ ደህንነት፣ ለኢኮኖሚ ዕድገት እና ለብልጽግና ብቸኛው መንገድ መሆኑን በመግለጫዋ አስታውቃለች።
ይህ የአሜሪካ መግለጫ የወጣው የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት በኤርትራ ላይ የከረረ ዛቻ ባሰሙበት እና የኤርትራ ጦር በበኩሉ በድንበር አካባቢ ግስጋሴ እያደረገ ነው በሚባልበት እጅግ ወሳኝ ወቅት ነው። የአሜሪካ "የሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ይከበር" የሚለው መልዕክት ለሁለቱም ሀገራት የተሰጠ ቀጥተኛ ማስጠንቀቂያ ሲሆን፣ በተለይም ግጭቱ ወደ አጠቃላይ የቀጠናው ጦርነት እንዳያመራ ያላትን ከፍተኛ ስጋት ያሳያል። የ2018ቱን የሰላም ስምምነት ማንሳት፣ ሁለቱ ሀገራት የትላንት ወዳጅነታቸውን አስታውሰው አፈሙዝ ከማዞር ወደ ዲፕሎማሲያዊ ጠረጴዛ እንዲመለሱ የተደረገ የዲፕሎማሲ ግፊት ነው።
______
🗣️ የዘ-ሐበሻ የመወያያ ጥያቄ፦ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እና የአሜሪካ ግፊት የኢትዮጵያ እና ኤርትራን ውጥረት አብርዶ ወደ ድርድር ጠረጴዛ ያመጣቸዋል ብላችሁ ታምናላችሁ?

10 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) ኢልሀን ኡመር ‹‹የኢትዮጵያ ህዝብ ሰላምና ፍትህ ያስፈልገዋል›› አሉ፡፡ የአሜሪካ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት ኢልሀን ኡመር የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ መግለጫ አውጥተዋል፡፡ የሚኖሶታ ግዛት ተወካይ የሆኑት ኢልሀን ኡመር መግለጫውን ያወጡት ከካሊፎርኒያው ተወካይ ጆን ጋራሚድኒ ጋር በመሆን ሲሆን በመግለጫቸው ‹‹ባለፈው ሳምንት በትግራይ ክልል እርዳታ ጭኖ ይጓዝ በነበረ ተሸከርካሪ ላይ የኢትዮጵያ ጦር የፈፀመውን ጥቃት ጨምሮ በኢትዮጵያ ውስጥ እየጨመረ የመጣው ግጭት በጣም አሳስቦናል›› በማለት ጀምረዋል፡፡
ሲቀጥሉም ‹‹በሰሜን ኢትዮጵያ የጠመንጃን ድምፅ ባስቆመው የ2022ቱ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ሁሉም አካላት ግጭትን ለማቆም፣ ሲቪሎችን ለመጠበቅ፣ ለተጎዱ ሰብአዊ አገልግሎት እንዲሰጥ ለመፍቀድና ለሰብአዊ መብት ጥሰቶች ተጠያቂዎችን ለህግ በማቅረብ የሽግግር ፍትህ ለማስፈን ቁርጠኛ መሆናቸውን የገለፁበት ነበር›› በማለት ጠቅሰው ይሁንና ስምምነቶቹ አለመከበራቸውንና ሁኔታዎቹ አለመሟላታቸውን አስታውቀዋል፡፡ በማስከተልም እየጨመረ የመጣው ግጭት መላውን አገሪቱንና ቀደም ባለው የአሜን ኢትዮጵያ ጦርነትና በሱዳን ግጭት የተጎዳውን ቀጠናውን ጭምር አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
በዚህ ውስጥ ሰላማዊ ሰዎች የጥቃቱ ሰለባ እንደሚሆኑ ጠቁመውም ‹‹በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ሁሉም አካላት በአስቸኳይ ለሰላም ድርድሩ ቁርጠኛ እንዲሆኑና በፕሪቶሪያ ስምምነት ስር ያሉ ሀላፊነቶቻቸውን እንዲወጡ እናሳስባለን›› ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ጎረቤት አገራትና አለም አቀፍ ማህበረሰቡም ውጥረቱን ለማርገብና ሰላምን ለማመቻቸት መስራት እንደሚገባቸው ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የተፈጠረውን ግጭት ለማስቆምና በዚህ ሀላፊነት ያለባቸውን ተጠያቂ ለማድረግ ከሁሉም አካላት ጋር እንዲሰራ ያሳሰቡት እነኢልሀን ኡመር በማጠቃለያቸውም ‹‹የኢትዮጵያ ህዝብ ሰላምና ፍትህ ያስፈልገዋል›› ብለዋል፡፡

12 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) አቡነ ተስፋስላሴ መድህን ‹‹ተነጥለናል፣ አስቸኳይ የሰብአዊ እርዳታ ጣልቃ ገብነት ያስፈልገናል›› አሉ፡፡ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የአዲግራት አገረ ስብከት ጳጳስ የሆኑት አቡነ ተስፋስላሴ መድህን ዛሬ በላኩት መረጃ ‹‹የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት እንዲመቻች፣ የሰላም ውይይት እንዲፈጠርና የማናቸውም አይነት ንግግሮች ሂደት እንዲጀመር ማድረግ እጅግ አጣዳፊ ጉዳይ ነው፡፡ የመገናኛ መስመሮቻችን ተቋርጠዋል፣ ከማንም ጋር ምንም ግንኙነት የለንም፡፡ ሙሉ በሙሉ ተነጥለናል›› ብለዋል፡፡ የቤተክርስቲያኗ የሀይማኖት አባቶች ባሉበት ቦታ ሆነው የተለመደ አገልግሎታቸውን እየሰጡና ህዝቡን በቻሉት መጠን እየረዱ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡
አስከትለውም ‹‹ባንኮች ተዘግተዋል፣ የካህናት ማሰልጠኛዎቻችንና ትምህርት ቤቶቻችን ስራቸውን እንዲቀጥሉ የምንፈልግ ቢሆንም እንዴት እንደሚቀጥሉ ግን በእርግጠኝነት አናውቅም፡፡ አስፈላጊ አቅርቦቶችን እንዴት እንደምናስተዳድር አናውቅም፡፡ የሚያውቀው እግዚአብሄር ብቻ ነው፡፡›› በማለት አስረድተዋል፡፡ ይህንን መልእክት ያስተላለፉት ለቤተክርስቲያኗ ድጋፉን በቀጠለውና ከውጭው አለም ጋር መጠነኛ ግንኙነት እንዲኖር ጥረት እያደረገ ባለው ለአለም ህፃናት መርጃ ድርጅት(ዩኒሴፍ) አማካኝነት ነው፡፡ መልእክቱን ለማስተላለፍ የፈለጉትም በትላንትናው እለት የአለም ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ሊዮ 14ተኛ በትግራይ ክልል ያለው ግጭት እንዲቆም ማሳሰባቸውን ተከትሎ ነው፡፡
ሊቀ ጳጳሱ በትላንት ንግግራቸው ‹‹ሁሉም አካላት የውይይት መንገድን እንዲመርጡ ከልብ የመነጨ ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡ ወታደራዊ ግጭቶች ችግሮችን አይፈቱም፡፡ ይልቁኑ ሞትን፣ ውድመትንና ጥላቻን በማስከተል ሁኔታውን የበለጠ ያባብሳሉ፡፡ ዘላቂ ሰላም ሊመጣ የሚችለው በቅንነት በሚደረግ ውይይት ብቻ ነው›› ካሉ በኋላ ይህን ጦርነት ተከትሎ ለችግር ለተዳረጉት አለም አቀፉ ማህበረሰብ አስፈላጊውን የሰብአዊ እርዳታ በማድረግ አስተዋፅኦ ያደርጋል የሚል ተስፋ እንዳላቸው መግለፃቸው ይታወሳል፡፡

በሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች በዩኒቨርሲቲ መኖሪያ ቤት ላይ በፈጸሙት የድሮን ጥቃት 5 ሰዎች ሲገደሉ 47 ሰዎች ቆሰሉ
የሱዳን የሃኪሞች መረብ እንደገለጸው፣ ጥቃቱ በማዕከላዊ ሱዳን ኤል-ኦቤይድ ከተማ የሚገኘውን የኮርዶፋን ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች መኖሪያ ቤት ዒላማ ያደረገ ሲሆን፣ ድርጊቱም ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ሕግን የጣሰ ነው ሲል ኮንኖታል።
እንደ ሱዳን የሃኪሞች መረብ ዘገባ ከሆነ ረቡዕ ዕለት ፓራሚሊታሪ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች (RSF) በማዕከላዊ ሱዳን ኤል-ኦቤይድ ከተማ በሚገኘው የኮርዶፋን ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች መኖሪያ ቤት ላይ በፈጸሙት የድሮን ጥቃት ቢያንስ አምስት ሰላማዊ ሰዎች ሲገደሉ 47 ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል።
በተጨማሪም በሰላማዊ ሰዎች እና በሕዝብ አገልግሎት ተቋማት ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች አሳሳቢ በሆነ ሁኔታ እየጨመሩ መምጣታቸውን አስጠንቅቋል። ቡድኑ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች እና የሰብአዊ እርዳታ ድርጅቶች በሰላማዊ ሰዎች መሰረተ ልማቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን እንዲያወግዙ፣ ተጠያቂዎችን ተጠያቂ እንዲያደርጉ እና ለተጎዱት አስቸኳይ የሕክምና እርዳታ እንዲያቀርቡ ጥሪ አቅርቧል።
የሱዳን ባለስልጣናት እና የሰብአዊ መብት ቡድኖች የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎችን በሰላማዊ ሰዎች ተቋማት ላይ ጥቃት ያደርሳሉ ሲሉ የሚከሱ ሲሆን፤ ፓራሚሊታሪ ቡድኑ ሰላማዊ ሰዎችን ለመጠበቅ እንሰራለን ከማለት ባለፈ ለክሶቹ ቀጥተኛ ምላሽ አይሰጥም።
ሱዳን ከሚያዝያ 2023 ጀምሮ በሰራዊቱ እና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች መካከል በሚካሄድ ውጊያ ውስጥ የምትገኝ ሲሆን፤ ይህም በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ለህልፈት እና ሚሊዮኖችን ደግሞ ስደት ዳርጓል።
ሰላማዊ ነጋሲ

13 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ(ኦቻ) ሀላፊ ዛሬ ባወጡት መግለጫ በሰሜናዊ ኢትዮጵያ ውስጥ በፍጥነት እየተለዋወጠ ያለውን ሁኔታ ከሰብአዊ እርዳታ ሰጪ ማህበረሰብና ከቀጠናው አጋሮቻቸው ጋር በመሆን በቅርበት እየተከታተሉት መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ሁኔታው በሰላማዊ ሰዎች ጥበቃ በተለይም ከዚህ ቀደም በነበረው ግጭት የተፈናቀሉ ሰዎችን የደህንነት ስጋት ውስጥ የሚከትና አዲስ መፈናቀልንም የሚያስከትል ሆኖ እንዳገኙትም አስረድተዋል፡፡
ተቋማቸው እንደሰብአዊነት ማህበረሰብ በግጭት በተጎዱት ቦታዎች መገኘቱን እንደሚቀጥል የጠቀሱት ሀላፊው ይሁንና ‹‹አሁን ግጭት በተቀሰቀሰባቸው የሰሜናዊ ኢትዮጵያ አካባቢዎች የእርዳታ ድርጅት ሰራተኞች፣ ንብረቶችና ግቢ ውስጥ እንዲሁም በሰላማዊ መሰረተ ልማቶች ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶችን በሚመለከት የሚደርሱኝ መረጃዎች ያሳስቡኛል›› ብለዋል፡፡ እ.ኤ.አ ከ2025 እስከ 2026 ባለው ጊዜ ውስጥ በግጭት በተጎዱ አካባቢዎች ከሚንቀሳቀሱ የእርዳታ ድርጅቶች ላይ ታጣቂ ሀይሎች ቢያንስ 10 የሰብአዊ እርዳታ ተሸከርካሪዎች መወሰዳቸውን ገልፀውም ከእነዚህ ውስጥ የተመለሱት 2ቱ ብቻ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡
እንዲሁም በእርዳታ ሰራተኞች ላይ እገታ ዝርፊያና ጥቃት መከናወኑን ጠቅሰው የህዝብ ንብረት የሆኑ ህንፃዎችና ወሳኝ መሰረተ ልማቶች መያዛቸውን፣ መጎዳታቸውንና መበላሸታቸውን አስታውቀዋል፡፡ እንዲህ አይነት እርምጃዎች ከፍተኛ የሰብአዊ እርዳታ ፍላጎት በሚኖርባቸው ጊዜያቶች የእርዳታ ስራዎችን በአግባቡ ለማከናወን እንዳይቻል እንቅፋት እንደሚፈጥሩም ገልፀዋል፡፡ መግለጫቸውን በመቀጠልም ‹‹የእርዳታ ሰራተኞችና ንብረቶቻቸው በአለም አቀፍ የሰብአዊነት ህግ መሰረት ጥበቃ የሚደረግላቸውና ኢላማ መሆን የማይገባቸው ናቸው›› ያሉት የኦቻ ሀላፊ እርዳታ ሰራተኞች ያለምንም ገደብ በነፃነት ስራቸውን እንዲሰሩ ሊፈቀድላቸው እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡
በመሆኑም በታጣቂ ሀይሎች የተያዙት የእርዳታ ድርጅቶች ተሸከርካሪዎች በሙሉ እንዲለቀቁ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ አስከትለውም ‹‹ሁሉም ወገኖች አለም አቀፍ የሰብአዊነት ህግን እንዲያከብሩ፣ የሰብአዊነት መርሆዎችን እንዲከተሉና የሰብአዊነት ስራዎችን እንዳያደናቅፉ እንዲሁም የሰብአዊ እርዳታ ሰራተኞች ደህንነቱ የተጠበቀና ያልተገደበ እርዳታ እንዲሰጡ እንዲያደርጉ ጥሪዬን አቀርባለሁ›› ብለዋል፡፡

Comments