4 months ago
ቴዲ አፍሮ ‘ኢቶሪካ’ የተሰኘውን አዲስ አልበም ሊለቅ ነው!
#ethiopia | የኢትዮጵያ የሙዚቃ ንጉሥ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) አድማጮቹ ለዓመታት በጉጉት ሲጠብቁት የነበረውን አዲስ አልበም ይፋ አደረገ።
‘ኢቶሪካ’ የተሰኘው ይህ አዲስ አልበም በመጪው ሐሙስ ለሕዝብ ይፋ ይሆናል።
ሐሙስ ሚያዝያ 8/2018 ዓ.ም.
ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
በ ቴዲ አፍሮ ይፋዊ የዩቲዩብ ቻናል
(Teddy Afro Official YouTube)
"ኢቶሪካ" - የታሪክና የዜማ ቅንጅት!
የጥበብ አፍቃሪው በጉጉት የሚጠብቀው ይህ አልበም፣ በኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ውስጥ አዲስ ታሪክ ይጽፋል ተብሎ ይጠበቃል።
#getu #teddyafro #etórica #newalbum #ethiopianmusic #breakingnews #teddyafroofficial #addisababa #ethiopia #ኢቶሪካ #ቴዲአፍሮ #አዲስአልበም #ጥበብ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

1 year ago
የአዲስ ነገሩ ዐቢይ ተክለማሪያም (ክፍል ሁለት)
#ethiopia | ተወዳጅ ሚድያ እና ኮምዩኒኬሽን የባለሙያዎችን የሕይወት ታሪክ ሰንዶ በማስቀመጥና በማሰራጨት፣ በመፅሐፍ ላይ እንዲታተም በማድረግ የባለሙያዎች አበርክቶ ተዘንግቶ እንዳይቀር የበኩላችን እየተወጣ ይገኛለን፡፡ እስከዛሬ ከ 400 በላይ በሚድያ እና በኪነ ጥበብ ሙያ ላይ ያሉ ባለሙያዎችን ጨምሮ ሌሎችም ታሪካቸው በመረጃ ቋታችን ላይ እንዲቀመጥ አድርገናል፡፡ ስለ እነርሱ ለማወቅ በተፈለገ ጊዜም ፣ታሪካቸው በቀላሉ መገኘት እንዲችል የዲጂታል አማራጮችን በማቅረብ የታሪኰቹ ተደራሽነት ዕውን እንዲሆን ሁሉን አመቻችተናል፡፡
ታሪኮቹ በጥራዝ መልክ ተሠንደው ዘመን ተሻጋሪ እንዲሆኑም ቅፅ አንድ እና ቅፅ ሁለት መዝገበ አእምሮን እያንዳንዳቸውን በ600ገፅ አድርገን አዘጋጅተን፣ አሳትመን ፣ አስተዋውቀን እና አስመርቀን ሀገራዊ ኃላፊነታችንን ተወጥተናል፡፡ አሁንም የስነዳ ሥራው ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን የመማክርት አባላት እንዲሰነዱ ስምምነት የደረሱባቸው ባለሙያዎችን እያፈላለግን መሥራታችን ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡
በቅፅ ሁለት የሕይወት ታሪካቸው ከሚሰነድላቸው መካከል የአዲስ ነገሩ ዐቢይ ተክለማሪያም አንዱ ነው፡፡ ስለ ዐቢይ ለመፃፍ ስንነሳ ቀዳሚ ግባችን በአገሪቱ የሕትመት ሚድያ አፃፃፍ ላይ የራሱን አሻራ ያኖረ በመሆኑ ነው፡፡ ሁለትም የዛን ጊዜ የነበረው የመዝናኛ እና የአዲስ ነገር ጋዜጦች የዝግጅት ቡድን ምን ያህል ጠንካራ ስብስብ እንደነበር ለማሳየት በማሰብ ነው፡፡ ይህ ቡድን በዐቢይ የሚመራ በመሆኑ የዛን ጊዜ ከነበረው ዐቅምና ጉልበት የዛሬዎቹ የሚድያ ሰዎች ምን ልንማር እንችላለን ? የሚለውንም ለመጠቆም ፈልገንም ነው።በአሁኑ ሰዓት የሕትመት ሚድያው ማንሠራራት ሲገባው ጭራሽ ያሉትም የህልውና አደጋ ተጋርጦባቸዋል፡፡ እናም በዚህ አጋጣሚ የሚመለከታቸውን ለማንቃት ይህ መጣጥፍ አንዳች አስተዋፅዖ ያበረክታል ብለን እናምናለን፡፡
ይህን ፅሑፍ ለማጠናከር ቀና ተባባሪ ሆነው መረጃ የሰጡንን ሰዎች ከታች በተቀመጠው መልኩ ምስጋናችንን ልናቀርብ እንወዳለን፡፡
ሕሊና ተክለማሪያም የዐቢይ ታናሽ እህት
ጌታቸው አዲሱ የዩኒቨርሲቲ አብሮ አደግ ጓደኛ
ዳኝነት መኰንን የሥራ ባልደረባ
ደመላሽ አማረ
ብርሀኑ ደቦጭ
መኰንን ተሾመ
ሔኖክ ስዩም።
ኤፍሬም ታደሰ አብሮ አደግ
ኤፍሬም ወዳጆ ገብሩ ከሁለተኛ ደረጃ ጀምሮ የሚተዋወቁ
ባሳዝነው ወንድሜነህ የአዲስ ነገር ግራፊክስ ዲዛይነር
በተለይ ዳኝነት መኰንን እና የሕግ ባለሙያ ጌታቸው አዲሱ 'የሠራ ሰው በአደባባይ መመስገን እና መታየት አለበት ታሪኩም ዘመን በሻጋሪ ዀኖ መሰነድ ይኖርበታል' የሚለውን መርሀችንን ተገንዝበው በተገቢው መልኩ ስለረዱን እና ትክክለኛ መረጃ ስለሰጡንም በልዩ ሁኔታ የምስጋና ቃላትን ማቅረብ እንወዳለን፡፡
ይህ የሕይወት ታሪክ ፅሑፍ ዛሬ ሐምሌ 7 2017 በይፋ የሚከበረውን 48ኛ ዓመት የዐቢይን ልደት ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ ሲሆን የፅሑፉም ባለመብት ተወዳጅ ሚድያ መዝገበ አእምሮ ዝግጅት ክፍል ሲሆን ፅሑፉንም ወስደው ሲያሰራጩ ምንጭ መጥቀሱን ፈፅሞ እንዳይዘነጉት፡፡ የፅሁፉ አዘጋጆች ታደሰ ማሞ እና ዕዝራ እጅጉ ሲሆኑ የማህበራዊ ሚድያውን ፖስተር ያሰናዳው ዘሪሁን አሰፋ ነው፡፡ በክፍል አንድ ቆይታችን የዐቢይን የህይወት መስመር ከልጅነት እስከ አዲስ ነገር ያለውን የምንቃኝ ሲሆን ስለ ዐቢይ እና ስለ አዲስ ነገር የሚያውቁ የላኩልንን ፅሑፍና የመልካም ምኞት መግለጫ በዚህ ክፍል አካተናል፡፡ ይህንን በ 2 ክፍል የተዋቀረ ፅሑፍ ያነበባችሁ ተጨማሪ የምትሉት ካለ ለማስተናገድ ዝግጁ ነን፡፡ መልካም ንባብ፡፡
አዲስ ነገር ጋዜጣ እና የዘመን ትውስታዎቼ
*ከደመላሽ አማረ
*ደመላሽ አማረ ለንባብ እና ለሂሳዊ ዕይታዎች ልዩ ፍቅር ያለው ባለሙያ ሲሆን በዐቢይ ተክለማሪያም መሥራችነት በየሳምንቱ ቅዳሜ ለሕትመት ትበቃ የነበረችውን ጋዜጣንም በጥልቀት ከሚያነቡት አንዱ ነው፡፡ ደመላሽ በሳልና በጥልቅ ዕይታ የታጀቡ ዳሰሳዎችን በማቅረብ የሚታወቅ ሲሆን ዛሬ የሚከበረውን የዐቢይ ተክለማሪያምን ልደት አስመልክቶ አንድ መጣጥፍ አዘጋጅቷል፡፡
***
የዚያን ዘመን ጋዜጦች አንባቢ የሆንን ሰዎች መጀመሪያ "መዝናኛ" በኋላም "አዲስ ነገር" ጋዜጣ የንባብ ልምዳችን ላይ ተፅዕኖ ፈጥረውብን ነበር ። እነዚህ ሁለት ጋዜጦች ቀደም ብሎ ከነበሩት ጋዜጦች የተለየ የአፃፃፍ ዘዬ ይዘው ስለመጡ በእነዚህ እነርሱን በማንበብ ሱስ ተለክፈን ነበር ። ከእኛም ባለፈ በግሉ ፕሬስ ህትመት ሚዲያ ላይ አዲስ የአፃፃፍ ዘይቤ አብዮት አስነስቶ እንደነበር በወቅቱ ጋዜጦች እና መፅሄቶችን የሚያነቡ ሰዎች የማይዘነጉ ሀቅ ነው።
ጋዜጣዋ በእኔ እና በመሰሎቼ እለተ ቅዳሜን ተወዳጅ እና ተናፋቂ ቀን እንዲሆን ምክንያት ከነበሩ ክስተቶች መሀል ግንባር ቀደም ነበረች ብል የተሳሳትኩ አይመስለኝም ። ምክንያቱም ቅዳሜን በጉጉት ከመጠበቅ በላይ ከቤቴ ዝንጥ ብዬ ወጥቼ ጫማዬን ሊስትሮ ካስጠረግኩ በኋላ አሁን በልማት ምክንያት ከፈረሰችው የኣውቶቢስ ተራዋ ፋሲካ ኬክ ቤት ካመራው በኋላ የተለመደውን ቅዳሜ ብቻ ቁርስ ልማዴ የሆኑትን ፈጢራ እና ማኪያቶ አዝዤ አዲስነገር ጋዜጣን መኮምኮም እቀጥላለሁ ። ቅዳሜ እስከ 6 ሰዓት ኮሌጅ ትምህርት ከሌለኝ በስተቀር በፍፁም ቀጠሮ አልይዝም ነበር ። ታዲያ አንዳንድ ቀን እና ዘና ብዬ ማንበብ ስፈልግ ብቻ ቦታ ቀይሬ ፒያሳ ጉድ ታይምስ ካፌ የፎቁ በረንዳ ላይ ቁጭ ብዬ አነብ ነበር ። ከምንባቡ አፍታ ጊዜ ሳገኝ የፒያሳን አስገራሚ ድባብ እግረ መንገዴን እቃኛ ነበር ። ይህንን ገራሚ የሆነ ቤት የዛቺው ጋዜጣ አምደኛ የሆነው መሀመድ ሰልማን የተባለ ፀሀፊ "ፒያሳ መሀሙድ ጋር ጠብቂኝ "በሚል ርዕሰ ገራሚ ፅሁፍ ፅፎበታል ፡፡ታዲያ ጋዜጣዋ ከህትመት ውጪ ከሆነች በኋላ ያንን ካፌ ባየሁ ቁጥር የጋዜጣዋ ትዝታ ፊት ለፊቴ ድቅን ይልብኘ ነበር።
አልፎ አልፎም ወደ ካፌው ብቅ ስል ከዚህ በፊት ጋዜጣዋን ሳነብ ቁጭ የምልበት ቦታ ላይ ሆኜ በትዝታ እንድተክዝ ያደርገኝ ነበር ።
ታዲያ የማይመለሰውን ጥበቃ በሚል ርዕስ ድህረ 1997ን ምርጫን አስመልክቶ በዚህችው ጋዜጣ ላይ የወጣ ፅሁፍ ነበር ። ፅሁፉን ለማጀብ በጋዜጣዋ ላይ የነበረውም ግራፊክስ አንድ 97 ቁጥር የሚል ታፔላ ያለበት ባስ መቆሚያ ስር ቆሞ የማትመጣውን አውቶቢስ በትካዜ የሚጠብቅ ሰው ምስል የያዘ ነበር ። እኔም ይሰማኝ የነበረው ስሜት እንደዛ ነበር ። ከዓመት ከሁለት ዓመት በኋላ እንደማይመለሱ ሳውቅ ያ ግራፊክስ አይምሮዬ ላይ እየመጣ ያስገርመኝ ነበር ። ጋሸ አሰፋ ጫቦ ለካ “ ሀበሻ የማይመለስ ነገርን የመጠበቅ ልማድ አለው “ የሚለው ወዶ አልነበረም።
እኔም ጉድ ታይምስ ካፌ ሰገነት ላይ ቁጭ ብዬ ይህን የማይመለስ የዘመኔ ክስተት የሆነውን ጋዜጣ በትዝታ የጠበኩባቸው ግዜያቶች ነበሩ ። ታዲያ ስለዚህ ጋዜጣ ባሰብኩ ቁጥር የጋዜጣው መስራች እና ለሀገራዊ አበርክቶው እና ጥሩ ሥራ የሠራው ዐብይ ተክለማርያምን አስታውሰው ነበር ። እርሱን ሳስታውስ ደግሞ አንድ አባባል ትዝ ይለኛል ። ሁላችንም የወጣነው “ከኒኮላይ ጎግል ካፖርት ውስጥ ነው “ የምትል የዶስቶፍስኪ አባባል ። አዲስ ነገር ጋዜጣ ዐብይ ተክለማርያም በጠረገው መንገድ ላይ ስንት እና ስንት እጅግ በጣም አስገራሚ የሆኑ ለሀገሪቷ ፅሁፍ ብቻ ሳይሆን ብዙ ነገር ያበረከቱ ሰዎች እዚህች ጋዜጣ ላይ በቋዋሚነትም ሆነ በተባባሪ ፀሀፊነትም ሲፅፋEzra Egigu Fana:
እንደነበር ብዙዎቻችን የምናስታውሰው ነው። ዛሬም በፖለቲካው እና በተለያዩ መስክ ላይ በብዙ አቅጣጫ የምናያቸው ሰዎች የዛ ጋዜጣ ላይ ይፀፉ የነበሩ ሰዎች መሆናቸውን ሳይ ይገርመኛል ።
በአጭር የተቀጨ አስገራሚ ጉዞ
ይህቺ ጋዜጣ እረጅም ግዜ ብትቆይ ኖሮ የንባብ ባህል ላይ ብቻ ሳይሆን የሀገሪቱ ሁኔታ ላይ ምን ለውጥ ልታመጣ ትችል ነበር ብዬ ሳስብ በአጭር በመቅረቷ አዝን ነበር። ምክንያቱም ያ ጋዜጣ ብቻ ሳይሆን ነጮች think thank group (የባለዕውቀቶች ስብስብ) እንደሚሉት ዓይነት ዘርፈ ብዙ የሆነ አብርክቶ መስጠት የምትችል ጋዜጣ እነደነበረች በነበራት ውስን ዓመታት ውስጥ ማሳየት ችላ ነበር ። በተለይ የፊቸር አምዳቸው ከጋዜጣ ትንታኔ የዘለለ ጥልቀት እና ስፋት ያላቸውን መረጃዎች ታቀርብልን ነበር ። በየሣምንቱ የ3 የ4 ፕሮፌሰሮች የሁለት ሶስት ዶክተሮች ብዙ ምርምሮችን አገላብጠው ነበር ያንን ፅሁፍ የሚያቀርቡልን ። ጊዜው እንዴት እንደሚበቃቸው ፈጣሪ ይወቀው ። ሰው እንዴት በየሳምንቱ መመረቂያ ፅሁፍ የሚመስል መረጃ ማቅረብ ይችላል? እጅግ የሚገርም ዐቅም ነው።
ይህ አቀራረብ በሀገራችን የጋዜጦች ታሪክ ውሰጥ የተለመደ ነገር አልነበረም። ጋዜጦች ዜና ከመቃረም እና ከማቅረብ በስተቀር በዛ ልክ ጥልቀት እና ስፋት ያላቸው ትንታኔዎች የሚያቀርቡበት አጋጣሚ አልነበረም።
ከመዝናኛ ወደ አዲሰ ነገር የተደረገው ሽግግር
ስለ አዲስነገር ሳስብ የሚገርመኝ መዝናኛ ጋዜጣ ላይ ስለ ተለያዩ ስፖርታዊ መዝናኛ ጉዳዮች ላይ ይፅፉ የነበሩ ልጆች ምርጫ 97 አስታኮ vote or died በሚል ርዕሰ ጉዳይ ወደፓለቲካ የተደረገው ሸግግር ቆይቶ አዲስ አዲስ ነገርን አዋልዶልናል። በዚህ ሸግግር ወስጥ የዐብዬ ሚና ለየት ያለ ይመሰለኛል ። ይህ እራሱ አስገራሚ ነገር ነው ።
ጋዜጣዋ ድህረ 97 የነበረውን የቅንጅት ጥንካሬ እና ድክመትን ከሌሎች ጋዜጦች በተለየ ሁኔታ ከመዘገቡዋም በላይ የቅንጅትን ስንጠቃ ሌሎች ጋዜጦች ደፍረው ከማውጣታቸው በፊት ፕሮፌሰር መስፍንን ቃለ-መጠይቅ በማድረግ ይህንንም ዐብይ ክስተት የገለጠችልኝ ጋዜጣ ነበረች ።
ከዚህ ውጪ ከአብዮታዊ ዲሞክራሲ እስከ ሊብራል ዲሞክራሲ ድረስ ያሉ ፅንሰ- ሀሳቦች የሚንሸራሸሩበት ነበር። በተለይ ለሊብራል ዲሞክራሲ እጅግ በጣም ሰፊ መደላደል ያለው እና ብዙዎቻችን ሊብራል ዲሞክራሲ ፅንሰ ሀሳብን አጥምቃናለች ባልልም እንኳን መረጃ ግን አብዝታሰጥታን ነበር ። ግን ያም ቢሆን ጋዜጦችን በጣም ከሚያስገርሙኝ ነገሮች አንዱ አብዮታዊ ዲሞክራሲንም ሆነ ልማታዊ መንግስትም ለሚሰብኩ ፀሀፊዎች በሯ ክፍት ነበር። በመንግሥት ጋዜጦች በዛ ልክ ከምርጫ ግዜ በፊት መንግስት ከሚከተለው ርዕዮተዓለም በተቃርኖ ለሚፀፉ ሰዎችን ያስተናግዳሉ ብዬ አላስብም። ይሄም የዐብይ ውጤት ነው። ታዲያ በአቢዮታዊ ዴሞክራሲ ርዕዬት ላይ ይፅፋ ከነበሩት መሀል አንዱ አቶ ጌታቸው ረዳ ነበር ። በወቅቱ የብዙዎችን ቀልብ የሳበው አዳዲስም አንባቢዎች እንዲመጡ ያረገው በአቶ ጌታቸው ረዳ እና በዶክተር ዳኛቸው አሰፋ መካከል ብርቱካን ሚደቅሳ ቃሌ በሚል በተናገረችው እና ለዳግም እስር በተዳረገችው ጉዳይ ላይ ሳምንታት የፈጀ ክርክር ነበር። ይህ የህግ ፣ የፍልስፍና እና የዲሞክራሰሲ ሙግት በጣም የበሰለ እና ጥልቀት ያለው ክርክር እንደ ነበር አስታውሳለሁ ።
በጋዜጣው ሌላው አስገራሚ ነገር የቴዲ አፍሮ ጉዳይ ነው ። ቴዲአፍሮ እና አዲስነገር ጋዜጣ የሆነ ሰዓት ላይ በርዕሰ አንቀፅ ደረጃ ሳይገባቸው ዙፋን የጨበጡ ብሎ ቴዲ አፍሮን የመተቸት ነገር ነበር ። መልሶ በኋላ በውስጥ ገፅ ላይ ቴዲ አፍሮ አይከን ነው ብሎ አውጥተዋል ። ሁለት አወዛጋቢ የሆነ ርዕስ በቴዲ ጉዳይ ላይ አዲስ ነገር ጋዜጣ። ሌላው አዲስነገር እና ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ናቸው ። በመጀመሪያ ቅርበታቸው ወዳጅነት የሚመስል ብዙ ርዕሶች ላይ ጉዳዮች ላይ ይገቡ ነበር ። በኋላም መስፍን ነጋሽ እና ከሌሎች አምደኞች ጋር በተለያዩ ምክንያቶች ሰጣገባ ውስጥ እንደነበሩ አስታውሳለሁ። እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ እና ደፍሮ መክሸፍን ሲፅፉ ያንን ጉዳይ ከተውት እንደነበር ትዝ ይለኛል ።የአዲስ ጉዳይ አበርክቶ ብዬ የማስበው ከኋላ ያሉ ታሪኮችን ወይም አዲስ ያሉ ክስተቶችን ከመተንተን ባለፈ እነዛ ነገሮች ወደፊት የሀገሪቷ የፖለቲካ የማህበራዊ እና ኢኮኖሚ ላይ የሚፈጥሩትን ነገሮች ሳይንሳዊ የሆነ ትንተና በማድረግ ትገምት ነበር ። ለምሳሌ የአዲስአበባን ውሃ እንደ አዲስነገር የፃፈ አላውቅም ። ውሃ ኢትዮጵያ አዲስአበባ ውስጥ ችግር ሊሆን እንደሚችል በደንብ አድርጋ ሞግታ በምክንያት ተንትና የተለያዩ ሀገራት ተሞክሮ አሳይታ ፅፋልናለች ። ሌላ የወደብ ችግር ወደፊት ሊከሰት እንደሚችል በማሰብ ኢትዮጵያ ምን ዓይነት የወደብ አማራጮችን መከተል አለባት ብላ የኤርትራን ጉዳይ አስታካ የጎረቤት ሀገሮች ያለንን ነገር ተንትና ያለውን ኪሎሜትር ብዙውን ነገር አስቀምጣለች። ዛሬ የምንጨነቅበትን የወደብ ጉዳይ ። እጅግ የሚገርመኝ ደግሞ የ 70/ 30 ፓሊሲ ይህ የትምህርት ፖሊሲ እንደመጣ አዲስነገር በፊቸር አምዷ ላይ ይህን የትምህርት ፖሊሲ በደንብ አድርጋ ተንትና አስቀምጣ ከዚህ በፊት ከነበሩ ነገሮች ጋር አሰናስላና የጋናን የሳውዝ ኤዥያ ጭምር ተንትና ይህ ፖሊሲ አስቸጋሪ እንደሆነ እና ወድያው ተግባራዊ ለመሆንም እራሱን የቻለ ተፅዕኖ ሊፈጥር እንደሚችል ከዛ ውስጥም 40% ኢንጅነሪንግ መሆኑ ወደፊት ኢትዮጵያ ውስጥ ኢንጅነሮች ለሥራ እጦት እንደሚዳረጉ ሁሉ ፅፋ ነበር ። የዛን ጊዜ በጥልቀት እና በስፋት የሚያነብ ቢኖሮ ኖሮ ከነዛ ሁሉ ነገሮች መጠንቀቅ ይቻል ነበር ።
አዲስ ነገር በታሪክ ውስጥ ምን ስፍራ ይሰጣት ነበር ብዬ ሳስብ የፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴን The pionner of change in Ethiopia የሚለው መፅሀፋቸውን ሳነብ ብዙ ፅሁፎቻቸውን የወሰዱት በወቅቱ እጅግ በጣም ተወዳጅ ከነበረው ብርሃን እና ሰላም ጋዜጣ ላይ ነበር ። በወቅቱ ኢትዮጵያ ውስጥ የነበሩ ምሁራን እንዴት ያስቡ ስለሀገር እንዴት ይመክሩ አቅጣጫ ያሳዩ እንደነበር በደንብ አድርገው አስፍረውታል ። ሌሎች ፀሀፊዎችም ከዛ ጉዳይ ላይ አርቲክል እየወሰዱ ሲፅፋ አይቻለው ።
ለኔ አዲስ ነገር ከ1928-1933 ከነበረው ጦርነት በፊት እጅግ በጣም ተራማጅ የሆኑትን ንጉስ በበላይ ጠባቂነት በሚያስተዳድሩት ብርሃንና ሰላም ጋዜጣ ከነበራት ቦታ እኩልና እንደውም ከዛም ከፍ ያለቦታ ይኖራታል ብዬ አስባለው ። በዛ አጭር ግዜ ቆይታዋ ውስጥ ያልዳሰሰችው ነገር የለም። በዚህ ሁላ ሂደት ውስጥ ታድያ የአንበሳውን ድርሻ የሚወስደው ዐብይ ተክለማርያም ነው ። መጀመሪያ መመስረቱ ሁለተኛ ያንን ቡድን ይዞ መቆየቱ ሶስተኛ ደግሞ አዳዲስ ሰዎች ወደዛ እንዲገቡ ማድረጉ አራተኛ እነዚህን የመሳሰሉ አዳዲስ የሆኑ እንደ ዘ ሰን ዋሽንግተን ፖስት ኢኮኖሚስት የመሳሰሉ ዓይነት የውጪ ጋዜጦች ላይ ያሉትን አይነት የአፃፃፍ ስልቶች በማምጣት ለኢትዮጵያዊያን ጋዜጠኞች አዲስ ትምህርት ያስተማረች ጋዜጣ ናት ። አጠቃላይ ለስርዓቱ ደግሞ በስርዓት ልንማር ብንችል ኖሮ ከብዙ ነገሮች እንድንጠበቅ ብዙ ነገሮች እንድንማር ሃሳቦችን እንድንወስድ ያደረገች ጋዜጣ ነበረች ። የሚፃፈው ፖሊሲ ጉዳዮች ላይ ነበር ። እማስታውሰው አዲስነገሮች ከሀገር ከወጡ በኋላ የወቅቱ ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ ሲጠየቁ አዲስነገርም አዲስ ዘመንም አንብቤ አላውቅም ብለው ነበር ። ነገር ግን የሁለት ምርጫዎች ወግ አቶ በረከት ስምኦን ሲፅፍ ጋዜጣዋ
ከፖለቲከኞች በላይ አጀንዳዎችን ታንሸራሽር እንደነበር ፅፏል ። ይህ የጋዜጣዋን ከፍታ ያሳያል ።ምክንያቱም የሥርዓቱን የመጨረሻ የፕሮፓጋንዲስት የሆነው ሰው ነው የተናገረው ።"
በተረፈ የዐቢይ ተክለማሪያም የሕይወት ታሪክ በተወዳጅ ሚድያ መሰነዱ ይበል የሚያሰኝ ነው፡፡
******
ዐብይ ተክለማሪያም፣ እኔና ዳንኤል
ከመኰንን ተሾመ
የተማሪነትና የጥናት ጓደኛዬ ዐቢይ ተክለማሪያም ልደቱ በይፋ ሊከበር ነው መባሉን ሰማሁ፡፡ ዐብይን የተዋወኩት 8ኛ ክፍል እያለሁ በጋራ ጓደኛችን እና አሁን በአሜሪካን ሀገር የተባበሩት መንግስታት መስሪያ ቤት የ IT ከፍተኛ ባለሙያ ሆኖ በሚሰራው አብሮ አደጌ ዳንኤል ብርሃኑ አማካኝነት ነበር፡፡ (በነገራችን ላይ በእኛ ዙሪያ የባከነ ሰው የለም) እናም የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች እያለን ሦስታችን ጎበዝ ብቻ ሳይሆን ከዚያ በላይ እጅግ ምርጥ ተማሪዎች ነበርን፡፡ የእኛ ላይብረሪ በአብዛኛው የገዳም ሰፈሩ የአራዳ ጊዮርጊስ ጓሮ ነበር፡፡
የአራዳ ጊዮርጊስ ጓሮና ጥናት
በየቀኑ በሚባል ደረጃ በጊዮርጊስ ጓሮ ባሉ ዘመን ጠገብ ዛፎች ስር ለረጅም ሰዓታት እናጠናለን ። ጥያቄ እንጠያየቃለን ፤ ማስታወሻ/note/ ወይም አጤሬራ እናወጣለን፡፡ እኔና ዳንኤል የሳይንስ ዐብይ ደግሞ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ነበርን፡፡
እናም ዐብይ የማህበራዊ ሳይንሶችን የሚረዳበትና የሚያስታውስበት መንገድ ተዓምር የሚያስብለን ነበር፡፡ ባለ ምጡቅ አዕምሮ መሆኑ በወቅቱ ለእኛ በጣም ግልጽ ነበር፡፡
ዐብይ ዝምተኛ፣ ትሁት፣አሰላሳይ እና ትልቅ ስብዕና ያለው መሆኑን ከልጅነቱ የሚያስታውቅ ልጅ ነበር፡፡
ቀለሜዎቹ
በዚያ በልጅነት ዘመን እኩዮቻችን በሌላ ቦታዎች ሲውሉ እኛ ነጋ ጠባ ደብተር ተሽክመን ዘጭ፥ዘጭ...ስንል የሰፈር ልጆች "ቀለሜ...ቀለሜ....'" እያሉ ሲያበሽቁን እኛ ስንረበሽ ዐብይ በተረጋጋ ስሜት የሚያረጋጋን ባለበሳል ስሜት ታዳጊ እንደነበረ አስታውሳለሁ፡፡.
ገዳም /አራዳ ሰፈር
እኔና ዳኒ የገዳም ሰፈር (08 ቀበሌ) ፥ ዐብይ ደግሞ ከ"ዳትስን" ሰፈር ከፍብሎ (ወ/ሮ ቀለመወርቅ ት/ቤት አካባቢ) /የ 09 ቀበሌ/ ወይም የአራዳ ልጆች ነን፡፡
የአራዳ ልጅነታችን ግን የሚገለፀው በእጅግ ጎበዝ ተማሪነት ፥ በመልካም ፀባይ እና በምሳሌነት ነበር፡፡
ዐብይ በተለይ በዛ እድሜው በልጅነት ብስለቱ / Emotional Intelligence/ የታወቀ ነበር፡፡
ዐብይ የሽምደዳው ንጉስ
ከደብተሩ ላይ ያጠናውን ነገር መልሰን ስንጠይቀው ያለማጋነን ሙሉ ደብተሩን ቃል ቃል መልሶ ይነግረን ነበር ፡፡
ዳንኤል ደግሞ በሳይንስ ትምህርቶች የቁጥር ቀመሮችን በመስራት አስደማሚ ችሎታ ነበረው፡፡ ዳንኤል እስከ 8ኛ ክፍል ገዳም ሰፈር ቤተልሔም ት/ቤት እኔ ደግሞ ኢትዮጵያ ትቅደም ት/ቤት ነው የተማርነው፡፡ ሁላችንም የደረጃ ተማሪዎች ነበርን፡፡ በእኔ በኩል ከ1-8 ክፍል በአብዛኛው ከክፍል ብቻ ሳይሆን ከሴክሽንም 1ኛ ነበር የምወጣው፡፡
በዚህ የዐብይን ብዙ አላስታውስም፡፡ በኋላ በ12ኛ ክፍል ከፍተኛ ውጤት ባልሳሳት 3.6 አምጥቶ የሶሻል ሳይንስ ተማሪ በመሆኑ 6 ኪሎ ዩኒቨርሲቲ ገብቶ የልጅነቱን ታሪክ በህግ ትምህርት ከፍተኛ ውጤት በማምጣት ደገመው፡፡
የህግና ትምህርትና የስፖርት ጋዜጠኝነት
ከምጡቅ የሕግ ተማሪነት ወደ ስፖርት ጋዜጠኝነት
በጣም የሚገርመኝ የዓብይ የሙያ ህይወት ለውጥ፡፡
ዛሬ
በዛ ዘመን ብቻም ሳይሆን አሁንም በዐብይ ደረጃ የህግ ትምህርት የተማረ ባለሙያ በሌለበት ሁኔታ ዐብይ ምን ነገር ጎትቶት ወደ ስፖርት ጋዜጠኛነት እንደገባ ይገርመኛል፡፡ በጋዜጠኝነት በአንድ ዘመን የሠራን ቢሆንም እኔና ዐብይ መንገድ ላይ ስንገናኝ ብቻ ሰላምታ እንቀያየራለን እንጂ በቁም ነገር ተገናኝተን አናውቅም፡፡ ለምን እንደሆነ አላውቅም፡፡ ከዚያ በኋላ ስለእርሱ የምሰማው በሩቁ ነው፡፡ ከዳንኤልን ጋር እንኳን አልፎ አልፎ ከአሜሪካ ሲመጣ ቡና እንጠጣለን፡፡ ሰሞኑን እንደውም እዛው አሜሪካ ከአንዱ የአሜሪካ ዩንቨርስቲ ልጁን ማስመረቁን በፌስ ቡክ አጋርቶን ደስ ብሎናል፡፡
አዲስ ነገር ጋዜጣ
ፖለቲካ ትንታኔ ፥ በረከት ስምኦን እና መስሪያ ቤቱ፥ የዊኪሊክስ መረጃ ፥ የአሜሪካው አምባሳደር፥ የነዓብይ ስደትና ሌሎቹንም ታሪኮች....... እመለስባቸዋለሁ።
*****
ስለ ዐቢይ ሔኖክ ስዩም
ዐቢይ ተክለማርያም የምቀናበት ሰው ነው። የህግ ሰው ስለሆነም ይሆናል መሰል ጥብስቅ ያለ የትንታኔ ጽሑፍ መክሊቱ ነው። አውቆ ስለመጻፍ ካነሳን ምሳሌ፣ ጽፎ ስለመግለጽ ከተናገርን ስሙን የምንጠራው ድንቅ ሰው። ዋጋ ባላቸው ቃላት የፃፋቸው ጥልቅ ትንታኔዎች ይደንቁኛል። መቆሟ ዛሬም አዲስ ነገር ሆኖ አልለመድ ወደአለን ዘመነ-አዲስ ነገር ስሄድ እነኛን የዐቢይ የትንታኔ ጽሑፎች እገረምባቸዋለሁ። እንዲህ ያለ ሰው እንደ ስጦታ እቆጥረዋለሁ። በእርግጥም እንኳን ተወለደ። መልካም ልደት።( ክፍል 3 ይቀጥላል)

Comments