የዓባይ ወንዝ ነገር ...
#ethiopia | ከቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተነስተናል። በካፒቴኖቹ ናሆም መስፍን ( ዋና አብራሪ) ፣ ጸጋዬ መንጌ እና ግሩም አስናቀ የሰማዩ ጢያራ ይዘው፣ በ 24 ሺህ ጫማ ከፍታ ነጉዱ። አየር ላይ - እፀገነት አማረ እና ኤዶም አሰፋ ሽር ብትን እያሉ በክብር አስተናገዱን።
ከ1 ሰዓት ከ አሥር ደቂቃ በረራ በኋላ የኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ አረፍን።
ወጭው
በጠዋቱ 30 ዲግሪ ሴንቲግሬድ የመቁት መጠን ያሳያል።
* * *
የኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ፤ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት፣ በመተከል ዞን፣ ቡአምዛ ቀበሌ፣ በጉባ ሲርቦ በለብያታና ነግሮ ተራሮች መካከል ይገኛል፡፡
ግድቡ ከኢትዮ ሱዳን ድንበር ከ20 እስከ 40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡
ከናይል ወንዝ መነሻ ምንጭ አንስቶ እስከ ግብጽ ሜዲትራንያን ዳርቻ ድረስ ‹‹የዓባይ ልጆች›› በድህነት ወለል የሚኖሩ ሕዝቦች ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሱዳን፣ ኬንያ፣ ታንዛኒያ፣ ኡጋንዳ፣ ቡሩንዲ፣ ሩዋንዳ፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎና ግብጽ በዓባይ ወንዝ እትብት የተሳሰሩ የአንድ ሥልጣኔ፤ የአንድ ወንዝ ልጆች ናቸው - የዓባይ ልጆች፡፡
ከዓባይ ወንዝ፤ ከኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ጋር ተያየን።
የዓባይ ወንዝ ከኢትዮጵያ ውሃውንና አፈሩን ጠራርጎ ያለማንም ከልካይ ለዘመናት መፍሰሱ ክፉኛ ያስቆጣቸው ገጣሚና ባለቅኔ ኃይሉ ገብረዮሐንስ (ገሞራው)፣ ወንዙን እንደሰው በስንኝ ‹‹እናትክን!›› ያሉት ትውስ አለኝ።
«እናትክን!» በሉልኝ
‹‹… ይፈሳል ይሉኛል፣ አባይ ዐይኑ ይፍሰስ
ያን ስንቱን ወገኔን የውሃ እጦት ሲያምስ
የድርቀት ጋንጩራ ሲበላ ስንቱን ነፍስ፣
ውሃ ውሃ እያለ ለጋው ሲቀነጠስ
ናይል አባያችን አለ ነበር ሲፈስ
ለፈፀመው ደባ ለሰራውም ግፉ
«እናትክን!» በሉልኝ በዚያ የምታልፉ …››
ገጣሚና ባለቅኔ ኃይሉ ገብረዮሐንስ (ገሞራው) ዓባይ በኩራት ሲገማሸር ዛሬ በተመለከቱት ብዬ ከልቤ፤ በክብር ተመኘሁ። የዘመናት ኡኡታ፤ የማንቂያ ደወል ድምፃቸው ይሰማኛል።
በኢትዮጵያ ሬዲዮ የሚሰረቀረቀው ዜማን ላስታውሳችሁ ...
ወንዞች ይገደቡ ይዋሉ ለልማት
በከንቱ ፈሰዋል ለብዙ ሺህ ዓመታት
ይውጡ ማዕድናት ለሀገራችን ጥቅም
ህዝቧም ታጥቆ ይስራ በተሻለው አቅም
ተነሳ ተራመድ ክንድህን አበርታ
ለሀገር ብልፅግና ለወገን መከታ
ሀ ሁ ኢትዮጵያ ትቅደም (2)
***
👉 ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ
* ከ13 ተርባይኖች 5,150 ሜጋዋት ያመነጫሉ
* እስካሁን ከ71 ቢሊየን ኪዩቢክ ሜትር በላይ ውሃ ይዟል። ቀሪውን 2.1 ቢሊየን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ በመጪዎቹ 7-10 ቀናት ውስጥ ይያዛል።
* በግድቡ የተያዘው ውሃ ወደኋላ ከ246 ኪሎ ሜትር በላይ ይተኛል።
* ኢትዮጵያ ገንብታ ባጠናቀቀችው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አማካኝነት ኃይል እያገኘች ትገኛለች።
* የኃይል ማመንጫ ግድቡ ነሐሴ 24/2017 ላይ 2530 ሜጋ ዋት በማመንጨት ኃይል መስጠት ችሏል።
* የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዋናው ግድብ በ1.8 ኪሎ ሜትር እርዝማኔና 145 ሜትር ከፍታ ተገንብቶ ተጠናቋል።
* በአጠቃላይ ከ10 ሚሊየን ኪዩቢክ ሜትር ያህል ኮንክሪት (RCC) ሙሌት ተካሂዷል።
* የግድቡ የስረኛው ክፍል 150 ሜትር ስፋት አለው። የላይኛው ክፍል ደግሞ 11 ሜትር ስፋት ሲኖረው ሁለት መኪኖችን ጎን ለጎን ማሳለፍ ይችላል።
* በግድቡ የውጨኛው ክፍል የሚታዩት የብረት አሸንዳዎች በግራ እና በቀኝ በኩል ላሉ ኃይል የሚያመነጩ ተርባይኖች ውኃ የሚተላለፍባቸው ሲሆን እያንዳንዳቸው 8.5 ሜትር ዲያሜትር ስፋት አላቸው። 300 ሜትር ኪዩብ በሰከንድ ማሳለፍ አቅም አላቸው።
* በግራ የኃይል ማመንጫ 7 ተርባይኖች፤ በቀኝ የኃይል ማመንጫ ደግሞ 6 ተርባይኖች ሙሉ ለሙሉ ተከላቸው ተጠናቋል። ከእነዚህ ተርባይኖች 5150 ሜጋ ዋት ኃይል ማመንጨት ይቻላል።
* ከዚህ ውስጥ 3ቱ የቅድመ ኃይል ተርባይኖች በመጠን አነስ ያሉ ሲሆን ቀሪዎቹ 10 ተርባይኖች እያንዳንዳቸው 400 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም አላቸው።
* ግድቡ ያመነጨው ኃይል በሁለት መስመሮች ማለትም በጣና በለስ አድርጎ በደብረ ማርቆስ እንደዚሁም በአሶሳ አድርጎ ወደ አዲስ አበባ ብሔራዊ የኃይል ቋት በመግባት ላይ ይገኛል።
* የሳድል ዳሙ ርዝመቱ 5.2 ኪሎ ሜትር እና 50 ሜትር ከፍታ ላይ ሆኖ ሙሉ ለሙሉ በ15 ሚሊየን ሜትሪክ ኪዩብ ድንጋይ የተሞላ ነው። የተያዘው ውሃ ሾልኮ እንዳያልፍ ከ30-40 ሴንቲ ሜትር ውፍረት ባለው ኮንክሪት ተለብጧል።
* የኮሬቻ (saddle dam) 74 ቢሊየን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ ለመያዝ ወይም የሚያመነጨውን 5150 ሜጋዋት ለማመንጨት የሚያስፈልገውን የውሃ መጠን ለመያዝ በጣም አስፈላጊ ነው። የኮሬቻ ግድብ (Saddle Dam) ከዋናው ግድብ በ15 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል።
***
ከአንጋፋው ገጣሚና ፀሐፌ ተውኔት ጌትነት እንየው ጋር ከታላቁ ህዳሴ ግድብ አናት ላይ ቆመናል።
ዛሬ እዚህ የተገኘነው ከዓባይ ወንዝ፣ ከኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ በተያያዘ በተለያዩ ሙያ የሠሩ ሙያተኞች በክብር መጋበዛችንን አስረድተውናል።
ጠሪ አክባሪ ይስጥልን።
በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ከሠራኋቸው በርካታ ዘጋቢ ፊልሞች ( Documentaries) መካከል "የዓባይ ልጆች" አንዱ ነበር። አቶ ዓባይ ምህረት፣ የስድስት ልጆች አባት ሲሆኑ፣ የሁሉም ልጆቻቸው ስም አወጣጥ ከዓባይ ወንዝ ጋር በቀጥታ የተቆራኘ ነው፡፡
‹‹የሰው ማንነቱ ከስሙ ይጀምራል›› ይላሉ - አቶ ዓባይ፡፡
ተፈራ ዓባይ
ስንታየሁ ዓባይ
ተናኘ ዓባይ
የግብፅ ሕይወት ዓባይ
ይገደብ ዓባይ
ይታያል ዓባይ።
‹‹የአባይን ወንዝ መሻገር የሚያስፈራው የውሃ ሙላቱ ብቻ አልነበረም፡፡ አደገኛውና ትልቁ የአዞ ዝርያ በአባይ ወንዝ ውስጥ ነው የሚገኘው፡፡ በአማካይ ከ6 እስከ 8 ሜትር ርዝመት ያለው እና የ‹‹ናይል አዞ›› በመባል የሚታወቀው እጅግ አደገኛ አዞ፤ (አረንጓዴ ቀለምና 360 ዲግሪ ማየት የሚችል ዓይን አለው)፡፡ የዓባይን ወንዝ የምንሻገረው በድልድይ አልነበረም፡፡ የዓባይ ወንዝ ዋናተኞች ሰውንም፣ ከብቱንም፣ ዕቃውንም በበሬ ቁርበት አዝለው ነበር። በውሃ ሙላትና በአዞ ጥቃት እየራዱና እየፈሩ የሚያሻግሩት››
ነበር ...
ትናንት።
***
"የዓባይ ልጅ ነኝ እኔ--"
ይኸው በአዲስ ዘመን አዲስ ቃል ዘመረ
ከራሱ ታረቀ ካፈሩ መከረ
ለሀገሩ ቆመ በሀገሩ አደረ
ዜማና ቅኝቱ ረገደ ምቱ
ከጊዜ ከትውልድ ከሀቅ ሰመረ
ሃገርን ባንድ ነዶ ባንድ ልብ አሰረ
ይኸው ካይናችን ስር ከእውነት የነጠረ ከእምነት የጠጠረ
ዓባይ ሃረግ ሆነ ከደም የወፈረ፡
የአንድ ወንዝ ልጅ ሁሉ ይህን የዓባይ ሀረግ ከእምነትህ ጋር ቋጥረህ
ከጋራ አንገት መድፋት ከጋራ መሳቀቅ ከጋራ አፍረት ወጥተህ
በያለህበቱ በየዓለማቱ ጥግ በአንተነትህ ኮርተህ
አንተ ማነህ ሲሉህ
ከወዴት ነህ ሲሉህ
በሙሉ ራስነት አንገትህን አቅንተህ
ድምጽህን ከፍ አድርገህ
ደረትህን ነፍተህ
የዓባይ ልጅ ነኝ እኔ
ጦቢያ ናት ሀገሬ በል አፍህን ሞልተህ…
-ገጣሚ ጌትነት እንየው-
***
ዛሬ
ታሪክ ተቀየረ።
ንጋት ሐይቅ ላይ ቆመናል።
ሁሉም ኢትዮጵያዊ፤ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ( በሀገር ውስጥ በባህር ማዶ) ያሉ ሁሉ "ህዳሴ"ን -"ንጋት"ን እንዲመለከቱ ጉዞ መመቻቸት ይኖርበታል።
ማየት ማመን ነው!
ማየት ኩራት ነው!
እናንት ያገሬ ልጆች
ኑ
የሥራ፤ ሕያው ሐውልታችሁን መርቁ
#ታላቁየኢትዮጵያህዳሴግድብ #dam #ethiopiandam

11 months ago