Logo
FIDEL POST NEWS
በቻይና ልጆቹ እንዳልሆኑ በምርመራ የተራጋገጠ ሰው ላሳደኩበት 6 ሚልየን ብር የቀድሞ ሚስቱ ካሳ ትክፈለኝ አለ

የ45 አመቱ የቻይናው የሻንዶንግ ግዛት ነዋሪ የሆነው ጂያንግ ሆንግታኦ በቀድሞ ባለቤቱ ላይ ክስ መስርቷል። ከቀድሞ ባለቤቱ የ300,000 ዩዋን (ወደ 6 ሚልየን ብር የሚጠጋ) እንዲመለስለት ጠይቋል።

የካሳው ገንዘቡ የጠየቀው ልጆቹን ለማሳደግና ለማስተማር ላዋለበት እንደሆነ ተናግሯል።

ጂያንግ በ2002 ዓ.ም. ተጋባ። የመጀመሪያ ልጁ በፈረንጆቹ 2004 እና ሁለተኛ ልጁ በ2014 ተወለዱ። ይሁን እንጂ በሚስቱ ተደጋጋሚ መቅረት እና በተለያዩ ችግሮች ምክንያት በ2022 ተፋተዋል።

በዚያን ጊዜ የጂያንግ ንብረት በሙሉ ወደ ቀድሞ ሚስቱ ሄደ። ጂያንግ አንድ መኪና ብቻ ቀረው።

ባለፈው አመት መስከረም ወር ላይ አዲስ ትዳር መስርቷል። ከዚያ በኋላ፣ የቀድሞ ሚስቱ እና ሁለቱ ልጆቹ ንብረቱን ለመጠየቅ ሲመጡ፣ ትልቁ ልጁ ሩንዠ በቤተሰብ አለመግባባት ወቅት አካላዊ ጥቃት ሰንዝሮበት “አባቴ አይደለህም” ሲል ጮኸ። ይህ ጂያንግን ለጥርጣሬ አነሳሳው። በኋላም የሩንዠን የጥርስ ብሩሽ ሰብስቦ ለዲኤንኤ ምርመራ አደረገ። የምርመራው ዘገባም በመካከላቸው ባዮሎጂያዊ ግንኙነት እንደሌለ አሳይቷል።

ከዚያ በኋላ፣ የትንሹ ልጅ የዲኤንኤ ምርመራ እንዲሁ ተመሳሳይ ውጤት አስገኘ። ጂያንግ የትልቁ ልጅ አባት የመንደሩ ጸሐፊ ሲሆኑ የትንሹ ልጅ አባት ደግሞ የአጎቱ ልጅ ነው ብሏል። ደንግጦም “የቀድሞ ሚስቴ ክፉኛ ጎድታኛለች” ሲል ተናግሯል። የጂያንግ ወላጆችም “ከሃያ ዓመታት በላይ እንደ የልጅ ልጆች ያሳደግናቸው በእርግጥም ደማችን አይደሉም” ብለዋል።

ክስተቱ በቻይና ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ከፍተኛ ክርክር አስነስቷል። ስለ ክስተቱ የወጡ ጽሁፎች ከ30 ሚሊዮን ጊዜ በላይ ታይተዋል።
11 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.