በ2017 በጀት አመት ከአትክልትና ፍራፍሬ ሽያጭ የተገኘው ገቢ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ጭማሪ ማሳየቱ ተነገረ
#ethiopia | በተጠናቀቀው የ2017 በጀት አመት ከሆርቲካልቸር ዘርፍ ከአትክልትና ፍራፍሬ ወጪ ንግድ ጥሩ ገቢ መገኘቱን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።
በሚኒስቴሩ የዓለም አቀፍ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ተስፋዬ ታደሰ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት በበጀት አመቱ 282 ሺህ 159 ነጥብ 67 ሜትሪክ ቶን የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶችን በመላክ 100 ሚሊዮን 36 ሺህ 140 የአሜሪካን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ ነበር።
በዚህም 190 ሺህ 454 ነጥብ 89 ሜትሪክ ቶን ምርትን ለውጪ ገበያ በመላክ 74 ሚሊዮን 939 ሺህ 820 የአሜሪካን ዶላር ተገኝቷል ነው ያሉት፡፡
ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ክንውን ጋር ሲነፃጸር በመጠን የ 4 ነጥብ 19 በመቶ በገቢ ደግሞ የ 19 በመቶ ጭማሪ እንዳለው
የአለም አቀፍ ግንኙነት ባለሙያው ጨምረው ለጣቢያችን ተናግረዋል።
የአትክልት ኤክስፖርት መዳረሻ ሀገራት ከተባሉት መካከል ሶማሊያ፣ ጂቡቲ እና ኔዘርላንድስ ተጠቃሽ ሲሆኑ ሳውዲ አረቢያ፣ ጂቡቲ እና ሶማሊያ ደግሞ የፍራፍሬ ምርት መዳረሻ ከሆኑት መካከል ይገኙበታል ሲል ዳጉ ጆርናል ዘግቧል።

11 months ago