ተስፋዬ እሸቱ (ረ/ፕሮፌሰር)
ከሲያትል፣ አሜሪካ 🇺🇸
#ethiopia | አሜሪካኖቹ እንድ ጉዳይ ላይ እሴት ጨምረው፣ አሳድገው የሚሸጡበት መንገድ ይገርመኛል!
የተነሳሁት ከሳን ሆዜ፣ ካሊፎርኒያ ነው፡፡ ከሁለት ሰአት በረራ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ እግሬ ሲያትልን ረገጠ፡፡ ከቀለል ያለ መደነባበር በኋላ ከጓደኛ ጋር ተገናኘን፡፡ ወደ ቤቱ ወሰደኝ፡፡ አገሬ እንዳለሁ እንዲሰማኝ ያስቻለ ምሳ ቤቱ ጋበዘኝ፡፡ ምሳው “ነብር ዥንጉርጉርነቱን፣ ኢትዮዽያዊ መልኩን ይቀይር ዘንድ ይቻለዋልንʔ“ የሚሉትን ብሂል አረጋገጠልኝ፡፡ ከምሳው በኋላ “ምን ማየት ትፈልጋለህ“ አለኝ፡፡ ከዚህ ቀደም ስለሲያትል ምንም አይነት መረጃ ስላልነበረኝ “እኔ እንጃ“ አልኩት፡፡ ከቤት ይዞኝ ወጣ፡፡ መኪና ውስጥ ገባን፡፡ ብቻ ዙሪያ ገባውን እንደ ሞኝ እያየሁም፣ እየተደነቁም ሳልጨርስ ያሰበው ቦታ ደረስን፡፡
ከፊት ለፊቴ “wings over Washington A flying Ride“ የሚል ማስታወቂያ አነበብኩ፡፡ “ምንድን ነው አልኩት“
“ሲያትል የገባ ቱሪስት ማየት የሚፈልጋቸውን የቱሪስት ቦታዎች ቀድሞ በ3ዲ የሚያይበትና ማየት የሚፈልገውን የሚመርጥበት ቦታ ነው“ አለኝ፡፡ የሆነ ጨለማ ክፍል ውስጥ አስገቡን፡፡ ትዕይንቱ ተጀመረ፡፡ በጣም በሚገርም የ3ዲ ቴክኖሎጅ ሲያትል ውስጥ መታየት ያለባቸውን ቦታዎች አየናቸው፡፡ መቸም ትዕይንቱ ድንቅ ነበር፡፡
“አሁን ካየሀቸው የቱን ቦታው ድረስ ማየት ትፈልጋለህ“ አለኝ፡፡ ሁለት ቦታ መረጥኩ፤ ተያይዘን ሄድን፤ ጎበኘኋቸውም፡፡
እውነትም አሜሪካኖቹ ምንም ነገር ላይ እሴት ጨምረውበት መሸጥ እንደሚችሉ በአይኔ በብረቱ አየሁ፡፡ ጉዳዩን ዘርዘር ለማረግ ልሞክር፡፡
የጉብኝቴ አንዱ መዳረሻ “Space Needle“ ነበር፡፡ በእ.ኤ.አ በ1960 አካባቢ የታነጸው ይህ ሽንጣም ማማ (Tower )መሳይ ነገር ቁመቱ 184 ሜትር ነው፡፡ ማማው ጫፍ ለመድረስ ከአርባ ሰከንድ በላይ አይወስድባችሁም፡፡ ጫፉ ላይ ስትደርሱ 360 ዲግሪ በሚሽከረከርና በመስታውት ከተሰራ ወለል ላይ ቆማችሁ የተንጣለለውን የሲያትል ከተማ ታያላችሁ፡፡ በግርድፉ ማማው ይህንን ይመስላል፤ አለቀ።
አሜሪካኖቹ ግን አሪፍ አይደሉ ይህንን ማማ እሴት ጨምረውበት፣ ማማ ሳይሆን ሌላ ነገር የምትጎበኙ እንዲመስላችሁ አድርገው የሚሸጡበት መንገድ በቃላት ለመግለጽ ይከብዳል፡፡
ጉዳዩን ከሆነ የማማ ጉበኝት አስወጥተውታል፡፡ ማማውን የከተማው ውድ መለያ ጌጥ አድርገውታል፡፡ ሲያትል ሲባል ማማው አእምሮህ ውስጥ እንዲቀመጥ ብቻ አላደረጉም፡፡ ማማውን ለመጎብኘት በውዴታ ትከፍላለህ፡፡ ወረፋ ተሎ እንዲደርስህ ከፈለክ አሁንም ትከፍላለህ፡፡ 184 ሜትር ወደ ላይ ወጥትህ ስትጨርስ ሬስቶራንት አለ፡፡
እየበላህ ፎቶ መነሳት ትፈልጋለህ፡፡ ለዚህም ትከፍላለህ፡፡ ጉብኝትህን ጨርሰህ ስትወርድ “ትዝታየን በምን ላስቀርʔ“ ካልህ ማማውን በአሻንጉት መሳይ ነገር፣ በቲሸርት፣ በኮፍያ ብቻ በሆነ ሳቢ፣ አጓጊና እንዲኖርህ በምትፈልገው ነገር ላይ አትመውልሀል፡፡ ሲለዚህ ተገደህ ሳይሆን ፈልገህ ትገዛለህ፡፡ መስተንግዷቸው ደጋግመህ እንድትጎበኘው ይጋብዝሀል፡፡
በአጠቃላይ ጉዳዩን ከተራ የማማ ጉብኝት አውጥተው እሴት ስለጨመሩበትና የከተማው መገለጫ ስላደረጉት እግሩ ሲያትልን የረገጠ ሁሉ እንዲጎበኘው በውዴታ ይገደዳል፡፡ መሸጥ ይሉሀል ይሄ ነው፡፡
ሁለተኛው የጭብጤ አስረጅ “The Museum of Flight“ እየተባለ የሚጠራው ሚዚየም ነው፡፡ ይህ ሚዚየም በአለማችን ግዙፉ የአየርና የስፔስ ሚዚየም በመሆኑ ሲጎበኝ ይኖራል፡፡ ዋናው ጥያቄ እንዴት ግዙፍ ሚዚየም አደርግው በሚገርም ሁኔታ የጎብኝን ልብ ያማልሉበታል የሚለው ነው፡፡
በዚህ ሚዚየም የ“አቬሽን“ ታሪክ በዜማ ይተረካል፡፡ 175 ገደማ የሚሆኑ፣ ከጥንት እስካሁን ያገለገሉና ከየዘመኑ የተሰበሰቡ አውሮፕላኖችን ይገኙበታል፤ እየተደመምክም ትጎበኛለህ፡፡
በመጀመሪያውና ሁለተኛው የአለም ጦርነቶች የተሳተፉ አውሮፕላኖችን ከነታሪካቸው ሰንዶ ማስቀመጥ ሳይሆን ለዛሬ እንዲሰራ እሴት ጨምረውበት ያስደምሙሀል፡፡
የግዙፉን የቦይንግ ካምፓኒ ታሪክ ያስጎበኙሀል፡፡ በታሪክ የምናውቀውና ከአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች መካካል ኬነዲ የተጓጓዘበትን “ኤር ፎርስ ዋን“ አውሮፕላንን ማየት ብቻ ሳይሆን የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የሆንክ ያህል እስኪሰማህ ድረስ ውስጡ ትምነሸነሽበታለህ፡፡
ታሪክን መተረክ አንደ ነገር ነው፣ እሴት ጨምሮ መሸጥ ደግሞ ሌላ ነገር ነው፡፡ እነርሱ አባቴ መተረክ ብቻ ሳይሆን እሴት ጨምረው ለአለም ገቢያ ሲያቀርቡት ታያለህ፡፡
ያለፈን ታሪክ ዘመኑ ከሚፈልገው የቴክኖሎጅ አስተሳሰብ ጋር ሰፍተውታል፡፡ ይሄንን ነው እንግዲህ እሴት መጨመር የምንለው፡፡ ለምሳሌ በመጀመሪያውና በሁለተኛው የአለም ጦርነቶች የተሳተፉ አውሮፕላኖችን ጊዜው ከደረሰበት የድምጽና የእይታ ግብአት ጋር አስማምተው ስለሚያስጎበኙህ በጊዜው የነበርክ ያህል ይሰማሀል፡፡ ሌላው ሚዚየሙን በሁሉም የእድሜ ክልል ያሉ ጎብኝዎች እንዲረዱት ያደረጉበት መንገድ ከቃል በላይ ነው፡፡
አሁንም ሚዚየሙን ጎብኝተህ ብቻ መውጣት የማይታሰብ ነው፡፡ መውጫ በሩ ላይ ሚዚየሙን የሚገልጹና ትዝታህን ለተቀረው አለም እንድታስረዳ የሚያስችሉ በርካታ ነገሮች ተኮልኩለው ታገኛህል፡፡ ልትቋቋማቸው አትችልም፡፡ ሌላው ቢቀር እንደኔ ችስታ ከሆንክ የቁልፍ ማንጠልጠያ ትገዛለህ፡፡ ኪስህ መግባት ነው ሚቀራቸው፡፡ ፈገግ እያልክ እየተደሰትክ ትገዛለህ፡፡
እና ይሄ ሁሉ ምን ለማለት ነው….
አንድ፣ በአገራችን በተለመደው መንገድ ሚዚየሞቻችን የምናስጎበኝበትና ገንዘብ የምንሰበስብበት መንገድ እንደገና ሊጤን ይገባዋል፡፡ ከሚዚየሞቻችን ትርጉም ፈልቅቆ፣ እሴትም አክሎ ለአለም ገበያ ማውል ተገቢ ነው፡፡ ዘመኑ ከሚፈልገው የቴክኖሎጅ ስርአት ጋር ጉብኝቱን ማስተሳሰር ያስፈልጋልም የሚል እምነት አለኝ፡፡
ሁለት፣ ታሪካችንንስ እንዴት ለአለም ገበያ እናብቃው የሚለውም ሊታሰብበት የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡፡ ለምሳሌ ታላቁን የአድዋን ድል በአመት አንዴ ብቻ እየዘከሩ ማለፍ የሚያዛልቅ አልመሰለኝም፡፡ እድዋን ለአለም ህዝብ እንዴት እንሸጠው የሚለው ልዩ ትኩረት የሚፈልግም ይመስለኛል፡፡
መልካም ጊዜ!

12 months ago