Logo
YenetaTube
አቤት እንደአንዳዶቻችሁ ቢሆን ትላንት ነበር በአደባባይ የምሰቀለው 🙆🏽‍♀️

አሁን የምፅፍላችሁ ከእናንተ ጋር መልስ ለመመላለስ ሳይሆን፤ እንድታውቁት የምፈልገው ነገር ስላለ ነው፤ እኔ ዘፋኝ ነኝ፤ አምኜ ተቀብየው ብዙ ቤተሰብ የማስተዳድርበት የተከበረ ሞያዬ ነው፤ ማንም አቁሚ ብሎኝ የማቆመው ሳይሆን እሱ በቸርነቱ በቃሽ ሲለኝ የማቆመው ጉዳይ ነው የዛኔ እንኳን ሙያዬን፤ ዓለምን ክጄም ልመንን እችላለሁ፤
እኔ እና ፈጣሪ ያለንን ንግግር ሰምታችሁ አታውቁም፤ እኔ እምነቴ ላይ ያለኝን ጥንካሬም አታውቁም፤ ሁሌ ፈጣሪዬን ተንበርክኬ የምጠይቀውን ጥያቄም አታውቁም፤ ጌታችን መድሀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ምድር ላይ እያለ እኮ ውሎው ከፃድቃን ጋር አልነበረም፤ ልክ እንደ አንዳንዶቹ ምን ሁኖ ነው ከሀፅያን ጋር የሚውለው ጥያቄያቸውም ነበር፤

የእመቤቴን የቅድስት ድንግል ማርያም ንቅሳት መነቀስ የዘመናት ህልሜ ነበር ማለት፤ መነቀስ አቅቶኝ ነበር ማለት ሳይሆን ልነቀሳት ወይስ አልነቀሳት የሚለው ጥያቄ ውስጥ ለዘመናት ነበርኩ ማለት ነው፤ መነቀሴ ልክ ነበር በጣም ደስተኛም ነኝ፤ የትም ብሆን ድሮም አብራኝ ነች አሁን ደግም በይበልጥ ይሰማኛል፤ (አንዳንዶቻችሁ) ልታደርግ ትችላለች ብላችሁ ያሰባችዋቸው አፀያፊ ተግባሮች፤ ትላንት ከእናንተ ገና ሰማሁት፤ እንምታስቡትም በዚ ልክ የወረድኩ ሴት አይደለሁም፤ ልኬን የማቅ ነኝ አሁን ደግሞ በይበልጥ ራሴን እንዳከብር እና ከብዙ ነገር እንድቆጠብ ትረዳኛለች፤ ለሰው እማ ቢሆን አልነቀሳትም ነበር፤

ማንም ምንም ቢል፤ እሷን በመነቀሴ ደስተኛ ነኝ ድሮም አብራኝ ነች አሁን ደግሞ በተለየ ❤️
Veronica Ada me

12 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.