"ለሱማሌላንድ እዉቅና ለመስጠት አስበናል" ! /ትራምፕ/
ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ዩኤስ ለሶማሊላንድ የሉአላዊነት ነፃነቷን እና እውቅና ለመስጠት ፍላጎት እንዳላት መግለፃቸው ተነገረ።
ፕሬዝዳንቱ ይህንን ያሉት ቅዳሜ እለት የረጅም ጊዜ ተቀናቃኞች ሆነው የቆዩትን በአዘርባጃን እና በአርሜኒያ መሪዎች መካከል የሰላም ስምምነት እያፈራረሙ በነበሩበት ወቅት ስለ ጉዳዩ ተጠይቀው ለጋዜጠኞች ምላሽ በሰጡበት ወቅት ነዉ።
ጋዜጠኞች ክቡር ፕሬዘዳንት ለረጂም አመታት የሀገርነት ጥያቄ እየጠየቀች የምትገኘዉ የሱማሌላንድ ጉዳይ እንዴት ያዩታል ? የሚል ጥያቄ ሲመልሱ
"ጥሩ ጥያቄ ነዉ "አሁን ለሶማሊላንድ እዉቅና የምንሰጥበትን መንገድ እየተመለከትን ነው. በእውነቱ ጉዳዩ ውስብስብ ቢሆንም ነገር ግን በዛ ላይ አሁን እየሰራን ነው" በማለት ትረምፕ ምላሽ ሰጥተዋል ።
ይህ የትራምፕ ንግግር ለአለም አቀፍ እውቅና ለማግኘት እየሞከሩ የሚገኙት የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት አብዲራህማን መሀመድ አብዲላሂ ኢሪን ለዩኤስ ስትራቴጂካዊ የወደብ ከተማ በርበራ ወታደራዊ ሰፈር እንዲሰጥ እና ሊቲየምን ጨምሮ ጠቃሚ የማዕድን ሃብቶችን እንዲያገኙ ያቀረቡትን ሀሳብ ተከትሎ ነው።
ፕሬዝዳንት ኢርሮ ከብሉምበርግ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ሶማሊላንድ ከሁለቱም የዩኤስ የመከላከያ ሚኒስቴር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር "ጥሩ ግንኙነት" ገንብታለች፣ ይህም በራስዋ ራሷን በምታወጀው ሪፐብሊክ እና በዋሽንግተን መካከል ያለው ግንኙነት እያደገ መሆኑን ያሳያል። ብለዋል ።
ኢርሮ ትራምፕን አስተዳደራቸው በቅርበት መስራት የሚችሉበት “ቢዝነስ-አስተሳሰብ” መሪ ሲሉ ገልጸው አሜሪካ ለሶማሌላንድ እውቅና በመስጠት የመጀመሪያዋ ሀገር እንደምትሆን ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።
እ.ኤ.አ. በ1991 ጀምሮ ሶማሊላንድ ከሶማሊያ የተነጠለች ሉአላዊነት ሀገር እንደሆነች ብትናገርም በየትኛውም ሀገር እውቅና ሳታገኝ ቆይታለች ።
ከጥቂት ወራት በፊት በሶማሊያ የአሜሪካ አምባሳደር ለሶማሊላንድ እውቅና መስጠቱ በዋሽንግተን እና በሞቃዲሾ መካከል ያለውን ግንኙነት ሊያሻክር እንደሚችል በማስጠንቀቅ ዩኤስ በጉዳዩ ላይ የሚያደርጉትን ውይይት እንድታቆም ማሳሰቡ ይታወሳል ።
በዚህ መልክ የቆየዉ የሱማሌላንድ ጉዳይ ዳግም ወደ መድረኩ ተመልሶ የዩኤስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እዉቅና የመስጠት ሃሳብ እንዳላቸው መናገራቸውን ምናልባት ሀገር የመሆኗ ጉዳይ አይቀሬ መሆኑ ማሳያ ተደርጓል ።
ምክንያቱም በስልጣን ላይ ያሉ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ስለ ሶማሌላንድ "እዉቅና መስጠት "ጉዳይ በይፋ ለመገናኛ ብዙሃን ሲናገሩ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ። ተብሏል ።
ለዘገባው ታይም ኦፍ እስራኤል TRT GLOBAL አልጀዚራን ተጠቅመናል ።
የኔታ ቲዩብ ዘጋቢ ፦ ታዴ የማመይ ልጅ

12 months ago