ሁቲዎች የቀይባህር ቀጠና እያመሱት ነዉ !
/ሂዩማን ራይትስ/
የየመን የሁቲ ቡድን በቀይ ባህር በሚንቀሳቀሱ መርከቦች ላይ በሚያደርሰው ጥቃት ምክንያት በምስራቅ አፍሪካ እና የአረብ ባሕረ ገብ መሬት ለሚገኙ በተፈጥሮና ሰዉ ሰራሽ ችግሮች ለተጋለጡ ወገኖች የሚያስፈልግ ወሳኝ ዕርዳታዎችን ማድረስ ከባድ እየሆነ መምጣቱ ተነገረ ።
ቀይ ባህር ከዚህ ቀደም ከ12 በመቶ በላይ የአለም ንግድን ይዞ የነበረ ቢሆንም የሃውቲ ጥቃቶች ካገረሹ በኋላ የመርከብ እንቅስቃሴው በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል። የምስራቅ አፍሪካ ላኪዎች የጭነት ወጪ በሶስት እጥፍ ጨምሯል ፣በአካባቢው በሚያልፉ መርከቦች ላይ ያለው የኢንሹራንስ አረቦን ከእጥፍ በላይ ጨምሯል። የሶማሊያ ወደ ውጭ የሚላከው ከበርበራ እና ቦሳሳሶ ወደቦች በተለይም በቀላሉ ሊበላሹ ለሚችሉ እንደ ከብቶች እና ለባህረ ሰላጤው ለሚገቡ ምርቶች ተጋላጭ እየሆነ መጥቷል። ሲል ሂዉማን ራይትስ ገልጿል ።
ከህዳር 2023 ጀምሮ ሁቲዎች በጋዛ ከሚገኙ ፍልስጤማውያን ጋር ተባብረው እንደሚሰሩ በመግለጽ በክልሉ በሚገኙ የንግድ መርከቦች ላይ ከ100 በላይ ጥቃቶችን ፈፅመዋል ።
ባሳለፈዉ ወር ብቻ በግሪክ ኩባንያ የሚተዳደርና ሌሎች መርከቦች በተመሳሳይ ሳምንት ውስጥ ኢላማ ተደርገዋል ያለዉ ተቋሙ ይህም በቀይ ባህር የባህር ላይ የጸጥታ ችግር ላይ ስጋት እንዲፈጠር ማድረጉን ገልጿል ።
እ.ኤ.አ. ጁላይ 28 MV Eternity C የተሰኘውና ከሶማሊያ ሰብአዊ ርዳታ የምታጓጉዝ መርከብ በበርበራ ለተባበሩት መንግስታት የዓለም የምግብ ፕሮግራም (WFP) የምግብ አቅርቦቶችን ካደረሰች በኋላ ወደ ሳዑዲ አረቢያ ጂዳህ ስትሄድ ኢላማ በማድረግ በመን የባህር ጠረፍ አቅራቢያ ማስጠሙንና ዘጠኝ ፊሊፒናውያን እና አንድ ሩሲያዊ ኤሌክትሪክ ሠራተኛን ማገቱን በመግለፅ አዉግዟል ።
ሂዩማን ራይትስ ዎች መርከቧ ወታደራዊ ስጋት እንዳላት ወይም ከእስራኤል ጋር ግንኙነት እንዳላት ምንም አይነት ማስረጃ እንደሌለ በመግለጽ ፊልሙን አውግዟል፣ ጥቃቱን እና የግዳጅ ኑዛዜዎችን “ከጦርነት ወንጀል ጋር የሚያያዝ” ሲል ጠርቷል።
የምግብ ዕርዳታ የሚያደርሱ ሲቪል መርከበኞች ያለምክንያት መታሰር ሕገወጥ እና ከሥነ ምግባር አኳያም የሚያስወቅስ ነው ሲል ሂውማን ራይትስ ዎች በመግለጫው ገልጿል።
ዩናይትድ ስቴትስ፣ የአውሮጳ ህብረት ወታደራዊ ሃይል ኦፕሬሽን አስፒድስ እና አለም አቀፍ እውቅና ያለው የየመን መንግስት ሁቲዎችን ለጥቃቱ ተጠያቂ በማድረግ የታፈኑት መርከበኞች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ ጠይቀዋል።
የኔታ ቲዩብ ዘጋቢ ፦ ታዴ የማመይ ልጅ

1 year ago