Logo
YenetaTube
በኢብራሂም ትራኦሬ ላይ አፈሙዝ አነሱበት !

‎የአልቃይዳ ቅርንጫፍ የሆነው ጀማአት ኑስራት አል ኢስላም ዋል ሙስሊም (ጄኒም) በሰሜናዊ ቡርኪናፋሶ በሚገኝ ወታደራዊ ካምፕ ላይ በታጣቂዎች በተፈፀመ ጥቃት 50 የሚጠጉ ወታደሮች መሞታቸውን የማህበረሰብ መሪ እና ነዋሪዎች ተናገሩ ።

‎እንደዘገባው ከሆነ ይህን ጥቃት በምዕራብ አፍሪካ ዙሪያ ጥቃቶችን ከሚፈጽሙ በርካታ የታጠቁ ቡድኖች አንዱ የሆነው JNIM ናስር አል እስላም ዋል ቡድን እንደፈፀሙት ተገልጿል ።

‎ለዘመናት በመፈንቅለ መንግስት ስትናጥ የቆየችው ቡርኪናፋሶ የወታደራዊው መሪ ኢብራሂም ትራኦሬ ከመጣ በኋላ የተሻለ እድገትና ለዉጥ የፖለቲካ እና የወታደራዊ አጋሮችን እንደገና ቢያደርግም JNIM እስላማዊ ቡድኖችን መቆጣጠር አልቻለም ያለዉ የአሶሽት ፕረስ ዘገባ ሁለቱ ምንጮች በመጥቀስ በሰራው ዜና ቡድኑ የምዕራብ አፍሪካ ሰሜናዊ ክልል ዳርጎ በሚገኘው ቦልሳ ግዛት ሰኞ ላይ በፈፀመው ጥቃት 100 የሚጠጉ ታጣቂዎች መሣተፋቸውን እና ታጣቂዎቹ ግድያው ከተፈፀሙ በኋላ ተቋማትን አቃጥለው ዘርፈዋል። ብሏል ።

‎በምዕራባውያን አስተባባሪነትና አስታጣቂነት ቡርኪናፋሶ አብዛኛዉን የሀገሪቱን ክፍል በተለይም ከመዲናይቱ ዉጭ ጥቃቶች ተበራክተዋል በንፁሃን ላይም የታጣቂ ቡድኖች ጥቃት እየደረሰ ነዉ።ሲል አክሏል አሶሼትድ ፕሬስ ።

‎በማሊ ቡርኪናፋሶ አካባቢ የሚገኘው የአልቃይዳ ቅርንጫፍ የሆነው ጀማአት ኑስራት አል ኢስላም ዋል ሙስሊም (ጄኒም) በኦፊሴላዊው የሚዲያ አካል አዝ-ዛላካ በኩል ባሰፈረው መረጃዎች የሳህል አካባቢ እስላማዊ መንግስት የመመስረት አላማ እንዳለው ከድህረገፁ ያገኘነው መረጃ ያሳያል ።

‎የኔታ ቲዩብ ዘጋቢ ፦ ታዴ የማመይ ልጅ


10 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.