Logo
FIDEL POST NEWS
የተከፈለ ካፒታላቸውን አምስት ቢሊዮን ብር ማድረስ ያልቻሉ የግል ባንኮችን በአስገዳጅነት እንዲዋሃዱ የሚያደርግ በመሆኑ ባንኮች እንዲዘጋጁ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክምክትል ገዥ አሳሰቡ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥ አቶ ሰለሞን ደስታ ሰሞኑን በተካሄደው የኢትዮጵያ ፋይናንስ ሪፎርም ላይ በግልጽ እንደተናገሩት፣ ባንኮች በተቀመጠላቸው ጊዜ የተከፈለ ካፒታላቸውን አምስት ቢሊዮን ብር ካላደረሱ፣ ብሔራዊ ባንክበቀጥታ እንዲዋሃዱ አስገዳጅ ዕርምርጃ ይወስዳል፡፡

የሚጠበቀውን ካፒታል እንዲያሟሉ እ.ኤ.አ. 2026 ድረስ ቀነ ገድብ የተቀመጠ መሆኑን ያመለከቱት ምክትል ገዥው፣ ‹‹ባንኮችን እባካችሁ ብለን አንለምንም፣ ይህንን ታሳቢ በማድረግ ሊዘጋጁ ይገባል፤›› ብለዋል፡፡

ወደ ውህደት እንዲገቡ የሚገደዱት ባንኮች ማን ከማን ጋርይዋሃዳሉ? የሚለውም ውሳኔ የሚሰጠው ከብሔራዊ ባንክእንደሚሆን ጠቁመዋል፡፡

Via Reporter Newspaper
11 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.