Logo
Getu Temesgen
በዲ/ን ያረጋል አበጋዝ

ሰዎች በአጠቃላይ በተለይም ደግሞ በዘመናችን ያሉ ወጣቶች ለልዩ ልዩ ተጽዕኖዎች ከመጋለጣቸው የተነሣ የተለያዩ ጥያቄዎች በአእምሯቸው ይመላለሳሉ።

በተለይም እንዲህ የሚሉት ጥያቄዎች ከብዙ ወጣቶች በተደጋጋሚ ይሰማሉ፡- እውነት ያለው በኦርቶዶክስ ክርስትና ውስጥ መሆኑን እንዴት እርግጠኛ መሆን እንችላለን? ሰው በተወለደበት ማኅበረሰብ ባገኘው እምነት ወደ እውነትና ዘለዓለማዊ ሕይወት መድረስ አይችልምን? በሁሉም ሃይማኖት ውስጥ ያለው አስተምህሮና መዳረሻስ አንድ አይደለምን?

በሂንዱይዝም ውስጥ አሉ የሚባሉት ታላላቅ ሰዎች (ጉሩዎች) የሚያደርጓቸው አስገራሚ ነገሮች ከእግዚአብሔር ኃይል የተገኙ አይደሉም ማለት እንዴት ይቻላል? ዮጋ የሚባለው የተመስጦ ልምምድስ ከሃይማኖት ጋር ይገናኛልን? ክርስቲያን ሆኜ ዮጋን ብለማመድ ምን ችግር አለው? . . .

ምናልባት እርስዎም እነዚህንና እነዚህን የመሰሉ ጥያቄዎች በአእምሮዎ የሚመላለሱ ከሆነ ወይም ጉዳዮቹ የሚያሳስቡዎት ከሆነ፣ ይህ መጽሐፍ ለእርስዎ ነው። የዚህ መጽሐፍ ጸሐፊ ራሱ በእንደዚህ ያሉ ጥያቄዎችና ፈተናዎች ውስጥ ያለፈ ሰው ነው።

በእነዚህ ጥያቄዎች ውስጥ ያለፈ ብቻ ሳይሆን ለጥያቆዎቹ መልስ ለማግኘት ሲል የራሱን ሕይወት ለአደጋ እስከ ማጋለጥ ደርሶ በጣም ሩቅ በሆኑ ቦታዎችና ፈታኝ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ ራሱን አስገብቶ በራሱ ላይ ሙከራ አድርጎ መልሱን ያገኘ ሰው ነው።

የዚህ መጽሐፍ ደራሲ ከግሪክ ተነሥቶ ወደ ህንድ አገር ሄዶ በዚያ ካሉ የሂንዱይዝም ታላላቅ ጉሩዎች ጋር ተገናኝቶ ያየውንና በራሱ ላይ በተጨባጭ የደረሰበትን ነገር የጻፈው እንደ እርሱ ያለ ጥያቄ ያላቸው ሰዎች በእርሱ የደረሰው ችግር ሳይደርስባቸውና ራሳቸውን ለአደጋ ማጋለጥ ሳያስፈልጋቸው ከእርሱ የድካም ፍሬ ትምህርት መውሰድ ይችሉ ዘንድ ነው።

ስለዚህ ከዚህ ዓይነቱ ተግባራዊ ሙከራና ውጤት መማር ጠቃሚም ተገቢም ነው። ወንድማችን ዲ/ን ሁነኛው ተሾመም ይህን መጽሐፍ ወደ አማርኛ ተርጉሞ ስላቀረበልን ከልብ አመሰግነዋለሁ። እግዚአብሔር ለወንድማችን መልካም ዋጋ ይክፈልልን፣ እኛንም አንብበን ለመጠቀም ይርዳን!

ዋና አከፋፋይ =- #የሀሁ_መጽሐፍት_መደብር

በመደብራችን ሁሉም አይነት መጻህፍት ይገኛሉ። የትምህርት መርጃ መጻህፍት፣ የልብወለድና የታሪክ መጻህፍት፣ መንፈሳዊና አለማዊ መጻህፍት፣ የግጥምና የወግ መጻህፍት፣ የፖለቲካና ኢኮኖሚ እሳቤ መጻህፍት፣ የፍልስፍና እና የስነልቦና መጻህፍት ሁሉም አሉ። ሀሁ መጥታችሁ የፈለጋችሁትን ብቻ ሳይሆን የረሳችሁትንም መጻህፍት ታገኛላችሁ። ከእናንተ የሚጠበቀው ግዜ ወስናችሁ መምጣት ብቻ ነው።

ሌላው በመደብራችን ከ20—50% ቅናሽ አለ። አስር መጽሀፍ ለሚገዙ ደንበኞቻችን ደግሞ አንድ መጽሀፍ በነጻ እናበረክታለን። ስትጎበኙን በደስታ፣ በቅልጥፍና እናስተናግዳችኋለን። ባላችሁበት ሆናችሁ መረጃ ለመጠየቅ ካሻችሁም ስልኩን አንስታችሁ ሀሎ በሉን።

በመደብራችን ሀሁ መጻህፍት ሁሉንም አይነት መጽሀፍ ያገኛሉ፦

የቆዩ እና አዲስ
መንፈሳዊም ሆነ አለማዊ
ክላሲክም ሆነ ዘመናዊ
የታሪክ፣ የፍልስፍና፣ ልብወለድ፣ የትምህርት፣ የስነልቦና፣ የሃይማኖት፣ ግለታሪክ ወዘተ

ሀሁ መጻህፍት መደብርን
በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@fa...
እንዲሁም በራሱ የፌስቡክ ገጽ https://www.facebook.com/h...
ማግኘት ይቻላል።

የፈለጋችሁትን መጽሀፍ እዘዙን፣ ጠይቁን። በቅልጥፍና፣ ከ20-50% በሚደርስ ቅናሽ፣ በደስታ እናቀርብላችኋለን።

አስታውሱ! በመደብራችን 10 መጻህፍት ለሚገዛ 1 መጽሀፍ በነጻ እንሰጣለን።
#የሀሁ_መጽሐፍት_መደብር

አድራሻ ሜክሲኮ ደብረወርቅ ህንጻ
አራት ኪሎ አብርሆት ጎን
ስ.ቁ 0911006705/0924408461

1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.