ብዛት ያላቸው አገልግሎቱን የማይጠቀሙ ሰዎች በሰልፍ ላይ መገኘታቸው በሥራዬ ላይ ጫና ፈጥሮብኛል ሲል የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ገለጸ
#ethiopia | አዲስ ፓስፖርት ለማውጣት እና የአገልግሎት ዘመኑን ያጠናቀቀ ፓስፖርት ለማደስ ወደ ተቋሙ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች የሚመጡ ተገልጋዮች አገልግሎቱን ከማይፈልጉ ወዳጅ ዘመዶቻቸው ጋር መምጣታቸው በሥራው ላይ ጫና እንዳሳደረበት የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ገለጸ።
የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት "አገልግሎቱን ከማይፈልጉ ከ10 በላይ ሰዎች ጋር ወረፋ ለመያዝ የሚመጡ አሉ" ሲሉ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
እንደ ዳይሬክተሯ ማብራሪያ፤ በዋናነት በጥቁር አንበሳ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የሚስተዋለው የወረፋ ሰልፍ ላይ ከአገልግሎት ፈላጊዎች ይልቅ ከወዳጅ ዘመዶቻቸው ጋር ጉዳይ ለማስፈጸም፣ አብሮ ለመሆን እና ለሌሎች ጉዳዮች የሚመጡት የበዛ ቁጥር አላቸው። ይህ መሆኑ አላሰፈላጊ ሰልፎች እንዳሉ እንዲታሰብ ማድረጉንም አንስተዋል።
በዋና ዋና ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች ያሉ ተገቢ ሰልፎችን በ50 በመቶ እንደቀነሰ የተናገሩት ወ/ሮ ሰላማዊት፤ ተቋሙ አሉበት ተብለው የሚጠቀሱት ችግሮች ለረዥም ዓመታት ሲንከባለሉ የመጡ እንደሆኑና ለመፍታት ጥረት እየተደረገ እንደሆነ ተናግረዋል።
ከለውጥ ሥራዎቹ መካከል አዳዲስ አመራሮች እና ሠራተኞች ወደ ተቋሙ ማምጣት፣ የነበረውን የአመለካከት ክፍተት በአቅም ግንባታ ሥራዎች መሙላት ይገኙበታል ተብሏል፡፡
አገልግሎቱን ከማዘመን ባለፈ ኢትዮጵያ ከዘርፉ ማግኘት ያለባትን ገቢ ማሳደግ መቻሉንም ዳይሬክተሯ ተናግረዋል፡፡
የኢምግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በ2017 በጀት ዓመት ብቻ ከ1 ነጥብ 4 ሚልዮን በላይ ፓስፖርት ለዜጎች መስጠት መቻሉ የተገለጸ ሲሆን፤ በዚህም አገልግሎት አሰጣጡን በቴክኖሎጂ የተደገፈ ዘመናዊና ቀልጣፋ እንዲሆን በማድረግ የተቋሙን ዓመታዊ ገቢ ከ34 ቢሊዮን ብር በላይ ማድረስ መቻሉን ማስታወቁ ይታወሳል፡፡ #ahaduradio

1 year ago