11 days ago
ሁሉ ደህና
https://youtu.be/GIpmmIoV3... የሚወጣው ጭስ ህይወታችንን እንዴት እያጠፋው ነው?||Ahadu TV#ahadutv #ahaduradio #ethiopia #አሐዱቲቪ
AHADU TM- Television Network news organization and Television program produce, managed to shift the dynamics of the media industry by producing strong political, social, and economic contents, which evolve from a secondary…

14 days ago
የእናቶች ሞት ከፍተኛ የሆነባቸውን ክልሎች በመለየት በትኩረት እንደሚሰራ ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ
መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬዲዮ) ሚኒስቴሩ አንድ እናት አንድ ህይወት አንድ የጋራ ኃላፊነት በሚል መሪ ቃል ከወሊድ በኃላ የሚከሰት የደም መፍሰስ ላይ ያተኮረ ሀገራዊ የምክክር መድረክ ዛሬ ማካሄድ ጀምሯል፡፡
በመድረኩም 100ሺ የነበረውን የእናቶች ሞት 141 መቀነስ የተቻለ ሲሆን በሚቀጥሉት 4 ዓመታት 70 ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም ተገልጻል፡፡
በ 2030 የእናቶችን ሞት ለመቀነስ የተያዘው እቅድ እንዲሳካ የጤና ባለሙያዎች እና የበላይ አመራሮች በትኩረት መስራት እንደሚጠበቅባቸው በመድረኩ የገለጹት የጤና ሚኒስትር ዴታ ዶክተር ደረጀ ድጉማ ናቸው፡፡
የእናቶች ሞት ከፍተኛ የሆነባቸውን ክልሎች በመለየት በትኩረት እንደሚሰራ አንስተው በኢትዮጵያ የእናቶች ሞት አሁንም አሳሳቢ የማህበረሰብ የጤና ስጋት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ከወሊድ በኃላ የሚከሰት የደም መፍሰስ ለእናቶች ሞት ቀዳሚ መንስኤ መሆኑን የተገለጸ ሲሆን ይህንን ችግር ለመቅርፍ ባለፉት ዓመታት ከተሰሩ ስራዎች በአለም አቀፍ ደረጃ ጊዜውን ያገናዘበ እና በአዳዲስ ጥናቶች ላይ መሰረት ያደረጉ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ተቀርጸው ተግባራዊ ሲደረግ መቆየቱን ገልፀዋል።
የጤና ሚኒስቴር ከክልል ጤና ቢሮዎች እና አጋር አካላት ጋር በጋራ በመተባበር የእናቶችና ህጻናት ሞት ለመቀነስና ጤናቸውን ለማሻሻል የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።
በህይወቴ ጌትነት
#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ፌስቡክ ገጽ፡- https://web.facebook.com/a...
ቴሌግራም ገጽ፡- https://t.me/ahaduradio

1 year ago
ሥራ አጥነትን ለመቀነስ የሰው ሐብት ልማት መር ኢኮኖሚ መዘርጋት ያስፈልጋል ሲሉ ባለሙያዎች ገለጹ
#ethiopia | በኢትዮጵያ እየተስፋፋ የመጣውን የሥራ አጥነትን ችግር ለመቀነስ፣ ለማስቀረት እና ሁለንተናዊ ዘላቂ ዕድገትን ለማስመዝገብ፤ መንግሥት የሰው ሐብት ልማት መር ኢኮኖሚን ተግባራዊ ማድረግ እንዳለበት አሐዱ ያነጋገራቸው የምጣኔ ሐብት ባለሙያዎች ተናግረዋል።
ሥራ ዕድል ከተሞች ተኮር በመሆኑ ሥራ ፍለጋ ከገጠር ወደ ትናንሽ ከተሞች የሚፈልሱ ከመጀመሪያ ደረጃ እስከ ዩኒቨርሲቲ፣ ሁለተኛ ዲግሪ እንዲሁም በተለያያ ደረጃ ከቴክኒክና ሙያ ተቋማት ተመርቀው የሚወጡ ወጣቶችን ማስተናገድ የሚችል የሥራ ዕድል ለመፍጠር፤ እንደ ግብርና እና ሌሎች ዘርፎች ሁሉ የሰው ሐብት ልማት ላይ መተኮር እንዳለበት የምጣኔ ሐብት ባለሙያው ፕሮፌሰር መልካሙ ማዳ ለአሐዱ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ፖሊሲ የወጣቱን እና ሥራ ፈላጊውን ፍላጎት ከሟሟላት አንፃር ክፍተት እንዳለበትም ባለሙያው አክለዋል።
ከ40 በላይ ከሚሆኑ ዩኒቨርሲቲዎች በየዓመቱ ከ150 ሺሕ በላይ ተማሪዎች የሚመረቁበት ወቅት መሆኑን ጠቁመው፤ "ይህም መንግሥት ተጨማሪ የሥራ ዕድሎችን መፍጠር እንዳለባት የሚያሳዩ ናቸው" ብለዋል።
ከሥራ አጥ ልየታ ጀምሮ እስከ ስምሪት ድረስ ሥራ አጥን ወደ ሥራ ከማስገባት አንጻር፤ የሥልጠና፣ የፋይናንስ እና የቦታ አቅርቦት ውስንነቶች መቀረፍ እንዳለባው ጠቁመዋል።
አሐዱ ያነጋገራቸው ሌላኛው የአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ መምህርና የኢኮኖሚ ባለሙያ ዶ/ር ኢዞ እማኮ በበኩላቸው፤ በኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ግብርና መር ኢኮኖሚን ከሥራ ዕድል ፈጠራ ጋር ተያይዞ ሥራዎች እንደተሰሩ ሁሉ፣ በኢንዱስትሪው ዘርፍም በመድገም የሥራ ጥነትን ለማስቀረት ሁነኛ መፍትሔ መሆኑን ተናግረዋል።
አክለውም ለአንድ ሀገር ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የሥራ ዕድል ፈጠራ ዋነኛው መስፈርት በመሆኑ በመግለጽ፤ ይህንን ለሟሟላት መንግሥት ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫው አድርጎ መስራት እንደሚገባው ሀሳባቸውን አጋርተዋል።
የዓለም ሀገራት በጋራ እየተፈተኑበት የሚገኘውን የሥራ አጥነት ችግር ለመፍታት የጋራ የሆነ ሥራ እንደሚያስፈልግም አብራርተዋል።
"የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ለሌሎች ሀገራት ለኢንቨስትመንት፣ እና ለንግድ ዕድሎችን እንዲያመጣ ሊተኮርበት ይገባል" ሲሉም አሳስበዋል።
ከፍተኛ የተፈጥሮ እና የግብርና ሐብት፣ ለሥራ አጥ ቅነሳ ከፍተኛ ዕድል እንደሚሆን ነው ባለሙያው የገለጹት፡፡
የምጣኔ ሐብት ባለሙያሙቹ አያይዘውም፤ "ችግሩ ላይ በአጽንኦት ከተሰራ ሰው ሐብት ተኮር ለውጥ ይመጣል" ሲሉ ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ በየዓመቱ ከ2 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የሥራ አጥ ገበያውን እንደሚቀላቀሉ አሐዱ ከዚህ ቀደም መዘገቡ ይታወሳል። #ahaduradio

Sponsored by
Surafel
1 year ago
በመዲናዋ ሰሌዳ ሳይፈታና መንጃ ፈቃድ ሳይወሰድ ቅጣት የሚፈጸምበት አሠራር መጀመሩ ተገለጸ
#ethiopia | በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ አሽከርካሪ የደንብ ጥሰት በሚፈጸምበት ወቅት፤ ሰሌዳ ሳይፈታበትና መንጃ ፈቃድ ሳይወሰድበት ቅጣት የሚፈፅምበትን አሰራር መጀመሩን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ለአሐዱ አስታውቋል።
የባለስልጣን መስሪያቤቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አማረ ታረቀኝ በተለዩ አንዳንድ ምክንያቶች ሰሌዳ ሊፈታ እንደሚችል አንስተው፤ ከእነዚህም ውስጥ አሽከርካሪው ቅጣት ተቀጥቶ ደረሰኝ እጁ ላይ ካለ እና ከተቀጣ በኋላ መንጃፈቃድ ሲጠየቅ ማሳየት የማይችል ከሆነ ያለው አማራጭ ሰሌዳ መፍታት እንደሆነ ተናግረዋል።
ይህ ሲሆንም ከተቀጣበት ቦታ ቤቱ ድረስ እስኪሄድ አልያም የመንግሥት ተቋማት ላይ ሂዶ ሕጋዊ ሂደቱን ተከትሎ ክፍያ ከፈፀመ በኋላ፤ መውሰድ እንዲችል እንጂ አገልግሎት እንዲሰጥበት አለመሆኑን ገልጸዋል።
ከዚህ በተጨማሪም የተከለከለ ቦታ ላይ ከቆመ እና አሽከርካሪው ከሌለ ሰሌዳው ሊፈታ እንደሚችል አንስተዋል።
በመሆኑም ተቆጣጣሪዎች በእነዚህ አይነት ምክንያቶች አሁንም ቢሆን ሰሌዳ የሚፈቱበት አጋጣሚ እንዳለ ገልጸዋል።
ነገር ግን ሰሌዳን መፍታት ለወንጀል ነክ ጉዳዮች የሚያጋልጥበት ዕድል እና ሰሌዳዎች በውጪ ምንዛሬ የሚመጡ በመሆናቸው እየተፈቱ በሚታሰሩበት ወቅት የሚያሳድሩት ተፅዕኖ ስለመኖሩ አንስተዋል።
በመሆኑም ይህንን ችግር ለመቅረፍ ሲባል ሰሌዳ ሳይፈታ እና መንጃ ፈቃድ ሳይቀበሉ የሚተገበርበትን መንገድ ለመፍጠር በቴክኖሎጂ የታገዘ ስርዓት መጀመሩን አስታውቀዋል።
በዚህ ስርዓትም ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ የብቃት ማረጋገጫ ያላቸው አሽከርካሪዎች እና ከ 800 ሺሕ በላይ ተሽከርካሪዎች መረጃ መወሰዱን ለአሐዱ ተናግረዋል።
መረጃውን በመያዝ ቅጣት ለመፈጸም በሚደረግበት ሂደት ግን በተለይም ቆየት ያሉ ተሽከርካሪዎች የተመዘገቡበት ስልክ ቁጥር በቤት ስልክ በመሆኑ፤ አሽከርካሪዎች ቅጣት የከፈሉበት የማረጋገጫ መልዕክት በስልካቸው መግባት አለመቻሉ ተግዳሮት ስለመሆኑ አንስተዋል።
በመሆኑም አሰራሩ መጀመሩን ገልጸው፤ ይህንን ችግር አስወግዶ በተሟላ ሁኔታ ለመተግበር ዝግጅት መጨረሱን ተናግረዋል።
"ከላይ በተጠቀሱት ምክንያቶችና ሌሎች የተለየ ችግር ካልገጠመ በስተቀር በአዲስ አበባ ውስጥ ሲስተም ላይ የተመዘገቡ መንጃፈቃድ እና የተሽከርካሪ ሰሌዳዎችን ሳይፈቱ እና መንጃፈቃድ ሳንቀበል ተግባራዊ እያደረግን ነው" ብለዋል። #ahaduradio

በመዲናዋ ከተፈቀደላቸው መጠን በላይ በሚጭኑ ተሽከርካሪዎች ላይ በደንቡ መሠረት እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ተገለጸ
#ethiopia | ከተፈቀደላቸው መጠን በላይ በሚጭኑ ተሽከርካሪዎች ላይ በደንቡ መሠረት እርምጃ እየወሰደ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ለአሐዱ አስታውቀዋል።
በኮሚሽኑ የትራፊክ ቁጥጥር መምሪያ የትራፊክ ሙያና ሕዝብ ግንዛቤ ዲቪዥን ኃላፊ ኢንስፔክተር ሰለሞን ደስታ ለአሐዱ እንደገለጹት፤ አሽከርካሪዎች ጭነት በሚጭኑበት ጊዜ ከተፈቀደላቸው ከፍታ፣ ስፋትና ርዝመት ውጪ በመጫን እቃው ወድቆ በሰዎች እና በንብረት ላይ ጉዳት እንዳያደርስ የሚከለክለው ደንብ ተግባራዊ በመደረግ ላይ ይገኛል።
በዚህም መሠረት ደንቡ እስከ 1 ሺሕ 50ዐ ብር የሚያስቀጣ ሲሆን፤ የትራፊክ ፍሰቱን ለመቆጣጠር በተገጠሙ የደህንነት ካሜራዎች ላይ፣ በኤሌክትሪክ መስመሮች እና የመብራት ፖሎች ላይ ጉዳት እስከማድረስ ደንቡን የተላለፉ አሽከርካሪዎች መኖራቸውን ኢንስፔክተሩ ገልጸዋል፡፡
ከልክ በላይ የሚጭኑ ተሽከርካሪዎች ለትራፊክ አደጋ መንስኤ መሆናቸውን እና በተለይ የጭነት ተሽከርካሪዎች በመሠረተ ልማት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱ መሆኑንም ኢንስፔክተር ሰለሞን ተናግረዋል።
"የትራፊክ እንቅስቃሴው ሕግን የተከተለና ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራ ቢሰራም፤ የሕግ ማስከበርና የቁጥጥር ሥራውም እየተሰራ ነው" ብለዋል።
በከተማው የትራፊክ እንቅስቃሴ እንዲኖር በማድረግ እና የመንገድ ትራፊክ አደጋን ለመከላከል ሥራዎችን እያከናወነ ነው ያሉት ኃላፊው፤ በተለይም ደህንነቱ የተጠበቀ የመንገድ ሥርዓት እንዲኖር ከባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ እየተሠራ መሆኑን አስታውቀዋል።
የጭነት መኪኖች ትልቁን የሀገሪቱን ምጣኔ ሀብት ከቦታ ቦታ የሚያንቀሳቅሱ በመሆናቸው፤ በተፈቀደላቸው ልክ መጫን እንደሚገባቸው ኃላፊው አሳስበዋል። #ahaduradio

ብዛት ያላቸው አገልግሎቱን የማይጠቀሙ ሰዎች በሰልፍ ላይ መገኘታቸው በሥራዬ ላይ ጫና ፈጥሮብኛል ሲል የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ገለጸ
#ethiopia | አዲስ ፓስፖርት ለማውጣት እና የአገልግሎት ዘመኑን ያጠናቀቀ ፓስፖርት ለማደስ ወደ ተቋሙ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች የሚመጡ ተገልጋዮች አገልግሎቱን ከማይፈልጉ ወዳጅ ዘመዶቻቸው ጋር መምጣታቸው በሥራው ላይ ጫና እንዳሳደረበት የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ገለጸ።
የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት "አገልግሎቱን ከማይፈልጉ ከ10 በላይ ሰዎች ጋር ወረፋ ለመያዝ የሚመጡ አሉ" ሲሉ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
እንደ ዳይሬክተሯ ማብራሪያ፤ በዋናነት በጥቁር አንበሳ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የሚስተዋለው የወረፋ ሰልፍ ላይ ከአገልግሎት ፈላጊዎች ይልቅ ከወዳጅ ዘመዶቻቸው ጋር ጉዳይ ለማስፈጸም፣ አብሮ ለመሆን እና ለሌሎች ጉዳዮች የሚመጡት የበዛ ቁጥር አላቸው። ይህ መሆኑ አላሰፈላጊ ሰልፎች እንዳሉ እንዲታሰብ ማድረጉንም አንስተዋል።
በዋና ዋና ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች ያሉ ተገቢ ሰልፎችን በ50 በመቶ እንደቀነሰ የተናገሩት ወ/ሮ ሰላማዊት፤ ተቋሙ አሉበት ተብለው የሚጠቀሱት ችግሮች ለረዥም ዓመታት ሲንከባለሉ የመጡ እንደሆኑና ለመፍታት ጥረት እየተደረገ እንደሆነ ተናግረዋል።
ከለውጥ ሥራዎቹ መካከል አዳዲስ አመራሮች እና ሠራተኞች ወደ ተቋሙ ማምጣት፣ የነበረውን የአመለካከት ክፍተት በአቅም ግንባታ ሥራዎች መሙላት ይገኙበታል ተብሏል፡፡
አገልግሎቱን ከማዘመን ባለፈ ኢትዮጵያ ከዘርፉ ማግኘት ያለባትን ገቢ ማሳደግ መቻሉንም ዳይሬክተሯ ተናግረዋል፡፡
የኢምግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በ2017 በጀት ዓመት ብቻ ከ1 ነጥብ 4 ሚልዮን በላይ ፓስፖርት ለዜጎች መስጠት መቻሉ የተገለጸ ሲሆን፤ በዚህም አገልግሎት አሰጣጡን በቴክኖሎጂ የተደገፈ ዘመናዊና ቀልጣፋ እንዲሆን በማድረግ የተቋሙን ዓመታዊ ገቢ ከ34 ቢሊዮን ብር በላይ ማድረስ መቻሉን ማስታወቁ ይታወሳል፡፡ #ahaduradio

ባለፉት 5 ዓመታት የኢትዮጵያ መንግሥት ወጪው ከገቢው በከፍተኛ ደረጃ እንደበለጠ ተገለጸ
#ethiopia | የኢትዮጵያ መንግሥት ባለፉት 5 ዓመታት ያወጣው ወጪ ከሚያገኘው ገቢ በከፍተኛ ደረጃ መብለጡን የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ባለሙያዎች ማህበር አስታውቋል።
የኢትየጵያ ኢኮኖሚክስ ባለሙያዎች ማህበር በዛሬው ዕለት 22ኛውን ዓለም አቀፍ ጉባዔ ያካሄደ ሲሆን፤ በመድረኩም ከወቅታዊ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ጥናታዊ ፅሁፎች ቀርበዋል።
በቀረበው ጥናትም የኢትዮጵያ መንግሥት ወጪው ከሚያገነው ከገቢ በከፍተኛ ደረጃ የበለጠ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በተቃራኒው መንግሥት ገቢው ከወጪው አንፃር አነስተኛ መሆኑን የገለጹት የማህበሩ ከፍተኛ ተመራማሪ ዶክተር አረጋ ሹመቴ፤ በጥናቱ 'የመንግሥት ወጪ አቅጣጫ ወዴት የሚያመዝን ነው?' የሚለውም መጠናቱን ገልጸዋል፡፡
"በከፍተኛ ሁኔታ የመንግሥት ካፓታል ወጪ መቀነሱም በጥናቱ ተረጋግጧል" ብለዋል፡፡
"ከ2016 ዓ.ም በፊት የመንግሥት ወጪ ትልቁን መደበኛ በጀት እየያዘ ኢንቨስትመንት እየቀነሰ መሄዱ ማሳያ ነው" ያሉት ዶክተር አረጋ "መንግሥት ትልቁ ኢንቨስተር ቢሆንም የሚጠበቀውን ያህል ግን ኢንቨሰት እያደረገ ለካፒታል በጀትም እየተያዘ አይደለም" ሲሉ ጠቁመዋል።
ሌላው ትኩረት የተደረገበት ጥናት የመንግሥት ዕዳ ላይ የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ ዕዳ ከፍተኛ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በመድረኩም "ማንኛውም ሀገር ዕዳ አለበት" የተባለ ሲሆን፤ ዕዳው ከሀገር ውስጥም ሆነ ከውጪ ሊሆን እንደሚችል ተናግረዋል።
ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ዕዳ ያለበት የውጭ ዕዳ በመሆኑና ዕዳውም የመጣው በመንግሥት በራሱ እና የመንግሥት ተቋማት እንደ ኤልፓ፣ ቴሌኮም እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመሳሰሰሉ ተቋማት ናቸው ብለዋል፡፡
በተመሳሳይ መልኩ ጥናቱ የኢትዮጵያ ዕዳ የመክፈል አቅሟም ለመመለከት የተሞከረ ሲሆን፤ ዕዳ የመክፈል አቅም የሚለካው ወደ ወጪ በሚላክ ምርት ጋር የተያያዘ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የኢትዮጰያ ዕዳ ከፍተኛው የውጭ ዕዳ በመሆኑ መለኪው ወደ ወጪ የሚላከው ምርቷ መሆኑ የተገለጸም ሲሆን፤ በዚህ አንፃር ሀገሪቱ ብዙ የውጭ ዕዳ አለባት ተብሏል፡፡ የሚካሄደዉ ጉባኤ እስከ ነገ የሚቀጥል መሆኑም ተገልጿል፡፡ #ahaduradio

በብርሃን እና ሰላም ማተሚያ ቤት ከደረሰኝ ህትመት ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰው ወረፋ እየጠበቀ እንደሚገኝ ተገለጸ
ችግሩን ለመፍታት ደረሰኝ የሚሰጥበት ጊዜ መራዘሙ ተነግሯል
በብርሃን እና ሰላም ማተሚያ ቤት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ግብር ከፋዮች ልዩ መለያ ኮድ (QR Cod) የተካተተበትን ደረሰኝ ለማሳተም ወረፋ በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኙ የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል።
የገቢዎች ሚኒስቴር እና ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት በደረሰኞች ላይ ልዩ መለያ ኮድ(QR-Code) አካቶ ማተም የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸውን ተከትሎ፤ አሁን ላይ በመላ ሀገሪቱ ዲጂታላይዝ የደረሰኝ ሥርዓት ወደ ሥራ እንዲገባ እየተደረገ መሆኑ ይታወቃል።
ይህንን ተከትሎም በርካታ ቁጥር ያላቸው ግብር ከፋዮች በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ደረሰኝ ለማሳተም ተሰልፈው በመጠባበቅ ላይ የሚገኙ ሲሆን፤ አሐዱም "ወረፋው የተፈጠረበት ምክንያት ምንድን ነው?" ሲል የፌደራል ገቢዎች ሚኒስቴርን ጠይቋል።
የሚኒስቴሩ መስሪያ ቤቱ የታክስ መረጃ ሽያጭ አስተዳደር ዳይሬክተር ወ/ሮ ራቢያ ይማም የደረሰኝ እጥረት እንዳልተከሰተ አንስተው፤ ነገር ግን ከፍተኛ የሆነ ወረፋ መስተዋሉን ተናግረዋል።
የወረፋ ሂደቱ የሚፈጥረው መስተጓጎል እንደሚኖር የጠቆሙም ሲሆን፤ "በዚህም የደረሰኝ እጥረት ሊከሰት ይችላል" ብለዋል።
"ወረፋ እንዲፈጠር ያደረገው አሰራር ሥርዓቱ እንደ ሀገር ለመጀመሪያ ግዜ የተጀመረ በመሆኑ ነው" ያሉት ዳይሬክተሯ፤ "በየትኛውም የኢትዮጵያ ክፍል የሚገኝ ማንኛውም ነጋዴ ከብርሃን እና ሰላም ማተሚያ ቤት ደረሰኝ አሳትሞ መውሰድ አለበት። ይህ ሕግ ነው" ሲሉም ገልጸዋል።
በተጨማሪም ብርሃን እና ሰላም ማተሚያ ቤት ካለው አቅም ጋር መናበብ አለመቻሉን ጠቁመው፤ ይህን የተፈጠረውን የወረፋ ችግር ለመፍታት የተቋሙ ሠራተኞች ለ24 ሰዓት እየሰሩ እንደሚገኙ ተናግረዋል።
በማተሚያ ቤቱ ዜጎች የገጠማቸውን የወረፋ ችግር ለመፍታት ተጨማሪ የህትመት ማሽኖችን ከውጭ መግባታቸውን የገለጹት የታክስ መረጃ ሽያጭ አስተዳደር ዳይሬክተሯ፤ ተጨማሪ የሰው ኃይል ቅጥር መደረጉንም አንስተዋል።
"የማሽኑ የሙከራ ሥራ እንዳለቀ ከነሀሴ ወር ጀምሮ ሥራ ይጀምራል፡፡ ይህ ማሽን እጥፍ የማምረት አቅም ስለሚኖረው አሁን የተፈጠረውን ችግር ይፈታል" ሲሉም ገልጸዋል።
አክለውም ከወረፋ ጋር ተያይዘው የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታል ማኅበረሰቡ ደረሰኝ የሚወስድበት ጊዜ እንዲራዘም መደረጉን አንስተው፤ "ሕጉ ጸድቆ ከፍትህ ሚኒስቴር እንደወጣ በይፍ የምናሳውቅ ይሆናል" ብለዋል።
ይህ ችግር የተፈጠረው ግብር ከፋዩ ማሕበረሰብ የመጨረሻ የመመዝገቢያ ጊዜ ሲደርስ በብዛት መምጣቱ ነው ተብሏል። #ahaduradio

ወደ ጎረቤት ሀገራት የሚሰደዱ የዱር እንሰሳት የመመለስ ዕድላቸው እየቀነሰ መምጣቱ ተገለጸ
#ethiopia | ባለፉት ሦስት ዓመታት በተደረገ ጥናት በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ጎረቤት ሀገራት የሚሰደዱ የዱር እንሰሳት ወደ ኢትዮጵያ የመመለስ ዕድላቸው ከቀደሙት ዓመታት የዚህኛው ዓመት መቀነሱ መረጋገጡን፤ የኢትዮጵያ የዱር እንሰሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል።
በፓርኮች ውስጥ የሚኖሩ የዱር እንሰሳት ወደ ጎረቤት ሀገራት የሚሰደዱት በሕገ-ወጥ አደን፣ በሕገ-ወጥ የሰዎች አሰፋፈር እና መሰል ሁኔታዎች ነው ተብሏል።
የባለሥልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሰሎሞን መኮንን፤ የጋምቤላ ብሔራዊ ፓርክን በምሳሌነት በማንሳት፤ ከፓርኩ ወደ ደቡብ ሱዳን ተሰደው የሚመለሱ የዱር እንሰሳት ከዚህ ቀደም ከነበረው በከፍተኛ መጠን መቀነሱን ለአሐዱ ተናግረዋል።
ችግሩን ለመፍታት "ኤፒ አፍሪካ ፓርክ" የተሰኘ ድርጅት ጋር በመተባበር እየተሰራ መሆኑን የገለጹም ሲሆን፤ እንደ ሀገር የዱር እንስሳት የጥበቃ ሽፋንን ለማሳደግ የተለያዩ ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑን አብራርተዋል።
"ዘርፉ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ የሚገኝበት ነው" ያሉም ሲሆን፤ ኢትዮጵያም ለተፈጥሮ ሀብቶች የተለየ ትኩረት በመስጠት ተጠቃሚነቷን ማስፋት እንዳለባት አሳስበዋል።
በተጨማሪም ሁሉም የሕብረተሰብ ክፍል የዱር እንሰሳት ላይ የሚፈጸመውን ሕገ-ወጥ አደን ጨምሮ ደህንነታቸውን ለመጠበቅ እና የቱሪዝት መስህብነታቸውን እንደጠበቁ እንዲቆዩ ለማገዝ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።
በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ የዱር እንሰሳት ጥበቃ ባለሥልጣን እና በክልሎች የሚተዳደሩና ከአጠቃላይ የሀገሪቱ መሬት የቆዳ ስፋት 10 ነጥብ 6 ከመቶ የሚሆነውን የሚይዙ፣ በዓለም የመረጃ ቋት የሚታወቁ 87 ፓርኮችና ጥብቅ ቦታዎች የሚገኙ ሲሆን፤ በተለያዩ ሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ ችግሮች ምክንያቶች በፓርኮቹ የሚገኙ የዱር እንሰሳት ቁጥር እየተመናመነ እንደሚገኝ ይገለጻል፡፡ #ahaduradio

በሐሰተኛ ሰነድ ሀገር ውስጥ ገብተው ሲንቀሳቀሱ የተገኙ ከ12 ሺሕ በላይ የውጭ ሀገር ዜጎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገለጸ
#ethiopia | ሐሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀት በሕገ-ወጥ መንገድ ሀገር ውስጥ ገብተው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ከ12 ሺሕ 127 በላይ የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች በሕግ ቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አስታውቋል
ተቋሙ ከባለድርሻ አካላት ጋር የ2017 በጀት ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2018 በጀት ዓመት እቅድ ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ በትናንትናው ዕለት አካሂዷል፡፡
በመድረኩም ከውጭ ሀገር ዜጎቹ በተጨማሪ፤ ከፓስፖርት አገልግሎት ጋር በተገናኘ ዜጎችን ለእንግልት የዳረጉና ብልሹ አሰራር ውስጥ የተገኙ 26 የተቋሙ ሠራተኞች በሕግ ተጠያቂ መደረጋቸው ተነግሯል፡፡
የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት 3 ሺሕ 868 ሰዎች የተጭበረበረ ሰነድ በመጠቀም ፓስፖርት ለማውጣት ሲሞክሩ በቁጥጥር በማዋል በሕግ ተጠያቂ መደረጋቸውን ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
በዚህም መሠረት በግለሰቦቹ ላይ በወንጀል ተጠያቂ ማድረግ፣ ከሀገር ማስወጣት እና ወደ ሕጋዊ መስመር እንዲገቡ በማድረግ እርምጃ መወሰዱን ጠቁመዋል፡፡
ባለፉው አንድ ዓመት በቁጥጥር ሥር ከዋሉ ሰዎች መካከል 2 ሺሕ 77 ሃሰተኛ ሰነድ በማቅረብ፣ 275 ኢትዮጵያዊ ሳይሆኑ ፓስፖርት ለማውጣት በመሞከር እንዲሁም የተቀሩት በተለያየ መንገድ ለማጭበርበር ሲሞክሩ የተያዙ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎቱ ባለፉት ሁለት ዓመታት አዲስ ሪፎርም ተግባራዊ በማድረግ፤ በርካታ ሥራዎችን መስራቱንም አስታውቀዋል፡፡ #ahaduradio

ሕገ-ወጥ ነጋዴዎች እና ደላሎች ያመረትነውን ምርት በአግባቡ እንዳንሸጥ እያደረጉን ነው ሲሉ አርሶአደሮች ቅሬታቸውን ገለጹ
#ethiopia | ሕገ-ወጥ ነጋዴዎች እና ደላሎች ያመረትነውን ምርት በአግባቡ እንዳንሸጥ እያደረጉን ነው ሲሉ በኦሮሚያ ክልል ሆለታ ከተማ የመደጉዲ ቀበሌ አርሶአደሮች ቅሬታቸውን ለአሐዱ ተናግረዋል።
አርሶአደሮቹ፤ "ያመረትናቸውን እንደ ቆስጣ፤ ሰላጣ ፤ጥቅል ጎመን እና የመሳሰሉ የአትክልት ምርቶችን በቀጥታ ወደ አዲስ አበባ በመላክ ስንሸጥብንቆይም አሁን ላይ ሕገ-ወጥ ነጋዴዎች እና ደላሎች ጣልቃ እየገቡ ከልክ በታች እንድንሸጥ እየተገደድን ነው" ብለዋል።
"ተደራጅተን ምርቱን ወደ አዲስ አበባ ስንልክ ሕገ-ወጥ ደላሎች ጣልቃ እየገቡ ከመደበኛ ነጋዴዎች ጋር በመነጋገር አትክልቱ ቶሎ እንዳይሸጥ ስለሚያደርጉ አትክልቱ እንዳይበላሽ ስንል ብቻ ሳንፈልግ በግማሽ ቀንሰን ለመሸጥ እንገደዳለን" ሲሉም ተናግረዋል።
በዚህም አርሶአደሮች "እንደዚህ አይነት ምርት ለምናቀርብ ሰዎች የገበያ ቦታ እንዲመቻችልና፤ ወደ ከተማ ወስደን ለመደበኛ ነጋዴዎች እንድናስረክብ አስቻይ ሁኔታዎች ሊኖሩ ይገባል" ብለዋል፡፡ በተጨማሪም ሕገ-ወጥ ደላሎችንና ነጋዴዎችን የሚመለከተው አካል እንዲቆጣጠር ጠይቀዋል።
አሐዱም የአርሶአደሮችን ቅሬታ በመያዝ የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮን ጠይቋል።
በዚህም በኦሮሚያ ንግድ ቢሮ የሰብል ምርቶች ግብይት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ጉቱ ተመስገን በሰጡት ምላሽ፤ "በሆለታ ከተማ አርሶአደሮች ምርታቸውን የሚያቀርቡበት የክልሉ ንግድ ቢሮ ያዘጋጀው ቦታ አለ" ብለዋል።
ዳይሬክተሩ በአዲስ አበባ ከተማ ዙሪያ ያሉ አርሶአደሮችም ወደ ከተማዋ ገብተው ምርታቸውን እንዲያቀርቡ በ5 ትልልቅ የገበያ ቦታዎች ለሁሉም ክልሎች በኮታ ተለይቶ ከአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ጋር እየተሠራ መሆኑን አስታውቀዋል።
"የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ በሰጠን ኮታ መሠረት ዓመቱን ሙሉ በቀጣይነት ለአዲስ አበባ ከተማ ማቅረብ የሚችሉ አርሶአደሮች ለይተን እየሰራን ነው" ሲሉም ተናግረዋል።
በክልሉ የሚገኙ ሕገ-ወጥ ደላሎችን እና ነጋዴዎችን ሙሉ በሙሉ ከመቆጣጠር አንፃር ክፍተቶች ቢኖሩም፤ ሕገ-ወጥነትን ለመቀነስ ንግድ ቢሮው በርካታ ሥራዎችን እየሰራ መሆኑን ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል። #ahaduradio

የፋሲል ቤተ-መንግሥት ከእድሳት በኋላ ከ60 ሺሕ በላይ ጎብኚዎች እንደጎበኙት ተገለጸ
📌አብዛኛው ጎብኚ የቅርሱ ዕድሳት አግባብነት ያለው መሆኑን ለማረጋገጥና ታሪካዊ ይዘቱን በጠበቀ መልኩ መታደሱን ለማየት መምጣቱን ታውቋል
#ethiopia | ከአንድ ዓመት በፊት መካሄድ የጀመረው የአጼ ፋሲል ቤተ-መንግሥት እድሳት ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ ለጎብኚዎች ክፍት መደረጉን ተከትሎ፤ ቅርሱን ለመጎብኘት ወደ ከተማዋ የገቡ ከ56 ሺሕ የሀገር ውስጥ ጎብኚዎች እና 1 ሺሕ 914 የሚሆኑ የውጭ ቱሪስቶች ቅርሱን መጎብኘታቸውን የጎንደር ከተማ የቅርስ ጥበቃ ቢሮ ለአሐዱ አስታውቋል።
ቅርሱ ከ1980 ጀምሮ ምንም እድሳት እና ጥገና ሳይደረግለት ቆይቶ ባሳለፍነው ዓመት ጥገናው መጀመሩ የተገለጸ ሲሆን፤ እድሳቱ ሦስት አይነት ሥራዎችን ያካተተ ስለመሆኑ የጎንደር ከተማ የቅርስ ጥበቃ ቱሪዝም ልማት ቡድን መሪ ዓይቼው አዲስ ተናግረዋል።
ይህም እድሳት የመጀመሪው ሙሉ ጥገና፣ ሁለተኛው ግቢውን ማስዋብ እና ሦስተኛው የኤሌትሪክ ኃይል የመስመር ዝርጋታን ያካተተ መሆኑም ጠቁመዋል፡፡
በ16ኛው ክፍለ ዘመን በአፄ ፋሲለደስ እንደተቆረቆረች በሚነገርላት ጎንደር ከተማ የሚገኘው እና ከ40 ዓመታት በፊት በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የዓለም ቅርስ ተብሎ የተመዘገበው የፋሲል ቤተ-መንግሥት የቅርስ ጥበቃ እና እድሳት ሂደትን በተከተለ መንገድ መታደሱንም ቡድን መሪው ለአሐዱ አብራርተዋል።
እንደ ቡድን መሪው ገለጻ፤ በከፍተኛ ጥንቃቄ የተካሄደው የቅርሱ እድሳት ተጠናቆ ጎብኚዎችን ማስተናገድ ከጀመረ ወዲህ ከተማዋን ለመጎብኘት የሚመጡ የሀገር ውስጥና የውጭ ዜጎች ቁጥር ከሌሎች ጊዜያት አንፃር በከፍተኛ መጠን ጨምሯል።
አክለውም፤ እድሜ ጠገቡ የፋሲል ቤተ-መንግሥት እድሳት መጠናቀቁ በኢትዮጵያ የቱሪዝም ማዕከል ከሆኑት እድሜ ጠገብ ከተሞች መካከል አንዷ በሆነችው ጎንደር ለሚከበረው የጥምቀት በዓል ልዩ ድምቀት ሰጥቶት ማለፉን አስታውሰዋል።
"በተለያዩ ምክንያቶች ተቀዛቅዞ የነበረው የቱሪዝም ዘርፍ እያንሰራራ ይገኛል" ሲሉም አቶ ዓይቼው ተናግረዋል፡፡
የአፄ ፋሲለደስ ቤተ መንግሥት ፋሲል ግቢ በ1628 ዓ.ም. የተሠራ ሲሆን፤ በውስጡ ቤተ መዛግብት፣ የአፄ ፋሲል መዋኛ፣ ቁስቋም ማርያም ቤተ ክርስቲያን፣ ራስ ግምብና ደረስጌ ማርያምን ይዟል ብለዋል፡፡
በዩኔስኮ 1979 ዓ.ም. በዓለም ቅርስነት የተመዘገበው የአፄ ፋሲለደስ ቤተ-መንግሥት፤ በውስጡ ያሉት ቤተ መንግሥቶች ከ100 በላይ ክፍሎች ያሏቸው ሲሆን፤ በአጠቃላይ 7 ሄክታር ወይንም 70 ሺሕ ስኩዌር ሜትር ይሸፍናል ሲሉ ገልጸዋል።
ቡድን መሪው አያይዘውም፤ ከጎንደር አብያተ መንግሥታት በተጨማሪ በሌሎች አካባቢዎችም ቅርሶች እየተጠገኑ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
"ጎንደር ከተማ በውስጧ ከሚገኙ ድንቅ ቅርሶቿ በተጨማሪ በጎንደር ዙሪያ ወረዳና አካባቢው በርካታ ታሪካዊ የቱሪስት መዳረሻዎች ጋር የተሳሰረች ከተማ ናት" ብለው፤ የሀገር ውስጥ ቱሪስቶች እና ለውጭ ሀገር ቱሪስቶች መጥተው እንዲጎበኙ ጥሪ አስተላልፈዋል። #ahaduradio

በትራፊክ ምክንያት የሚከሰቱ አደጋዎችን በሚቀጥሉት 5 ዓመታት በ25 በመቶ ለመቀነስ እየተሰራ እንደሚገኝ ተገለጸ
#ethiopia | በመንገድ ላይ የትራፊክ አደጋ የሚከሰቱ የሞትና የአካል ጉዳቶችን በሚቀጥሉት 5 ዓመታት ውስጥ በ25 በመቶ ለመቀነስ የመንገድ ደህንነት ስትራቴጂ ቀርፆ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን አስታውቋል።
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከዚህ ቀደም ለአምስት ዓመት የሚቆይ የመንገድ ደህንነት ስትሬቴጂን ተግባራዊ ሲያደርግ እንደነበረ የገለጸ ሲሆን፤ ከዓለም አቀፍና ከሀገር አቀፍ ተቋማት ጋር የተለያዩ ጥናቶችንና ትግበራዎችን በማድረግ ለውጥ ማምጣት ስለመቻሉ አንስቷል።
በዚህም የመጀመሪያ ዙር ተግባራዊ በተደረገው ስትራቴጂ መሠረት በመንገድ ትራፊክ አደጋ የሚከሰቱ አደጋዎችን ቀድሞ ከነበሩ ጊዜያት 19 በመቶ ያክል መቀነስ ተችሎ እንደነበር አሐዱ ከተቋሙ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
አሁን ላይ ተግባራዊ በሚደረገው ሁለተኛው ዙር ስትራቴጂም አጠቃላይ የትራፊክ አደጋን 25 በመቶ ያክል ለመቀነስ እቅድ መያዙን የገለጸው ባለስልጣኑ፤ ይህንን ለማሳካትም ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር በተለያዩ ዘርፎች በርካታ ሥራዎች እንደሚሰሩ አስታውቋል።
ለአብነትም በ2024 በተጠናው ጥናት በአንድ ዓመት ውስጥ 401 የሞት አደጋ የተመዘገበውን በ2030 ወደ 200 ለማውረድና 3 ሺሕ 666 የአካል ጉዳት አደጋዎች የደረሱትን ደግሞ ወደ 1 ሺሕ 833 ለመቀነስ ታቅዷል።
በዚህም መሠረት የፍጥነት መቆጣጠሪያ መሳሪያዎችን፣ የመንገድ ላይ የትራፊክ ምልክት ቀለሞችን መቀባት፣ መንገዶችን የመጠገን እንዲሁም የተሽከርካሪና የአሽከርካሪ ብቃትን የማሳደግ እና የእግረኞችን ትክክለኛ የመንገድ አጠቃቀም ልማድ የማዳበር ሥራ በስፍት እንደሚሰራ ተገልጿል።
ከዚህም ባሻገር የተለያዩ አሰራሮች ላይ ቴክኖሎጂን በመጠቀም በቀላሉ አደጋን ማስቀረት የሚቻልበት መንገድ እንደሚመቻች ተጠቁሟል።
ከትራፊክ አደጋ ቅነሳ ጋር ተያይዞ በርካታ መመሪያዎችን አቅፎ የያዘውና በቅርቡ እንደአዲስ ተሻሽሎ በመፅደቅ 2017 በጀት ዓመት ጥር ወር ላይ ተግባራዊ መደረግ የጀመረው የሚኒስትሮች ም/ቤት ደንብ ቁጥር 557/2016 የበለጠ እንደሚያግዝም ተመላክቷል።
የሞትና የጉዳት መጠንን ለመቀነስ ታስቦ የተዘጋጀው የመንገድ ደህንነት ስትራቴጂን በተመለከተም ከትራፊክ ማኔጅመንት በተጨማሪ፤ የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን እና ትራንስፖርት ቢሮን ጨምሮ በርካታ የፌዴራል ተቋማት በበላይነት እንደሚመሩት ተገልጿል። #ahaduradio

የግብፅ መንግሥት 'ስምምነቱ በፅሁፍ ይሁን' ማለቱ በግድቡ ዙሪያ የሚሰሩ ሥራዎች ላይ ገደብ ለማስቀመጥ ነው ሲሉ የዓለም አቀፍ ግንኙነት ባለሙያዎች ገለጹ
#ethiopia | የግብፅ መንግሥት በብራዚል ሪዮ ዲ ጄኔሮ በተካሄደው የብሪክስ አባል አገራት ስብሰባ ላይ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አሕመድ የህዳሴ ግድብን በተመለከተ ኢትዮጵያ ግብፅን እንደማትጎዳ ለተናገሩት ንግግር በፅሁፍ እንዲሆን በይፋ ጠይቋል፡፡
ጉዳዩን አስመልክቶም አሐዱ ባለሙያዎችን ያነጋገረ ሲሆን፤ ባለሙያዎቹ "ግብፅ ይህንን ጥያቄ ያቀረበችው በሕዳሴው ግድቡ ዙሪያ የሚሰሩ ሥራዎች ላይ ህጋዊ ሰነድ በመያዝ ጫና ለማድረግ በማሰብ ነው" ሲሉ ገልጸዋል፡፡
አሐዱ ያነጋገራቸው የፓለቲካ ተንታኙ እና የዓለም አቀፍ ግንኙነት ባለሙያው ጥላሁን ሊበን፤ "ግብጽ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር የነበረው ንግግር በፅሁፍ እንዲሆን የጠየቀችው፤ የሕዳሴው ግድብ ሙሌት እንዲቀንስ እና በዙሪያው ከሚገኙ ደሴቶች አገሪቱ የውጭ ምንዛሬ ገቢ እንዳታገኝ ለማድረግ ነው" ብለዋል፡፡
በተጨማሪም የኢትዮጵያ መንግሥት ስምምነቱን የሚፈራረም ከሆነ፤ ከስምምነቱ ውጭ ለሚሰሩ ሥራዎች በዓለም አቀፍ ሕግ ተጠያቂ ለማድረግ የታሰበ መሆኑን ባለሙያው ተናግረዋል።
"በመሆኑም የኢትዮጵያ መንግሥት ግድቡን በሚገነባበት ጊዜ የዓለም አቀፍ ህግን ያከበረ በመሆኑ ስምምነቱን መፈረም የለበትም" ብለዋል።
ሌላኛው የዓለም አቀፉ ግንኙነት፣ የፖለቲካ ተንታኝ እና የቀድሞ ዲፕሎማቱ ደያሞ ዳሌ በበኩላቸው፤ "ግብፅ ይህን ስምምነት በወረቀት እንዲሆን ጥያቄ ማቅረቧ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ ችግር ቢከሰት የኢትዮጵያ መንግስት ከግድቡ ምንም ውሃ እንዳይጠቀም ለማድረግ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።
አክለውም "ይህን ስምምነት በፊርማ እንዲሆን መጠየቋ ተጨማሪ ግድብ እንዳይገነባ ለማድረግ እና ውሃውን ለመስኖ እንዳንጠቀም ለማድረግ ነው" ብለዋል።
ባለሙያዎቹ ግብፅ በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ የምትፈጥረውን የዲፕሎማሲ ጫና ለመቋቋም የሀገር ውስጥ አንድነትን ማስጠበቅና ማጠናከርም ያስፈልጋል ሲሉም አሳስበዋል። #ahaduradio

በቡሩንዲ በጥንቆላ ማጭበርበር የተከሰሱ 6 ሰዎች በገዢው ፓርቲ አባላት ተደብድበው መገደላቸው ተሰማ
#ethiopia | በቡሩንዲ በጥንቆላ ማጭበርበር የተከሰሱ 6 ግለሰቦች ከገዥው ፓርቲ ጋር ግንኙነት ባለው የወጣቶች ንቅናቄ ቡድን አባላት ተደብድበው መገደላቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት ተናግረዋል፡፡
ድርጊቱ ከቡሩንዲ ዋና ከተማ ቡጁምቡራ በስተምስራቅ 10 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ጋሳራራ ውስጥ ሰኞ ዕለት መፈጸሙ የተገለጸ ሲሆን፤ በተባበሩት መንግሥታት እና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ቡድኖች ዘንድ በሰፊው በሚታወቀው የገዥው ፓርቲ "የኢምቦኔራኩሬ የወጣቶች ንቅናቄ" መፈጸሙን ባለስልጣናቱ ስለመናገራቸው ቲአርቲ ዘግቧል።
እንደ ባለሥልጣናቱ ገለጻ፣ ኢምቦኔራኩሬ የተባለው የወጣቶች ንቅናቄ ቡድን በጥንቆላ ወደ ተከሰሱ አሥር የሚጠጉ ግለሰቦች ቤት በመግባት ጥቃቱን የፈጸመ ሲሆን፤ በሕይወት እያሉ የተቃጠሉ ሁለት ግለሰቦች ጨምሮ ስድስት ሰዎች በዚሁ ጥቃት ተገድለዋል።
"ሌሎቹ በዱላ ተደብድበው ተገድለዋል ወይም በድንጋይ ተወግረው ተገድለዋል" ያሉት ባለስልጣናቱ፤ ይህ አስደንጋጭ እና ሊገለጽ የማይችል የጭካኔ ድርጊት ነበር" ብለዋል፡፡
በተጨማሪም ሦስት ግለሰቦች ጥቃት የደረሰባቸው ሲሆን፤ ነገር ግን ፖሊስ ጣልቃ በመግባት ከታደጋቸው በኋላ በሕይወት መትረፋቸውን አስታውቀዋል፡፡
የቡጁምቡራ ግዛት አስተዳዳሪ ዴሲሬ ንሴንጊዩምቫ ማክሰኞ ዕለት ከግድያው ጋር በተያያዘ 12 ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን አረጋግጠዋል።
የኢምቦኔራኩሬ የወጣቶች ንቅናቄ ቡድን ለረጅም ጊዜ ከባድ የሰብዓዊ መብት ረገጣዎች ክስ ሲቀርብበት ቆይቷል። እንደ ሂዩማን ራይትስ ዎች ያሉ ድርጅቶች በተለይም እ.ኤ.አ. ከ2005 እስከ 2020 ሀገሪቱን በመሩት በቀድሞው ፕሬዝዳንት ፒየር ንኩሩንዚዛ ዘመን፤ ቡድኑ ግለሰቦችን በማሰቃየት እና ያለፍርድ ግድያ በመፈጸም ክስ በተደጋጋሚ ውንጀላ ቀርቦበታል።
የክርስትና እምነት ተከታዮች በብዛት በሚኖሩባት ብሩንዲ፣ ባህላዊ እምነቶች አሁንም ጠንካራ መሆናቸው የሚገለጽ ሲሆን፤ ነገር ግን ምንም እንኳን ማስረጃ ባይኖርም ጥንቆላ በሀገሪቱ በተደጋጋሚ ለሚስጢራዊ ሞት ተጠያቂ መሆኑ ይነገራል። #ahaduradio

Comments