በሙዚቃዎችህ ውስጥ የዕድሜዬ ትዝታ አለ:: በግጥምህ ቅንብብ ውስጥ ስዕል እያቀለምኩ ኖሬያለሁ:: ባንተ ሙዚቃ ውስጥ የተጋድሎን ምስል:: ቀቢፀ ተስፋ ላይ ያቆጠቆጠን ፍቅር:: በዛሬ አትሮንስ ላይ ትናንትናን መመርመርን:: ላለመለያየት ኪዳን ማሰርን:: ከልብ ማሳ ላይ ቂምና አረምን ነቅሎ ፍቅርን መትከልን በብርሀናማ ገፃቸው ሲገለጡ ተመልክቻለሁ::
በ'ሞናሊዛ' ስራህ ውስጥ ለረዥም ዘመናት ጭው ያለ እንቅልፍ ውስጥ የነበረችው አውሮፓ በ15ኛው ክፍለ ዘመን ከእንቅልፏ ስትነቃ አይቻለሁ:: የዘመነ-ህዳሴ ትሩፋት የሆኑት ሥነ-ጥበብ ፣ ሥነ - ህንፃ ፣ ሥነ-ፅሁፍ ፣ ሎጂክ ፣ ፊዚክስ ፣ ኮስሞሎጂ ከፍሎረንስ ተነስተው አለምን ሲያዳርሱ ተመልክቻለሁ:: "ዘመን ከሰለሞን ጥበብ ተበድሮ ታላቅ ብርሃን ሆነ ከሮማ ጀምሮ"
"በሄዋን እንደዋዛ" ስራህ ውስጥ ገልብጣ ልጥትለን የነበረችው የሄዋን መኪና ማርያም ፍሬን ይዛ ለመዳን ምክንያት እንደሆነችን ተመልክቻለሁ:: በ'እንደ ቢራቢሮ' ስራህ እንደ ሩር የሾለች በየሄደችበት የምትለጋ ሴት መዘዝ እንጂ ማር እንደምታመጣ ተገንዝቤያለሁ:: በ"ለማን ልማሽ" ውስጥ የነውርን መጋረጃ በምላስ አለመግለጥን:: ስቆ ማለፍን አይቻለሁ:: በ"ባይገርምሽ" ውስጥ የማቴዎስ ወንጌልን አይቻለሁ::
በ'70 ደረጃ' ስራህ ውስጥ ሩብ ክፍለ ዘመንን አይቻለሁ:: ሸዋ ዳቦ ከመምጣቱ በፊት አርመኖች ፉርኖ ዳቦን ሲቸበችቡ አይቻለሁ:: ሴሼንቶ ሹፌሮች ከጀነራል በላይ ሲከበሩ አይቻለሁ:: ሴቶች ጥላቸውን አይተው ሰዓት ከመገመት ወጥተው ክንዳቸው ላይ ሰዓት አስረው መዘመን ሲጀምሩ አይቻለሁ::
በ'ያስተሰርያል' ውስጥ የተማሪ ማዕበል የሚንጠውን የአብዮት ባህር አይቻለሁ:: ስድሳዎችን አዛውንት ከተማሪ ጋር ስልቅጥ አድርጎ የዋጠውን የምደር አኬልዳማ ከርስን አይቻለሁ:: ለም መሬታችን አራሙቻ ሲያበቅል አይቻለሁ:: ወጣቱ በኤች አይ ቪ ምጣድ ሲቆላ አይቻለሁ:: ይሁ ሁሉ መዓት በፍቅር ሱባዔ እንደሚነፃም ሲተነበይ አይቻለሁ:: የማርቆስ ወንጌልን አይቻለሁ::
'በሼመንደፈር' ባቡር ውስጥ ልዩነት ፣ ሐይማኖት ያላጠረው ኃያሉ ፍቅር የሰብዓዊነትን ፉርጎ እያሳበረ አርያም ሲወስደን አይቻለሁ:: በ'ላምባዲና' ውስጥ መቅረዝ የብርሃን ማኖሪያ እንጂ በራሱ ብርሃን እንዳልሆነ አይቻለሁ። በሉቃስ ወንጌል 18:42 ላይ የተፃፈውን የኢያሪኮውን አይነስውር ታሪክ አይቻለሁ። ካዩት ይልቅ ያለየው እውሩ አምኖት ድህነትን ሲጠይቅና ሲድን አይቻለሁ::
'ሙዚቃ ሕይወቴ' ውስጥ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ የተመሰሉትን የያሬዳዊ ዜማዎችን ግዕዝ ፣ ዕዝል እና አራራይን አይቻለሁ:: አባትህ አቶ ካሳሁን ገርማሞን አይቻለሁ:: ሙዚቃን ፣ ህይወትን ፣ ውበትን እንዲውም መተው የማይችሉት ፍቅር ፣ ፀፀት ፣ ኑዛዜ ፣ ዕጣ ፋንታ እና ከራስ ጋ እርቅ ማውረድን አይቻለሁ::
የፓን አፍሪካን ጀግና ግርማዊነቶን:: ዘመንን በረዥሙ የመተረውን ባለራዕዩን መይሳውን ፤ ቀኙ ገብርዬን:: እንዲሁም ማርኮ የሚምረውን እምዬ ምንይልክን በተለያዩ የግጥም ነዶ ክምር ውስጥ ተመልክቻለሁ:: ኢትዮጵያ ታበፅዕ እደዊአሀ ኅበ እግዚአብሄር! አትሌቶቻችን ሰንደቃችንን በአለም መድረክ ከፍ ሲያደርጉት አይቻለሁ:: የሀገሬ ህልውና ተነካ ብለህ ህመማችንን ታመህ "እያመመው መጣ" ብለህ ልባችን ላይ የወኔ ነጋሪት ስትጎስም ተመልእቻለሁ::
የቱን አንስቼ የቱን እተዋለሁ...የአዳም እግር አሻራን ፣ የዮቶር ርዕስት ሀገሬን አይቻለሁ:: ይቅርታን ፣ መፀፀትን፣ ተማፅኖን የልብ ስብራትን አይቻለሁ:: ለውጥን ፣ ተስፋን ፣ የትናንቱን ፣ የዛሬን የወደፊቱን አይቻለሁ:: አፋኝ ስርዓትን ፊት ለፊት መጋፈጥን አይቻለሁ:: ታላላቆች ሲወደሱ አይቻለሁ:: የስደትን አስከፊነት:: የአገርና የሕዝብ አንድነትን:: ለቅሶና ትካዜ ያጎበጠውን ተስፋ የራቀውን ቀና ማድረግን አይቻለሁ:: ቅዱስ ቃሉ ተሰንጎም አይቻለሁ::
ንጉስ ሆይ ስለገነባኸው የራስህ የሙዚቃ ኢምፓየር እጅ እንነሳለን! ስለ ህያው ስራዎችህ እጅ እንነሳለን! እንኳን ተወለድክልን🙏
49ኛው
Via ዮአኪን በቀለ

11 months ago