Logo
Ethio telecom
በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ይፋዊ የሥራ ርክክብ ተካሄደ

አዲስ ኃላፊነት የተቀበሉት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ክብርት ፍሬሕይወት ታምሩ ከቀድሞው ሚኒስትር ክቡር ዶክተር በለጠ ሞላ የሥራ ኃላፊነቱን በዛሬው ዕለት በይፋ ተረክበዋል።

የሥራ ርክክብ መርሐ ግብሩን በንግግር የከፈቱት ክቡር ዶክተር በለጠ ሞላ፣ ለአዲሷ ሚኒስትር "እንኳን ደህና መጡ" በማለት፤ የተቋሙ አመራሮችና ሠራተኞች የሀገሪቱን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ራዕይ ለማሳካት ከእርሳቸው ጋር በቅርበት በመሥራት ድጋፋቸውን እንዲቀጥሉ አሳስበዋል።

ክብርት ሚኒስትር ፍሬሕይወት ታምሩ በበኩላቸው፣ ክቡር ዶክተር በለጠ ሞላ ባለፉት አምስት ዓመታት ለሰጡት አመራር፣ ላበረከቱት አገልግሎትና ለሀገራችን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ላደረጉት አስተዋጽኦ ከልብ አመስግነዋል። እንዲሁም ለተደረገላቸው ሞቅ ያለ አቀባበል ለእርሳቸውና ለተቋሙ አመራሮች ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የሥራ ኃላፊነቱን መረከባቸውን አስመልክቶ ክብርት ሚኒስትር ፍሬሕይወት ታምሩ ለውድ የኢትዮ ቴሌኮም ቤተሰቦችና ደንበኞች፣ ለመንግሥትና የተቋማት አመራሮች፣ ለሀገር ውስጥና የዓለም አቀፍ አጋሮች እንዲሁም ለወዳጆችቻቸው ያስተላለፉት መልዕክት ከዚህ ፖስት ጋር ያገኙታል።
#ethiopiantechnologyauthority #ethiopiancommunicationsauthority #spacescienceandgeospatialinstitute #innovationandtechnologytalentdevelopmentinstitute #ethiopianintellectualpropertyauthority #nationalresearchfundandcouncil #gsma #itu #oecd #g6countries #huawei #zte #ericsson #nokia

1 day ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.