Logo
EBC
ከማክሮ ኢኮኖሚ መረጋጋት እስከ ዘላቂ ዕድገት፡ የኢትዮጵያ የሁለንተናዊ ብልጽግና ጉዞ
**********

የማንኛውም ሀገር ዘላቂ ደህንነት እና ሉዓላዊነት በጠንካራ ኢኮኖሚ ላይ የተመሠረተ ነው። የመደመር መንግሥት የሀገር ግንባታን ሁለንተናዊ ለማድረግ በያዘው ስትራቴጂያዊ ርዕይ ውስጥ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሥራዎች የለውጡ ማዕከላዊ አንቀሳቃሽ ሞተር ሆነው ይገኛሉ። ፖለቲካዊ ሰላም፣ ማህበራዊ ትስስር እና ኢኮኖሚያዊ ነፃነት ተደጋግፈው ሢሠሩ፣ ሀገርን ወደ ላቀ የብልጽግና ከፍታ ማሸጋገር ይቻላል።

የመደመር መንግሥት ተግባራዊ ያደረገው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ የሀገራችንን እምቅ ሀብት በአግባቡ ለመጠቀም፣ የምርት እና ምርታማነት አቅምን ለማሳደግ እና የግሉን ዘርፍ በስፋት ለማሳተፍ ያስቻለ ትልቅ እርምጃ ናቸው።

ግብርናን በቴክኖሎጂ ማዘመን፣ ክረምትና በጋን ማስተሳሰር፣ የ“ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ፣ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ እና የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን የሚስቡ ምቹ የንግድ አሠራሮችን መዘርጋት የዚህ ሁለንተናዊ ለውጥ ማሳያዎች ናቸው።

የማክሮ ኢኮኖሚ መረጋጋትን ለማረጋገጥ፣ የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር እና የውጭ ምንዛሪ አቅርቦትን ለማሻሻል የተወሰዱት የፖሊሲ እርምጃዎች የኢኮኖሚውን አቅም ወደ ላቀ ደረጃ እያሸጋገሩት ይገኛሉ።

የመደመር መንግሥት የገበያ ሥርዓቱን ፍትሐዊ፣ ተወዳዳሪ እና አሳታፊ በማድረግ ረገድ የወሰዳቸው እርምጃዎች የሀገራችንን የንግድ እና ኢንቨስትመንት ከባቢ በከፍተኛ ደረጃ ለውጠውታል።

በባንክ አገልግሎቶች፣ በፋይናንስ ተደራሽነት እና በካፒታል ገበያ ግንባታ የተከናወኑ ሥራዎችም የኢኮኖሚውን አጠቃላይ አቅም አጎልብተውታል።

ከዚህ በተጨማሪ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማስፋት የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታን እውን ለማድረግ የተሠሩ ሰፋፊ ሥራዎች የገበያውን ተወዳዳሪነት አጠናክረውታል።

እነዚህ ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ዜጎች በፈጠራ ሥራዎች እንዲሰማሩ፣ ሥራ አጥነት እንዲቀነስ እና ፍትሐዊ የሀብት ክፍፍል እንዲሰፍን ምቹ ሁኔታ ፈጥረዋል።

የሰላም እና የልማት ትስስር ተጠናክሮ ሲቀጥል፣ ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ቀጣና የኢኮኖሚ ማዕከል ሆና የምትወጣበት አቅሟ በይበልጥ እየተረጋገጠ ይመጣል።

በሔዋን ጌታቸው
#የመደመርመንግሥት
#ethiopia #economy #homegrowneconomicreform #digitaleconomy #medemer #prosperity #ethiopiatamirt #ebc

1 day ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.