ኢትዮጵያን ይምረጡ | Vote
አትሌት ትዕግሥት አሰፋ በ2026 የዓለም አትሌቲክስ የዓመቱ የላቀ አትሌት ሽልማት እጩዎች ስብስብ ውስጥ ተካተተች
#ethiopia | ስመ-ገናናዋ የኢትዮጵያ የማራቶን አትሌት ትዕግሥት አሰፋ ለ2026 የዓለም አትሌቲክስ የዓመቱ ምርጥ አትሌት ክብር በዕጩነት መመረጧን የዓለም አትሌቲክስ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
አትሌቷ በ2026 የለንደን ማራቶን በሴቶች ብቻ ውድድር የዓለም ክብረወሰንን በ2 ሰዓት ከ15 ደቂቃ ከ41 ሴኮንድ በማሻሻል አንደኛ ወጥታለች።
በተጨማሪም በበርሊን ማራቶን የቦታውን ውድድር ለሦስተኛ ጊዜ በበላይነት ማጠናቀቋ የሚታወስ ሲሆን፣ ያስመዘገበችው የ2 ሰዓት ከ11 ደቂቃ ከ04 ሴኮንድ ሰዓት በሴቶች ማራቶን ታሪክ ሦስተኛው ፈጣን ሰዓት ሆኖ ተመዝግቧል።
በ2023 የዓለም አትሌቲክስ ከስታዲየም ውጭ የዓመቱ ምርጥ አትሌት ተብላ የተሸለመችው አትሌት ትዕግሥት አሰፋ፣ በያዝነው ዓመት በማራቶን ያሳየችው የላቀ ብቃት አሁንም ለታላቁ ሽልማት በዕጩነት እንድትቀርብ አድርጓታል።
አሸናፊውን ለመለየት የሚረዳው የደጋፊዎች የድምፅ አሰጣጥ ስነ-ስርዓት ከመስከረም 26 እስከ ጥቅምት 7 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ የሚካሄድ ሲሆን፣ የስፖርቱ አፍቃሪያንና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቤተሰቦች ድምፅ በመስጠት ድጋፋቸውን እንዲሰጡ ጥሪ ቀርቧል።
ድምፅዎን ለትዕግሥት አሰፋ ለመስጠት ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ።
Who has your vote?
👉 https://bit.ly/4y66IHT
#tigistassefa #worldathletics #marathon #ethiopianathletics #athletics #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

2 days ago