Logo
Tikvah-University
#moe

ትምህርት ሚኒስቴር በ2019 ዓ.ም በመምህራን ትምህርት ኮሌጆች በዕጩ መምህርነት ለመሰልጠን ለሚወዳደሩ አመልካቾች የመቁረጫ ነጥብ ይፋ አድርጓል።

ሚኒስቴሩ ለሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የትምህርት ቢሮዎች በቀን 19/01/2019 ዓ.ም በጻፈው ደብዳቤ፤ የመቁረጫ ነጥቡ የክልሎችን ነባራዊ ሁኔታ እና የ2018 ዓ.ም የፈተና ውጤት ባገናዘበ መልኩ መወሰኑን ገልጿል።

ለዲፕሎማ (12+2) ፕሮግራም

● ለተፈጥሮ እና ለማኅበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 215 እና ከዚያ በላይ ፤ ለሴት ተማሪዎች 205 እና ከዚያ በላይ

● ለአፋር፣ ሶማሌ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና ጋምቤላ ክልሎች የተፈጥሮ ወይም ማኅበራዊ ሳይንስ ወንድ እና ሴት ተማሪዎች 185 እና ከዚያ በላይ

● ለአርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች የተፈጥሮ ወይም ማኅበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች 185 እና ከዚያ በላይ

● በተፈጥሮ ወይም ማኅበራዊ ሳይንስ አካል ጉዳት ያለባቸው ወንድ እና ሴት ተማሪዎች 185 እና ከዚያ በላይ

● በማኅበራዊ ሳይንስ የተፈተኑ ዓይነ ስውራን ወንድ እና ሴት ተማሪዎች 150 እና ከዚያ በላይ

ለሰርተፊኬት (12+1) ፕሮግራም

● ለተፈጥሮ እና ማኅበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 210 እና ከዚያ በላይ ፤ ሴት ተማሪዎች 195 እና ከዚያ በላይ

(ተጨማሪ መረጃ ከላይ ከተያያዘው ምስል ይመልከቱ።)

ይህ የመቁረጫ ነጥብ የሚያገለግለው ለ2019 ዓ.ም የዕጩ መምህራን ውድድር ብቻ መሆኑ ተገልጿል።

@tikvahuniversity
21 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.