Logo
Getu Temesgen
የፖፕ ፍራንሲስ ምሥጢራዊ የግል ማስታወሻ መጽሐፍ ሊመረቅ ነው!
#ethiopia | የሊቀ ጳጳስ ፍራንሲስ ግላዊ ማስታወሻ የያዘው መጽሐፍ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሊታተም ነው።

በካርዲናል ቪክቶር ማኑኤል ፈርናንዴዝ የተዘጋጀው "The Private Diary of Pope Francis" የተሰኘው መጽሐፍ ለንባብ እንደሚበቃ ተገለጸ።

መጽሐፉ ሊቀ ጳጳስ ፍራንሲስ ከ1992 እስከ 2024 ባሉት ዓመታት ውስጥ የጻፏቸውን የግል ማስታወሻዎች መሠረት በማድረግ የተዘጋጀ ነው ተብሏል።

መጽሐፉ በህዳር 24 በመላው ዓለም በ5 ቋንቋዎች ተተርጉሞ በ94 ሀገራት ውስጥ በአንድ ጊዜ ለገበያ እንደሚቀርብ ተገልጿል።

እንግሊዝኛ ዕትሙ በፔንግዊን ራንደም ሀውስ እንዲሁም ጣሊያንኛ ዕትሙ በቫቲካን ማተሚያ ቤት አማካኝነት እንደሚሰራጭ ታውቋል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #popefrancis #vaticannews #catholicchurch #penguinrandomhouse

2 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.