የፖሊስ አባሏ መፀዳጃ ጉድጓድ የተጣለች አራስ ሕፃንን ጡት በማጥባት ከመሞት ታደገቻት።
👉ጉድጓድ ውስጥ ጥላ የተሰወረችውን እናት ለመያዝ ፖሊስ ክትትል እያደረገ ነው።
በደቡብ ምስራቅ ኦሮሚያ ዞን በነንሠቦ ወረዳ 12 ሜትር ጥልቀት ባለው የመፀዳጃ ቤት ጉድጓድ ውስጥ የተጣለችን አራስ ሕፃን የፖሊስ አባሏ በሕብረተሰቡ ትብብር ከጉድጓድ አውጥታ የራሷን ጡት በማጥባት ሕይወቷን መታደጓን የወረዳው ፖሊስ አስታወቀ።
የነንሠቦ ጨቢ ከተማ የፀጥታ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ማሙሽ ከድር እንዳስታወቁት፤ የነንሲቡ ወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት የሴቶችና ሕፃናት ክፍል ኃላፊ የሆነችው ዋና ሳጅን አስቴር ደበሌ ይህንን የሰብአዊነት ተግባር ፈፅማ ሕፃኗን ከሞት ታድጋታለች።
መስከረም 21 ቀን 2109 ዓ.ም ከነንሠቦ ጨቢ አካባቢ ነዋሪዎች ለፖሊስ ባደረሱት ጥቆማ መሠረት፣ ዋና ሳጅን አስቴር ደበሌ 21 ኪሎ ሜትር ያህል መንገድ በመጓዝ መፀዳጃ ጉድጓድ ውስጥ ተጥላ ስታለቅስ የነበረችውን ሕፃን በፍጥነት በሕዝብ ትብብር ማስወጣት ችላለች።
የፖሊስ አባሏ ከመፀዳጃ ጉድጓድ የወጣችውን ሕፃን ሳትጠየፍ ካጠበችው በኋላ የራሷን ጡት በማጥባት በሕይወትና በሞት መካከል የነበረችውን የሳምንታት ዕድሜ አራስ ልጅ ታደጋለች።
አቶ ማሙሽ ከድር አክለው እንደገለጹት፣ የዋና ሳጅን አስቴር ደበሌ ተግባር ለብዙዎች ታላቅ አርአያና የእውነተኛ ሰብአዊነት ማሳያ መሆኑን የገለፁ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ከመፀዳጃ ጉድጓድ የወጣችው ሕፃን በነንሠቦ ጨቢ ጤና ጣቢያ የሕፃናት ማቆያ አስፈላጊው ክትትል ተደርጎላት በሙሉ ጤንነት ላይ ትገኛለች።
የሳምንታት እድሜ ያላትን ልጅ መፀዳጃ ጉድጓድ ውስጥ ጥላ የተሰወረችውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር ለማዋል በፖሊስ በኩል ክትትል እየተደረገበት ይገኛል።
ትግስት ላቀው
#ዳጉ_ጆርናል

2 days ago