Logo
ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal
የኢትዮጵያ አየር መንገድ 10 የቦይንግ ጭነት አውሮፕላኖችን ለመግዛት ስምምነት ተፈራረመ

 
አየር መንገዱ 8 እጅግ ዘመናዊ B777-8F እና 2 B777 የጭነት አውሮፕላኖችን ለመግዛት ከቦይንግ ኩባንያ ጋር ተፈራርሟል።
 
አውሮፕላኖቹ እያንዳንዳቸው እስከ 117 ቶን ጭነት መሸከም የሚችሉና ነዳጅ ቆጣቢ ሲሆኑ፣ የአየር መንገዱን የካርጎ ተደራሽነትና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት በከፍተኛ ደረጃ ያሳድጋሉ።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ B777-8F የጭነት አውሮፕላኖችን በማዘዝ የመጀመሪያው የአፍሪካ አየር መንገድ ሆኗል።

ስምምነቱን የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው እና የቦይንግ ኩባንያ ከፍተኛ ምክትል ፕሬዝዳንት ብራድ ማክሙለን ፈርመውታል።

#ዳጉ_ጆርናል
6 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.