በማንቸስተር ዩናይትድ «ኦልድ ትራፎርድ» ስታዲየም ጸሎት ተደረገ
#ethiopia | በማንቸስተር ዩናይትድ «ኦልድ ትራፎርድ» ስታዲየም በናይጄሪያዊው ፓስተር ጄሪ ኢዜ በተመራው ታላቅ የጸሎት ጉባኤ ላይ በ75 ሺ የሚቆጠሩ ክርስቲያኖች መሳተፋቸው ተገለጸ።
«ስትሪምስ ኦፍ ጆይ ኢንተርናሽናል» በተሰኘው አገልግሎት የተዘጋጀው ይህ «NSPPD UK Prayer Conference» የተሰኘው ጉባኤ፤ ከመላው እንግሊዝ እና ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች የተወጣጡ ክርስቲያኖችን ለአንድ ቀን የጸሎት፣ የምስጋና እና የአምልኮ ጊዜ አንድ ላይ አሰባስቧል።
በቅድሚያ ምዝገባ ይጠይቅ የነበረው ይህ መርሃ ግብር፣ እስከ 74 ሺህ ሰዎችን የመያዝ አቅም ያለውን ታሪካዊውን ስታዲየም ሙሉ በሙሉ በምእመናን አጥለቅልቋል።
በጉባኤው ላይ እንደ መርሲ ቺንዎ ፣ ደንሲን ኦየካን ፣ ሰንሚሶላ አግቤቢ እና ኬስትሪንግስ ያሉ የወንጌል ዘማሪዎች አምልኮን መርተዋል።
ፓስተር ጄሪ ኢዜ በየዕለቱ በኢንተርኔት አማካኝነት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን የሚስበው «ኒው ሲዝን ፕሮፌቲክ ፕሬየርስ ኤንድ ዲክላሬሽንስ» (NSPPD) የተሰኘው ታዋቂ የጸሎት መድረክ መስራች ሲሆን፤ በናይጄሪያ፣ በእንግሊዝ፣ በአሜሪካ እና በካናዳ ቅርንጫፎች ያሉት «ስትሪምስ ኦፍ ጆይ» ቤተክርስቲያን መሪ ነው።
የዘንድሮው የማንቸስተር ጉባኤ ቀደም ሲል በለንደን ከተማ ከተካሄዱት ተመሳሳይ ታላላቅ የጸሎት መርሃ ግብሮች ቀጥሎ የተደረገ ሲሆን፣ያለፈውጰሁለት ዓመት በትዊከንሃም ስታዲየም በተካሄደው ጉባኤ ላይ ከ80 ሺህ በላይ ሰዎች መሳተፋቸው ይታወሳል።
የNSPPD ተከታዮች በየዕለቱ በሚደረጉት እነዚህ የጸሎት ፕሮግራሞች ላይ የተለዩ ተአምራት እና የፈውስ ምስክርነቶች እንደሚስተናገዱ ይናገራሉ።
ከመርሃ ግብሩ ፍጻሜ በኋላ ፓስተር ጄሪ ኢዜ በኢንስታግራም ገጹ ባሰፈረው ስሜታዊ መልእክት «ይህንን ሁሉ ያደረግኸው አንተ እንደሆንክ እኔና አንተ እናውቃለን፤ ልቤ በደስታ ተሞልቷል... እኔን ሁልጊዜ የምትረዳው ጌታ» ሲል የጸሎት ጉባኤው ስኬት ከአቅም በላይ እና በቃላት የማይገለጽ እንደነበር አስታውቋል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu

8 days ago