የኢትዮጵያ እና ጅቡቲ የነዳጅ መስመር ስምምነት የቀጣናውን የኢኮኖሚ ትስስር እንደሚያጠናክር ባለሙያዎች ገለጹ
መስከረም 16 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬዲዮ) ኢትዮጵያ ከጅቡቲ ጋር ያካሔደችው የነዳጅ መስመር ዝርጋታ ስምምነት የሁለቱን ሀገራት ኢኮኖሚያዊ ትስስር እንደሚያጠናክርና ለዘላቂ እድገት አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት አሐዱ ሬዲዮ ጉዳዩን አስመልክቶ ሐሳብ የጠየቃቸው የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ተናግረዋል። ስምምነቱ የቀጣናውን የኢኮኖሚ ትስስር ከማጠናከሩ ባለፈ ሌሎች የጎረቤት ሀገራትንም ሊያካትት እንደሚችል ተጠቅሷል።
የምጣኔ ሀብት ባለሙያው አቶ ዘላለም በቀለ እንደተናገሩት፣ ጅቡቲ የኢትዮጵያ ዋና የወጪና ገቢ ንግድ በር በመሆኗ የሁለቱ ሀገራት የቅርብ ጊዜ የነዳጅ ማስተላለፍ ስምምነት የጋራ ተጠቃሚነትን ያሳድጋል።
የመስመሩን እና የመንገዱን ደኅንነት በጋራ መጠበቅ የሾፌሮችን እና የመሰረተ ልማቱን ደኅንነት ለማረጋገጥ ትልቅ እድል እንደሚፈጥርም ገልጸዋል።
የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ዝርጋታው ሀገሪቱ ለነዳጅ ማጓጓዣ የምታወጣውን ከፍተኛ ወጪ እንደሚቀንስ ለአሐዱ የተናገሩት ደግሞ የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ዶክተር ቆስጠንጢንዮስ በርኸተስፋ ናቸው።
ባለሙያው አክለውም፤ የትራፊክ አደጋዎችን እና የመንገድ ብልሽቶችን ለመቀነስ እንዲሁም የትራንስፖርት ዘርፉን በማዘመን ረጅም ጊዜ የሚወስዱ የወጪ ጫናዎችን ለማስቀረት እንደሚረዳ ገልጸዋል።
በደረጄ መንግሥቱ
#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ፌስቡክ ገጽ፡- https://web.facebook.com/a...
ቴሌግራም ገጽ፡- https://t.me/ahaduradi

10 days ago