የባህል እና የሃይማኖት መገለጫ ብቻ ሳይሆን የአብሮነት እና የኢኮኖሚ ማዕከላት የሆኑት የኢትዮጵያ በዓላት
************************
ኢትዮጵያ በልዩ ልዩ ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ በዓላቷ በዓለም አቀፍ ደረጃ የምትታወቅ ሀገር ናት። የሀገራችን በዓላት የሕዝቦቿን አብሮነት፣ ፍቅር እና ሰላም የሚያንጸባርቁ ናቸው።
እንደ መስቀል ደመራ እና ኢሬቻ ያሉ በዩኔስኮ የዓለም ቅርስ ሆነው የተመዘገቡ በዓላት፣ ኢትዮጵያውያንን ከማስተሳሰር ባለፈ ለሀገራችን የቱሪዝም ገጽታ ግንባታ እና ለኢኮኖሚ ተጠቃሚነት የላቀ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ነው።
በዓላቱ የሃይማኖት እና የባህል ይዘት ያላቸው እና የኢትዮጵያውያን አንድነት መታወቂያዎች ናቸው። ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ያለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ይሳተፍባቸዋል።
ባለፉት ጥቂት ዓመታት በተከናወኑ የልማት ሥራዎች እና በተሻሻሉ የቱሪዝም መዳረሻዎች፣ በእነዚህ በዓላት ላይ የሚሳተፉ ቱሪስቶች ቁጥር ከፍተኛ ዕድገት አሳይቷል።
ይህ የቱሪስት ፍሰት ለሆቴሎች፣ ለትራንስፖርት፣ ለአስጎብኚዎች እና ለተለያዩ የአገልግሎት ዘርፎች ሰፊ የሥራ ዕድል የፈጠረ ሲሆን፣ በከተማዋ ኢኮኖሚ ውስጥ ገንዘብ እንዲሽከረከር በማድረግ ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል።
አዲስ አበባን ጨምሮ ሌሎች ከተሞች አሁን ላይ ኮንፈረንሶችን እና ታላላቅ በዓላትን ለማስተናገድ ምቹ መሠረተ ልማት ያሟሉ፣ ጽዱ እና ውብ በመሆናቸው ለዓለም አቀፍ ጎብኚዎች ተመራጭ መዳረሻዎች ሆነዋል።
በዓላቱን የበለጠ ውጤታማ እና ለቱሪስቶች ምቹ ለማድረግ ባለድርሻ አካላት በዓላቱ በሚከበሩበት ወቅት ለቱሪስቶች ትክክለኛ መረጃ ለመስጠት ዲጂታል ካርታዎችን እና የመረጃ ማዕከላትን መጠቀም፣ ለጎብኚዎች ደኅንነት ቅድሚያ መስጠት እንዲሁም የምግብ ንጽሕናን ከመጠበቅ ጀምሮ የአስጎብኚዎችን ሙያዊ ብቃት ማሳደግ ላይ ትኩረት ሰጥተዋል።
በተጨማሪም ዳያስፖራው በበዓላቱ ላይ በብዛት እንዲታደም እና የሀገሩን ለውጥ በቅርበት እንዲያይ ልዩ አቀባበል እና ፓኬጆች እየተዘጋጁ ይገኛሉ።
የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላት የኢትዮጵያን ባህል እና እሴት ለዓለም የሚያስተዋውቁ ትልልቅ አውደ ርዕዮች ናቸው።
እነዚህን በዓላት በዘመናዊ አሠራር እና በጠንካራ ቅንጅት መምራት፣ ኢትዮጵያን የቱሪዝም ተጠቃሚ ከማድረጉም በላይ የኢኮኖሚ አቅሟን ለመገንባት እና የአብሮነት እሴቷን ለቀጣይ ትውልድ ለማሸጋገር ትልቅ ዕድል ይፈጥራል።
በሔዋን ጌታቸው
#ebcdotstream #visitethiopia #culturalheritage #irreecha #meskel #ethiopia #tourismethiopia

12 days ago