ምስጋና
በምክትል ዋና ዳይሬክተርነት ከተመደብኩበት ጀምሮ አሁን ዋና ዳይሬክተር ሆኜ እያገለገልኩ እስካለሁበት ድረስ ላለፉት ዓመታት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲን በቅንነት፣ በታማኝነት እና በፍፁም ንፅህና ህዝብ እና መንግስት የሰጠኝን አደራ በመጠበቅ ለማገልገል ጥረት አድርጊያለሁ። ሃገር ማገልገል መታደል ነው:: ከሃገርስ በላይ ምናለ?!::
ተቋሙ ላለፉት በርካታ ዓመታት ከነበረበት የችግር ዕዳ ፈቀቅ አድርጓና አላቆ የተሻለ ተቋም መሆን እንዲችል ከስራ ባለደረቦቼ እና ከመላው የኤጀንሲው ሰራተኞች ጋር በጋራ ተግተናል።
ትናንት የዘራነው ፍሬ እንዲሁም ዛሬ የጣልነው መሰረት ነገ የተሻለ አገልግሎት የሚሰጥ ፣ በህዝብ የተመሰከረለት ተቋም እንዲሆን እንዲሁም የነደፍናቸው በርካታ አዳዲስ ሃሳቦች ፍሬ አፍርተው ተቋሙ በሃገራችን የሲቪል ምዝገባ ቀዳሚ ማዕከል እንደሚያደርገው በሙሉ መተማመን ነው።
መሪነት እውቀት እና ችሎታ ብቻ አይደለም። የእግዚአብሔር ረድዔት ከሌለው ከንቱ ነው። ብዙ ተስፋ የሚያስቆርጡ ፣ ጉልበት የሚያደክሙና አታካች ግዚያትን ጉልበት ሆኖ ላገዘኝ ፣ የማይቻሉ የሚመስሉትን በጥበቡ ላስቻለኝ፣ ብዙ ግፍያዎችን በድል ላከናወነኝ ፣ በብዙ ሁኔታ ውስጥ ደግፎ ተስፋ ያለው ተቋም ከባልደርቦቼ ጋር እንድገነባ እና በስተመጨረሻም በክብር የራሴን ድርሻ ተወጥቼ እንድሻገር ላስቻለኝ እግዚአብሔር ክብር ሁሉ ይሁን።
ይህ እንዲሆን በጋራ አብረን ለለፋን አመራሮች፣ ሰራተኞች እና የተቋማችን ቤተስቦች አክብሮቴ የላቀ ሲሆን ተቋሙን በነፃነት እንድመራ በሙሉ ልብ ከጎኔ ለነበሩት እንዲሁም እንደ ሃገር አዲስ ምዕራፍን የሚከፍት እየተቋቋመ የሚገኘው የከተማው አዲስ ተቋምን እንድመራ እድሉን ለሰጡኝ የከተማችን ከንቲባና እሳቸው ለሚመሩት የከተማ አስተዳደር ምስጋናዬ ከፍ ያለነው።
ውድ ከዋና መስርያ ቤት እስከ ወረዳ ጽ/ቤት ያላችሁ አመራሮች እና ሰራተኞች ሁሌም በልቤ ናችሁ ! ቀጣዩ ራዕያችሁ በተቋሙ በመስራታችሁ የምትኮሩበት፣ ሌብነትን የሚጠየፍ ስርዓት የምትገነቡበትና እና ብቁ አመራር የሚወጣበት ሞዴል ሃገራዊ ተቋም መገንባት ነው!
ዮናስ አለማየሁ
ዋና ዳይሬክተር
የአዲስ አበባ ከተማ አዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግስት አገልግሎት
/ Addis Ababa City Addis Mesob One Center Digital Government Service /

11 months ago