Logo
Getu Temesgen
ደቡብ አፍሪካን ያለ መሪ ያስቀረው ምስጢራዊ እረፍት!
#ethiopia | የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ በህመም ምክንያት ከህዝባዊ እንቅስቃሴ እርቀዋል።

የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ከህንድ የብሪክስ (BRICS) ጉባኤ ከተመለሱ በኋላ ባጋጠማቸው የጤና መታወክ ምክንያት ጊዜያዊ እረፍት መውሰዳቸውን የፕሬዝዳንቱ ፅህፈት ቤት አስታወቀ።

73 አመታቸው ላይ የሚገኙት ራማፎዛ የግል ዶክተራቸው እረፍት እንዲያደርጉ እንደመከራቸው ተገልጿል።

ስለ ህመማቸው አይነትም ሆነ ለምን ያህል ጊዜ ከስራ ገበታቸው እንደሚርቁ ዝርዝር መረጃ ግን አልተሰጠም።

በተመሳሳይ መልኩ የሀገሪቱ ምክትል ፕሬዝዳንት ፖል ማሻቲሌ የህክምና ዕረፍት መውሰዳቸውም ታውቋል።

ሁለቱም ከፍተኛ አመራሮች በሌሉበት ወቅት የደቡብ አፍሪካ ህገ-መንግስት ፕሬዝዳንቱ የሚሰይሙት ሚኒስትር በጊዜያዊነት ሀገሪቱን እንዲመራ ይፈቅዳል።

በቅርቡ በኒውዮርክ በሚካሄደው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ደቡብ አፍሪካን ወክለው የሚሳተፉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሮናልድ ላሞላ ይሆናሉ ተብሏል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #cyrilramaphosa #brics #southafrica #worldnews #unga

18 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.