አየር መንገዱ በድመቷ ምክንያት ተቀጣ!
#ethiopia | በቱርክ ኢስታንቡል ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ያልተጠበቀ እንግዳ የፈጠረችው ውዝግብ የአንድን የረጅም ርቀት በረራ ለሁለት ሰዓታት ያህል ለማስተጓጎል በቅታለች።
አንዲት ድመት ተሳፋሪዎችና የኤርፖርቱ ሠራተኞች ባልጠረጠሩት ሁኔታ አምልጣ ወደ አውሮፕላኑ ጭነት (ካርጎ) ክፍል ለመግባት በመሞከሯ ምክንያት መደበኛው የበረራ መርሃ ግብር እንዲስተጓጎል ሆኗል።
ድመቷ ወደ ጭነት ክፍሉ መግባቷ ከታወቀ በኋላ የበረራ ደህንነትን ለማረጋገጥ ሲባል የአውሮፕላኑ ሠራተኞች በአስቸኳይ ፍለጋ ማድረግ መጀመራቸውን ገለፁ።
ነገር ግን ድመቷ በተደረደሩት በርካታ ሻንጣዎችና እቃዎች መካከል ተሸሽጋ በመቆየቷ ምክንያት ፍለጋው ፈታኝና ጊዜ ወሳጅ ሆኖ አልፏል።
የካቢንና የምድር ላይ ሠራተኞቹ ባደረጉት ጥረት ድመቷን በቀላሉ ማግኘት ባለመቻላቸው ሁኔታውን ለመቆጣጠር የቴክኒክ ቡድን አባላት በአስቸኳይ ፍለጋ እንዲያደርጉ ተደርጓል።
የቴክኒክ ቡድኑና የአውሮፕላን ማረፊያው ሠራተኞች ባደረጉት የተቀናጀና ጥንቃቄ የተሞላበት ፍለጋ ድመቷ ያለ ምንም ጉዳት በሰላም ለመያዝ ተችላለች።
ከተያዘች በኋላም አስፈላጊውን እንክብካቤና ምርመራ እንድታገኝ ወደ ኤርፖርቱ የእንስሳት ማረፊያ ክፍል ተወስዳለች።
በዚህ ያልተለመደ ክስተት ምክንያት አውሮፕላኑ ከተያዘለት መደበኛ የመነሻ ሰዓት ሁለት ሰዓታት ዘግይቶ እንዲነሳ ተገዷል።
ተሳፋሪዎችም ድመቷ በሰላም መያዟንና የበረራው ደህንነት መረጋገጡን ተረድተው ጉዞአቸውን ቀጥለዋል ሲል ዩፒአይ አስነብቧል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #istanbulairport #flightdelay #catnews #aviationnews #oddnews

20 days ago