Logo
Getu Temesgen
"የአንድ ሰው ድህነት የኩባንያ ማስታወቂያ መሳሪያ ከማድረግ እንቆጠብ!"
#ethiopia | በኢትዮጵያ አዲስ ዓመትና በሌሎችም በዓላት አዳንድ ተቋማት ለችግረኛ ወገኖቻችን በተለያየ መልኩ ድጋፍ በማድረግ ማህበራዊ ሃላፊነታቸውን ይወጣሉ።

ይህ በእርግጥ የሚደገፍና የሚበረታታ ተግባር ነው።

ነገር ግን ችግረኛ ወገኖችን ፎቶ በማንሳት፣ የኑሮ ችግራቸውን በማሳየትና ይህንንም ለድርጅቱ የማስታወቂያ ዓላማ በማዋል ላይ አንድ ጥያቄ ማንሳት ይገባል።

የአንድ ሰው ድህነት የኩባንያ ማስታወቂያ መሳሪያ ከማድረግ እንቆጠብ!

በዚህ ጉዳይ ላይ ቀደም ሲል በሳምንታዊው ካፒታል የእንግሊዘኛ ጋዜጣ ላይ “Are Companies Giving Back to Society or Seeking Publicity through Corporate Social Responsibility?” በሚል ርዕስ በJuly 12, 2026 አንድ መጣጥፍ ጽፌ ነበር።

ማህበራዊ ሃላፊነት መወጣት ሲተዋወቅ ትኩረቱ በዓላማው፣ በተፈጠረው ተፅዕኖና በተገኘው ለውጥ ላይ እንጂ በተረዱት ሰዎች ችግርና ተጋላጭነት ላይ መሆን የለበትም።

አቅም በፈቀደ ሰዎችን እንርዳ፣ ማህበራዊ ሃላፊነት መወጣት ከማህበረሰቡ በተለያየ መልኩ የወሰድነውን ሃብት ማህበራዊ ሃላፊነታችንን በመወጣት እንመልስ፣ በበጎት ተፅዕኖ እንፍጠር ነገር ግን ድጋፍ የሚደረግለት ግለሰብ ክብር እንጠብቅ።

ትክክለኛ ማህበራዊ ሃላፊነትን መወጣት የሚለካው ባገኘነው የማስታወቂያ መጠን ሳይሆን፣ ድጋፍ በማድረግ ምን ያህል አዎንታዊ ለውጥ ፈጥረናል በሚለው ነው! ሃሳብ ስጡበት!

በደስታና በሃሴት የተሞላ አዲስ ዓመት ከልቤ እመኛልሁ!
መልካም በዓል!

አስቻለው ታምሩ ነኝ

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #corporatesocialresponsibility #humandignity #ethiopia #newyear #aschalewtamiru #socialimpact #ethicalgiving

29 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.