Logo
Getu Temesgen
“መና የሚዘጋጅበት የሰማይ ቤት ከተዘጋ ቆይቷል!”
— ፖሎ ሉሙምባ
#ethiopia | የፓን አፍሪካኒዝም ተሟጋች ፕሮፌሰር ፖሎ ፓትሪክ ሉሙምባ በናይጄሪያ ሌጎስ በተካሄደ ዓለም አቀፍ መድረክ ላይ ለአህጉሪቱ መሪዎችና ለሕዝቡ ጠንከር ያለና አሳሳቢ መልእክት አስተላልፈዋል።

ፕሮፌሰር ሉሙምባ ባደረጉት ንግግር አፍሪካ አሁን ካለችበት አስከፊ ድህነት ኋላቀርነትና መዋቅራዊ ጭቆና ልትወጣ የምትችለው በጾምና በጸሎት ሳይሆን በተግባራዊ ሥራ በሳይንስና በጥበብ የተሞላ እርምጃ መውሰድ ስትጀምር ብቻ እንደሆነ አስገንዝበዋል።

“መና የሚዘጋጅበት የሰማይ ቤት ከተዘጋ ቆይቷል!” ያሉት ፕሮፌሰሩ የችግሮች ሁሉ መፍትሔ ጸሎት ብቻ እንደሆነ ተደርጎ መወሰዱንና ለአህጉሪቱ እድገት ወሳኝ የሆኑ ተግባራዊ መፍትሔዎች ወደ ጎን መገፋታቸውን በፅኑ ኮንነዋል።

የሃይማኖት ተቋማትን ሚና በጥብቅ የነቀፉት ፕሮፌሰሩ በርካታ የአፍሪካ አብያተ ክርስቲያናትና መስጊዶች እራሳቸውን የሞራል የበላይ አድርገው ቢያቀርቡም በሕዝቡ ላይ የሚፈጸመውን መዋቅራዊ ብዝበዛና ስልታዊ ሙስና ግን በዝምታ ያልፉታል ብለዋል።

አብያተ ክርስቲያናትና መስጊዶች ከአማኞቻቸው አሥራትና ምጽዋት በሚሰበስቡበት አህጉር ሕዝቡ አሁንም ንጹህ የመጠጥ ውሃ የኤሌክትሪክ አገልግሎት አጥቶ በጨለማ እንዲኖር ተፈርዶበታል ነው ያሉት።

ፖሮፌሰር ፖሎ እውነተኛ ለውጥ የሚመጣው በተግባር የተደገፈ ጥረት ሲታከልበት ብቻ መሆኑን በማስመር ንግግራቸውን አጠናቅቀዋል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #africa #nigeria #church #plolumumba #poverty #panafricanism #economy

1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.