ኢትዮ ቴሌኮም በመላ ሀገራችን በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ድጋፍ ለሚሹ ተማሪዎች የመማሪያ ደብተር ድጋፍ አደረገ
የኩባንያችን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ የመማሪያ ደብተር ልገሳ መርሃ-ግብሩን በይፋ ያስጀመሩ ሲሆን፤ በዚህም በመላ ሀገራችን በሚገኙ የተመረጡ ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ 105,496 ድጋፍ ለሚሹ ተማሪዎች 1,265,952 የመማሪያ ደብተሮች ድጋፍ ተደርጓል።
ኩባንያችን #ለነገ_ተስፋዎች በሚል መሪ ሐሳብ ያዘጋጀው ይህ የአዲስ ዓመት የደብተር ልገሳ፤ ከ113.3 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ሲሆን፣ ዓላማውም ተማሪዎች በትምህርት መርጃ መሣሪያዎች እጥረት ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው እንዳይቀሩ ተስፋ ለመስጠትና ለመደገፍ ነው።
ኩባንያችን በሚከተለው ሰው-ተኮር ስትራቴጂ መሠረት፣ የደብተር ድጋፉ አካታችነትን ባረጋገጠ መልኩ በአዲስ አበባ እና በሁሉም የሀገራችን ክፍሎች አዲሱ የትምህርት ዘመን ከመጀመሩ በፊት የሚከናወን ነው።
ይህ ተግባር በስትራቴጂያችን ተካትቶ በዕቅድ የሚተገበር ሲሆን፤ የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድ ለማፍራትና በማህበረሰቡ ውስጥ የመደጋገፍ ባህልን ለማጎልበት የምናደርገው ተከታታይ ጥረት አካል ነው።
ኢትዮ ቴሌኮም ባለፉት ሰባት ተከታታይ ዓመታት ለ483.8 ሺህ በላይ ተማሪዎች ከ434.1 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ የመማሪያ ደብተር ድጋፍ አድርጓል።
#ለነገ_ተስፋዎች #ከግንኙነት_ባሻገር_ለወገን_አጋር ! #በአዲስ_ጅማሮ_በአዲስ_ተስፋ_በአዲስ_ዕይታ_2019አዲስ_ዓመት !
#ethiotelecom #nexthorizon #csr #esg #gsma #oecd #g6countries

30 days ago