የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስላለበቁ አሁን ስላለበት ቁመና ሪፖርት አቀረበ
#ethiopia | የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2025/26 የበጀት ዓመት በሁሉም ቁልፍ የሥራ አፈፃፀም መለኪያዎች ታሪካዊ የተባለ ስኬት ማስመዝገቡን ገለጸ።
ባንኩ የዚሁ በጀት ዓመት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርቱን የመንግስት የልማት ድርጅቶችን በባለቤትነት ለሚያስተዳድረው ለኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ያቀረበ ሲሆን በዓመቱ ከ84 ቢሊዮን ብር በላይ የተጣራ ትርፍ ማበሰሩ ተገልጿል።
የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ በሪፖርት ማቅረቢያ መድረኩ ላይ እንደተናገሩት፣ ተቋሙ በበጀት ዓመቱ ሰፋፊ የብድር አማራጮችን በማቅረብ ከ645 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር ለተጠቃሚዎች ማዳረስ ችሏል።
ከዚህም ባሻገር ከ707 ቢሊዮን ብር በላይ አዲስ ተቀማጭ ገንዘብ መሰብሰብ የተቻለ ሲሆን፣ ከውጭ ምንዛሬ በኩል ደግሞ ከ5.5 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል።
ባንኩ የዘመናዊ አሰራር ትራንስፎርሜሽኑን በማፋጠኑም 90 በመቶ የሚሆነው የገንዘብ እንቅስቃሴ በዲጂታል አማራጮች መከናወኑን አቶ አቤ አብራርተዋል።
ተቋሙ ከሚያስመዘግበው የፋይናንስ ስኬት ጎን ለጎን ለማህበራዊ ኃላፊነት ስራዎችና ለተለያዩ ድጋፎች ከ309 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ማድረጉም ተጠቅሷል።
ባንኩ በቀጣዩ በጀት ዓመት የብድር ተደራሽነቱን ይበልጥ በማስፋት ከ1 ትሪሊዮን ብር በላይ ለማቅረብ እንዲሁም የተቀማጭ ገንዘብ አሰባሰቡን ወደ 832.59 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ታላቅ ዕቅድ ይዞ ወደ ሥራ መግባቱ ተገልጿል።
በግምገማ መድረኩ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ መለከት ሳህሉ በበኩላቸው፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያሳየው አጠቃላይ ስኬት ተቋሙ በጥሩና በጤናማ አካሄድ ላይ እንደሚገኝ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው ብለዋል።
ባንኩ የሀገሪቱ አጠቃላይ ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት ሆኖ መቀጠሉን የጠቆሙት ምክትል ሥራ አስፈፃሚዋ፣ ይህ ጥንካሬው ከአለም አቀፍ ተፎካካሪነቱ ጋር ተጣጥሞ እንዲቀጥል አሳስበዋል።
በውይይቱ ወቅት ከተሳታፊዎች ለተነሱት የተለያዩ የአቅጣጫ ጥያቄዎችም በባንኩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አማካኝነት አጥጋቢ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።
(CBE)
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

1 month ago