Logo
Getu Temesgen
በ9 ወር ውስጥ 2722 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ሞተዋል፣ ከዚህ ውስጥ ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዘው የትግራይ ክልል ነው :- የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት
#ethiopia | የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት በ9 ወር ውስጥ 2722 ሰዎች በትራፊክ አደጋ መሞታቸውን እና በአመቱ መጨረሻ ላይ ሁሉም መረጃዎች ሲሰባሰቡ የሞት መጠኑ ከፍተኛ ጭማሪ ሊኖረው እንደሚችል ገልጿል።

የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ምክትል ስራ አስኪያጅ መሀመድ ሀሰን የባለፉት አመታት ሪፖርቶችን በማሰባሰብ የትራፊክ አደጋ በምን ደረጃ ላይ መሆኑን የሚያሳይ ጥናት አድርገናል ብለዋል።

አቶ መሀመድ ሀሰን ስለጥናቱ በዝርዝር ምን አሉ?

የአለም ጤና ድርጅት እ.ኤ.አ በ2023 ይፋ ባደረገው ሪፖርት በየአመቱ 1.19 ሚሊየን ገደማ ሰዎች ይሞታሉ፣ ከዚህ ውስጥ 13 በመቶ የሚሆነውን ኢትዮጵያ ትይዛለች።

በየአመቱ ከ3 እስከ 4 ሺህ ሰዎች ይሞታሉ፣ ከዚህ ውስጥ ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዙት ህፃናት እና ከ15-29 እድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ወጣቶች ናቸው። በዚህ ሁኔታ ከቀጠለ ሀገር ምን ያክል እየተጎዳች መሆኑን መገንዘብ ተችሏል።

በ2016 ዓ.ም በፌዴራል ፖሊስ በኩል በተደረገ ሪፖርት 3111 ሰዎች ሞተዋል። 10 ሺህ ዜጎች ከቀላል እስከ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ወደ 4 ቢሊዮን አካባቢ የንብረት ውድመት ደርሷል።

በ2017 ዓ.ም ከባለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር 489 አካባቢ አደጋዎች ጭማሪ አለው፣ ከባለፈው አመት ዘጠኝ ወር ጋር የዘንድሮው አመት ሲነፃፀር 21 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።

አሽከርካሪዎች ለአደጋ የሚጋለጡበት ምክንያት ምንድን ነው ?

- ከተፈቀደላቸው የፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከር፤
- እርቀትን ጠብቆ አለማሽከርከር
- በአሽከርካሪዎች የሥነ-ምግባር ጉድለት፤
- ሹፌሮች ያለምንም እረፍት እስከ 72 ስአት ማሽከርከር ተጠቃሽ ናቸው።

አደጋዎች የሚበዙት ምቹ በሆኑበት ቦታ ላይ ነው።

በትግራይ ክልል በ9 ወር ውስጥ 264 ዜጎች ሞተዋል። ይህ የሆነው አደጋዎች ከተከሰቱበት እስከ 1 ወር የህክምና አገልግሎት አግኝተው ህይወታቸው የሚያልፉትንም ስለተካተቱ ነው። ይሁን እንጅ በ2017 ዓ.ም የትራፊክ አደጋ የመጨመር አዝማሚያ ላይ ነው። #tm

11 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.