Logo
Getu Temesgen
"ዶላርን በዶላር እንመልሳለን!" የባለዶላሮቹ ፀብ!

*ላይ የ50 በመቶ የታሪፍ ጭማሪ ጥሏል።
#ethiopia | የአሜሪካ አስተዳደር የ20 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ ባላቸው የካናዳ ምርቶች ላይ 50 በመቶ ታሪፍ ጣለ።

አስተዳደሩ እንደ የእንጨት ውጤቶች አልኮል እና የስፖርት እቃዎች ላይ ነው የ50 በመቶ የታሪፍ ጭማሪ የጣለው።

ሁለቱ ሀገራት በዋሽንግተን ሲያካሂዱት የነበረው የንግድ ድርድር በመጨረሻው ደቂቃ ላይ ባልተስማሙባቸው ነጥቦች ምክንያት ተቋርጧል።

የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ካርኒ አሜሪካ ያቀረበችው የመጨረሻ ሀሳብ ፍትሃዊ ያልሆነና አስተማማኝነት የጎደለው ነው በማለት ድርድሩን አግደው ተወካዮቻቸውን ወደ ኦታዋ መልሰዋል።

ካናዳ የአሜሪካን እርምጃ ለመመለስ ተመጣጣኝ የሆነ ታሪፍ በቅርብ ቀናት ውስጥ እንደምትጥል አስታውቃለች።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #canada #america #tradewar #imposes #tariff #taxation

1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.