Logo
Getu Temesgen
"እንኳን ደስ አላችሁ!!"
ምክክራችን ለዛሬው አለቀ

* ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት እንደጻፉት!...
#ethiopia | የምክክር ሂደታችን የዚህ ምዕራፍ ተጠናቅቋል። ሌላውን ምዕራፍ ቀጣዩ ትውልድ አሻሽሎ ይቀጥልበታል።
ምክክር ሆኖብን ነው እንጂ ጦርነት ቢሆን ኖሮ ዐርባ ቀን አይፈጅብንም ነበር። የዐድዋን ጦርነት በ9 ስዓት ውስጥ የጨረስን ጀግኖች ነንኮ። የጦርነትን ያህል ምክክር ልምድ የለንም። አትፍረዱብን።

እንዲህ ሆነ እንዲያ ተፈጠረ የምንለው ምክክር ሆኖብን ነው እንጂ ጦርነት ቢሆንማ ይህ ሁሉ ወሬ ከየት ይመጣል።

እኛም ተከታታዮች ምክክሩን በጦርነት መንፈስ ስለተከታተልነው ነው - ተኮሰ- ሳተ- መከተ-ሸሸ- ፈረጠጠ -አሸነፈ-ተሸነፈ- ስንል የከረምነው።

በጦርነት ልማድ ምክክርን መሥራትና መከታተል እንዴት ፈታኝ መሰላችሁ።

እንኳን ደስ አላችሁ።

​#nationaldialogue #consultationprocess #peacebuilding #ethiopianpolitics #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.