Logo
YenetaTube
ቡርኪናፋሶ የምዕራባውያን ተቋማት አገደች !

የቡርኪናፋሶው ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ትራኦሬ ሀገሪቱን የማበጥበጥ ሰላም የመንሳት ማህበራዊ እረፍት የማሳጣት አላማ አላቸው ያሏቸውን አራት በምዕራባውያን እና አሜሪካ የሚመሩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ፈቃዳቸውን መቀማቱን እና ሌሎች ሁለት ማህበራትን ማገዱ ተነገረ ።

እ.ኤ.አ. በሴፕቴምበር 2022 በተካሄደው መፈንቅለ መንግስት ስልጣኑን የተቆጣጠረው የቡርኪና ጦር ሃይል ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የብሄራዊ ሉዓላዊነትን ማስመለስን ከቅድሚያ ጉዳዮች ውስጥ አንዱ በማድረግ በ"ግጭት " ተግባር የተከሰሱ ዲፕሎማቶች ከሀገር እንዲባረሩ ተደርገዋል፣በርካታ የውጭ ሚዲያዎችም ለመዝጋት ተገደዋል።

የወታደራዊው መንግስት ቀጣይነት ያለው የጸጥታ እርምጃዎች አካል የሆነዉና በሰኔ ወር አጋማሽ ላይ የሀገሪቱ ፍርድ ቤት ባወጣው ድንጋጌዎች መሰረት ሀገሪቱን ለብጥብጥ እና ግጭት ለመዳረግ እያሴሩ ነዉ ያሏቸውን አራት የውጭ መንግስታዊ ያልሆኑ ማኅበራት ለሶስት ወራት ታግደዋል፣ ሁለቱን በመረጃ ጥሰት ክስ በመመስረት ፍርድ ቤት አስቁመዋቸዋል ይህ እርምጃም ቀጣይነት እንዳለዉ አረጋግጫለሁ ሲል የመንግስት ሚኒስትርን ዋቢ በማድረግ የዘገበው አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ነዉ ።

11 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.