የመጀመሪያው ትሪሊየነር ተፈጠረ ድህነትን ለማጥፋት ግን ከ200 ዓመታት በላይ ይወስዳል!
#ethiopia | በዓለም አቀፍ ደረጃ በሀብታሞች እና በድሆች መካከል ያለው ሰፊ የሀብት ልዩነት አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ላይ መድረሱን የኢኮኖሚ አኃዞች ገለጹ።
የፎርብስ የሀብት መዝገብ መሠረት በማድረግ የወጡ መረጃዎች እንደሚያመላክቱት የዓለማችን እጅግ ባለሀብት የሆኑ ግለሰቦች ሀብት በከፍተኛ ፍጥነት በማደግ ላይ ይገኛል።
የኢሎን መስክ የሀብት መጠን የ1 ትሪሊዮን ዶላር ገደብን በማለፍ በዓለም ታሪክ የመጀመርያው ትሪሊየነር መሆን ችሏል።
የቢሊየነሮች ሀብት በደቂቃ በከፍተኛ መጠን በሚጨምርበት በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ ድህነትን ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት ከ200 አመታት በላይ ሊወስድ እንደሚችል ነው ፎርብስ ባወጣው መረጃ የተገለፀው።
የኤሎን መስክ አንድ ትሪሊዮን ሀብት በዓለም ላይ ካሉ 46 በመቶ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ሰዎች አጠቃላይ ሀብት ጋር እኩል ወይም የሚበልጥ ሆኖ ተገኝቷል ይላል።
አንድ ሰው 1 ትሪሊየን ዶላር ለመጨረስ በቀን 1 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ቢያደርግ እንኳ 2,740 ይወስድበታል።
እንደዚሁም የዚህ ሀብት 10 በመቶ ብቻ ታክስ ቢደረግ በዓለም ላይ በከፍተኛ ድህነት ውስጥ የሚኖሩ ከ800 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ለሙሉ አንድ ዓመት ከድህነት ማውጣት እንደሚችልም ነው መረጃው የጠቆመው።
የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች እንደሚናገሩት የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች እና የሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘርፍ ዕድገት የጥቂት ባለሀብቶችን ሀብት በከፍተኛ ፍጥነት እያሳደገው ይገኛል ይላሉ።
በተቃራኒው የታችኛው ህብረተሰብ ክፍል ግን በዋጋ ንረት እና በስራ እጦት ምክንያት ወደ ጥልቅ ድህነት እየተገፋ ይገኛል ብለዋል።
ይህ የሀብታምና ድሀ ከፍተኛ ልዩነት ለማጥበብ የዓለም ሀገራት መሪዎች ጥብቅ የሀብት ታክስ እንዲጥሉ እና ፍትሃዊ የኢኮኖሚ ፖሊሲዎችን እንዲተገብሩ ሲሉ ባለሙያዎች መክረዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #marginalgaps #economy #poor #rich #business #billionaire #taxation

2 months ago